ከፌደራል እስከ ክልል ያለው የትምባሆ ቁጥጥር ሪፖርት ቅብብሎሽ እና እርምጃ አወሳሰድ ሊጠናከር እንደሚገባው ተገለፀ፡፡
መጋቢት 2/ 2017 ዓ.ም አዳማ በተካሄደው የፌደራልና የክልሎች የትምባሆ ቁጥጥር አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ሲከፍቱ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሄራን ገርባ እንደተናገሩት ምንም እንኳን እንደ አገር በትምባሆ ቁጥጥር ዙሪያ አበረታች ውጤቶች ቢገኙም ከፌደራል እስከ ክልል ያለው የትምባሆ ቁጥጥር ሪፖርት ቅብብሎሽ እና እርምጃ የሚጠበቀውን ያህል ባለመሆኑ መጠናከር አለበት፡፡
በአገር አቀፍ ደረጃ የትምባሆ ቁጥጥርን የማስተባበርና የማስተዳደር ኃላፊነት በአዋጅ ለባለስልጣ መስሪያ ቤቱ መሰጠቱን የተናገሩት ዋና ዳይሬክተሯ የትምባሆ ክልከላ ሕጉን በመፈፀም ላይ ያሉት የክልል ተቆጣጣሪ አካላት በትምባሆ ቁጥጥር ዙሪያ የሚሠሯቸውን ስራዎች በሙሉ ለባለስልጣኑ ሪፖርት በማድረግ ረገድ ያለውን ክፍተት በመገንዘብ ወደ እያንዳንዱ ክልል ወርደው ድጋፍ የሚያደርጉ ባለሙያዎች እንዲመደቡ ትዕዛዝ መሰጠቱን አስታውቀዋል፡፡
ባለስልጣኑ ከክልል ተቆጣጣሪ አካላት ጋር በትምባሆ ቁጥጥር ዙሪያ የሚያደርገው የሁለት ቀናት ግምግማ ዓላማ እስካሁ በተሰሩ ስራዎች ዙሪያ የተገኙ ጠንካራ ልምዶችን በመቀመር ወደ ሌሎች ለማስፋትና ድክመቶችን ነቅሶ በማውጣት ለማረም እንዲሁም በቀጣይ ተጠናክረው ሊሰሩ የሚገባቸው የቁጥጥር ስራዎችን ለይቶ በማውጣት አቅጣጫ ለማስቀመጥ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሯ አብራርተዋል፡፡
በግምገማ መድረኩ የሁሉም ክልሎችና የሁለቱ ከተማ አስተዳደር የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት በትምባሆ ቁጥጥር ዙሪያ የተሠሩ ስራዎች የዕቅድ አፈፃጸም ቀርቦ ሰፊ ውይይት እንደሚደረግ ይጠበቃል፡፡