በትምባሆ ቁጥጥር ሕጉ ዙሪያ ግንዛቤ ከመፍጠር አኳያ በቀጣይነት በትኩረት ለመስራት መዘጋጀታቸውን የክልል ተቆጣጣሪ አካላት አስታወቁ፡፡
መጋቢት 3 /2017 ዓ.ም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከክልል ተቆጣጣሪ አካላት ጋር በትምባሆ ቁጥጥር ዙሪያ ባሰናዳው የስድስት ወራት የግምገማ መድረክ ላይ በትምባሆ ቁጥጥር ዙሪያ የሚሰሩ የክልል ባለሙያዎችና አስተባባሪዎች እንደተናገሩት የትምባሆ ቁጥጥር ሕጉን በማስተዋወቅ ረገድ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ ለፍትህ አካላት፣ለሚዲያዎችና በአጠቃላይ ለሕብረተሰቡ ለመስራት መዘጋጀታቸውን ገልፀዋል፡፡
ለዚህም የህብረተሰብ ንቅናቄ መድረኮች በመፍጠርና አመራሩን በማሳተፍ የቁጥጥር ስራዎችን የመደገፍ ስራዎችን እንዲሰሩ በትኩረት ለመስራት መዘጋጀታቸውን ገልፀው ከባለስልጣኑ የሚደረጉ የክትትልና የድጋፍ ስራዎች በተጠናከረ መልኩ ሊሰራ ይገባል ብለዋል፡፡
ከተሞችንና ተቋማትን ከትምባሆ ጭስ ነፃ በማድረግ ሞዴል ተቋማትና ከተሞች የተፈጠሩበት፣ የትምባሆ ቁጥጥር ስራዎችን በእያንዳንዱ ሴክተር ተቋማት ውስጥ ተካተው እንዲሰሩ ከማድረግ፣ ከፍትህ አካላት ጋር በጋራ ከመስራት ረገድና ቁጥጥርን አቅዶ ከመስራት አኳያ ያሉ ምርጥ ተሞክሮዎችን ከራሳቸው ነባራዊ ሁኔታ አንፃር አጣጥመው ለመተግበር መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል፡፡