EthioTech Talk


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Технологии


Welcome to Ethio Tech Talk – Your Gateway to the Future of Technology and Programming! 🚀✨
Embark on a journey into the realms of technology and programming with us.

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Технологии
Статистика
Фильтр публикаций




✅✅✅ Dark web ምንድን ነው???

ዌብ(web) ማለት ማንኛውም ኮምፒውተራችን ወይም ስልካችን ላይ ያለን መረጃ ኢንተርኔትን ተጠቅመን ለሌሎች የምናጋራበት ዘዴ(Information sharing system) ነው። ሶስት የዌብ አይነቶች ያሉ ሲሆን እነርሱም surface web፣ deep web እና dark web ናቸው።
➡️ surface web የምንለው ማንኛውም ሰው የተለመዱትን ብሮዘሮች(chrome, firefox እና የመሳሰሉትን) ተጠቅሞ access ማድረግ የሚችላቸው ሲሆን ይህም አጠቃላይ ኢንተርኔት ላይ ካለው መረጃ አስር ፐርሰንቱን ብቻ ይሸፍናል።

➡️ Deep webን የተለመዱትን ብሮዘሮች ተጠቅመን access ማድረግ አንችልም። ይህን የዌብ አይነት ተጠቅመን የምናገኛቸው ፔጆችም ፓስወርድ  ያላቸው ሴኪውርድ የመንግስት መረጃዎችን የያዙ ናቸው።

✅✅✅ Dark web በተወሰነ መልኩ ከ deep web ጋር ተመሳሳይ ቢመስልም ውስጡ ባሉት መረጃዎች ትልቅ ልዩነት አላቸው።
dark webን ለመጠቀም እንደ ቶር አይነት ከተለመዱት የተለዩ ብሮዘሮችን መጠቀም ያስፈልጋል። በdark web ውስጥ የሚካተቱት መረጃዎች እጅግ አደገኛ ሲሆኑ ተጠቃሚው ተገቢውን ጥንቃቄ ካላደረገ በእያንዳንዱ በሚያደርጋቸው ክሊኮች አደጋ ውስጥ የመግባት እድሉ ሰፊ ነው። በዚህ web ውስጥ በብዛት የምናገኘው  የተሰረቁ(hack የተደረጉ የግለሰብ መረጃዎች) ለገበያ የሚቀርቡባቸው ሳይቶች፣ ጊዜ ያለፈባቸው እና ህገ ወጥ መድሀኒቶች የሚሸጡባቸው ሳይቶች፣ ሰዎችን ከፍሎ ማስገደያ ሳይቶች፣ ከትንሽ እስከ ትልቅ የጦር መሳሪያ የሚገበያዩባቸው ሳይቶች እና ሌሎችም ከተለመደው የተለዩ አደገኛ ሳይቶች ናቸው።

‼️ dark webን አለመጠቀም ይመከራል። ግደታ ሆኖ የምንጠቀም ከሆነ ግን ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርብናል። ያለንበትን ቦታ ወይም ሎኬሽናችንን ለመቀየር ቪፒን መጠቀም፣ የተለያዩ አይነት scam ሊንኮች ሊላኩልን ስለሚችል አለመክፈት እና ሌሎች ራሳችንን ከሀከሮች ልንጠብቅባቸው የምንችላቸውን ዘደዎች መጠቀም ያስፈልጋል።

ይህ ቻናል ይጠቅማል ለሚሉት ሰው share ማድረግዎን እንዳይረሱ🙏🙏🙏

@saleslikegift
@saleslikegift


✅✅✅ ላራቬል(Laravel)  setup እና የመጀመሪያ ፕሮጀክት።👇👇👇

ላራቬል(laravel) የphp ፍሬምወርክ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት ለbackend development በስፋት ጥቅም ላይ ይውላል።

❔setup ለማድረግ ምን ያስፈልጋል??

➡️ በመጀመሪያ php በኮምፒውተራችሁ ላይ መጫናችሁን አረጋግጡ። ካልጫናችሁ 👉  https://www.php.net/downloads.php ውስጥ በመግባት የእናንተን OS መርጣችሁ ጫኑና install አድርጉ። ከዚያም ፓዙን enviromental variable ውስጥ አስገቡ። ይህን ለማድረግ ፋይሉን የጫናችሁበት ፎልደር ውስጥ ገብታችሁ bin እስከሚለው ፓዙን ኮፒ አድርጉ። ከዚያም የኮምፒውተራችሁ setting ውስጥ ገብታችሁ enviromental variable ከዚያም edit ብላችሁ ኮፒ ያደረጋችሁትን ፓዝ ፔስት ካደረጋችሁ በኋላ ok ብላችሁ ውጡ።
➡️  በመቀጠል composer ስለሚያስፈልጋችሁ ከ 👉https://getcomposer.org/download/ ላይ ለእናንተ OS ጭናችሁ install አድርጉና ከላይ ባየነው መልኩ ፓዙን አስተካክሉ።

❔የመጀመሪያ ፕሮጀክት(first project)  እንደት እንፈጥራለን??

✅ በመጀመሪያ ፎልደር ፍጠሩ። ፎልደራችሁን በvisual studio ወይም ሌላ text editor ክፈቱ። ከዚያም terminal ከፍታችሁ 👇 እነዚህን ኮማንዶች execute አድርጉ።

🧑‍💻 composer create-project laravel/laravel

ትንሽ ጊዜ ሊቆይ ስለሚችል እስከሚጨርስ በትዕግስት ጠብቁ።

🧑‍💻 cd

🧑‍💻 php artisan serve

ምንም አይነት ስህተት ካልሰራችሁ የ development server ሊንክ ተርሚናላችሁ ላይ ታገኛላችሁ። ሊንኩ ላይ በመጫን ወደ ብሮውዘራችሁ ገብታችሁ የመጀመሪያ(starting) ፕሮጀክታችሁን ማየት ትችላላችሁ።

ለበለጠ መረጃ ዶክሜንቴሽኑን 👉 https://laravel.com/docs/10.x/installation  ላይ በመግባት ማየት ትችላላችሁ።

ሌሎች ጠቃሚ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናሉን share ማድረግዎን እንዳይረሱ።🙏🙏🙏


✅✅✅ Slicethepie ትክክለኛ የገንዘብ መስሪያ ፕላትፎርም ነው???👇👇👇

❔slicethepie ምንድን ነው?

slicethepie የተለያዩ የsurvey ጥያቄዎችን በመመለስ እንድሁም ሙዚቃዎችን ለ 90 ሰከንድ ሰምታችሁ አስተያየት እና review በመስጠት ገንዘብ የምታገኙበት የፍሪላንስ ፕላትፎርም ነው። በዚህ ፕላትፎርም በአንድ ስራ ከ0.01 እስከ 0.19 ዶላር እንደስራው ሁኔታ ወደ አካውንታችሁ ማስገባት ትችላላችሁ። በተጨማሪ የሚመጡላችሁን survey's በጥንቃቄ ከሞላችሁ ከአንዱ ብቻ በርከት ያለ ገንዘብ ታገኙበታላችሁ። ያጠራቀማችሁት ገንዘብ ከ10 ዶላር በላይ ሲሆን ወደ paypal አካውንታችሁ በቀጥታ መላክ ያስችላችኋል።

❔መጠቀም የምንችለው እንደት ነው?

በመጀመሪያ የፕላትፎርሙ offical website www.slicethepie.com ላይ ገብታችሁ አስፈላጊውን form ሞልታችሁ አካውንት መክፈት ይኖርባችኋል። አካውንት በምትከፍቱበት ጊዜ ኢሜላችሁን verify እንድታደርጉ እና ሌሎች ቀለል ያሉ ጥያቄዎቹን እንድትመልሱ ትጠየቃላችሁ። ይህን ከጨረሳችሁ በኋላ በቀጥታ ወደ ዳሽቦርዳችሁ ገብታችሁ ስራ መጀመር ትችላላችሁ።

❔መወሰድ ያለባቸው ጥንቃቄዎች ምን ምን ናቸው?

1⃣ ዌብሳይቱ ኢትዮጲያ ውስጥ ስለማይሰራ vpn ተጠቅማችሁ ሌላ ሀገር እንዳላችሁ ማስመሰል ይኖርባችኋል። ነገር ግን vpn እየተጠቀማችሁ እንደሆነ ካዎቁ ለ security issue ሲባል አካውንታችሁ block ይደረጋል። ስለሆነም ቪፒናችሁ location እና ip address በየጊዜው እንደማይቀያይር ማረጋገጥ ይኖርባችኋል። ከዚህ በፊት በሰራነው ፖስት ላይ እንደት አካውንታችሁ ብሎክ እንዳይደረግ ማድረግ እንደምትችሉ ለማሳየት መሞከራችን ይታወሳል።

2⃣ ገንዘብ ከአካውንታችሁ ወደ paypal በምትልኩበት ጊዜ paypal አካውንታችሁ ላይ የምትጠቀሙት ኢሜል slicethepie አካውንት ከከፈታችሁበት ኢሜል ጋር ተመሳሳይ ካልሆነ ገንዘቡን መላክ አትችሉም። ስለዚህ አካውንት በምትከፍቱበት ሰዓት ተመሳሳይ ኢሜል መጠቀማችሁን አረጋግጡ።

✅slicethepie 100% real ነው።

ቻናሉን share ያድርጉ ፣ ሌሎች ጠቃሚ መረጃዎችን ማግኘትዎን ያረጋግጡ። 🙏🙏🙏

@ethiotecchtalk
@ethiotecchtalk


1.2 ሚሊዮን በላይ LED ስለታጀበው እና አጠቃላይ ስፋቱ ከአስር የኳስ ሜዳዎች ስለሚበልጠው sphere ስለሚባለው አዳራሽ ሰምታችኋል???👇👇

ወትሮም በቅንጡ እና እጅግ ዘመናዊ ህንፃዎች የምትታዎቀው የሀገረ አሜሪካዋ Las Vegas ውስጥ የተገነባው የክብ ቅርፅ ያለው ሕንፃ የሰሞኑ መነጋገሪያ መሆን ችሏል።
ለመገንባት በአጠቃላይ ከ2.5 ቢሊዮን ዶላር በላይ የፈጀ ሲሆን ይህም በአለም ላይ ካሉ ህንፃዎች በጣም ውዱ ያደርገዋል።

ይህን ህንፃ ከሌሎቹ የሚለየው ውድ መሆኑ ብቻ አይደለም። ይልቁንስ ህንፃውን ለመስራት ጥቅም ላይ የዋለው የቴክኖሎጅና የኢንጅነሪንግ ጥበብ እንጅ። ክቡ አዳራሽ 54 ሺህ ካሬ ሜትር(ወይንም 10 የኳስ ሜዳዎችን የሚያክል ስፋት ያለው) HD ቪድዮ ማጫዎት የሚችል ስክሪን የለበሰ ሲሆን ይህም  ስክሪን ከ50 ሜትር ርቀት ላይ  በአሁኑ ሰዓት ከ30cm ርቀት ከፍተኛ የምስል ጥራት ከሚሰጠው የapple Tab በብዙ እጥፍ የተሻለ የምስል ጥራት ይሰጣል።

አዳራሹ 18 ሺህ ሰዎችን መያዝ የሚችል ሲሆን 15ሺህ ካሬ ሜትር ስፋት ያለው 360 ድግሪ እይታን የሚሰጥ ባለ 16K HD ስክሪን በውስጥ በኩል ተገጥሞለታል።

የተራቀቀ ሳዉንድ ኢንጅነሪንግ ጥቅም ላይ የዋለበት ይህ አዳራሽ  በአጠቃላይ 167 ሺህ ስፒከሮች ከስክሪኑ ጀርባ ተገጥመውለታል። እንደ ባለሙያዎቹ ገለፃ ለእያንዳንዱ ታዳሚ የHead Phone ጥራት ያለው ድምፅ የሚያደርስ ሲሆን ይህም ማለት ለእያንዳንዱ ታዳሚ የ8 ስፒከሮች ድምፅ ይደርሰዋል እንደማለት ነው። ሌላው አስደናቂ ነገር ጎን ለጎን የተቀመጡ ሁለት ሰዎች አንዱ አንዱን ሳይረብሸው ሁለት የተለያየ ቋንቋ መስማት እንዲችሉ ማድረጉ ነው።

አዳራሹ ከውጭ ባለው ስክሪኑ በኩል ውስጥ ላይ ያሉትን ትዕይንቶች እንዲሁም የተለያዩ ክብ ቅርፅ ያላቸውን እንደ ኢሞጅ አይነት ምስሎች በማራኪ ሁኔታ ማሳየት ይችላል።

በአጠቃላይ ህንፃው ታዳሚዎች አዳራሽ ውስጥ ያሉ እስከማይመስላቸው ድረስ ስሜትን መቆጣጠር የሚችሉ ቴክኖሎጅዎች የተገጠሙለት ሲሆን ባለሙያዎቹ ህንፃውን ለመስራት ወደ ኋላም ወደፊትም ያሉ የፊዚክስ ቀመሮችን መጠቀማቸውን ተናግረዋል።

ሌሎች ጠቃሚ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናሉን share ማድረግዎን እንዳይረሱ።🙏🙏🙏

@ethiotecchtalk
@ethiotecchtalk




እነዚህን ትሪኮች android ስልካችሁ ላይ ሞክራችሁ ታውቃላችሁ???👇👇

1⃣ የስልካችሁ lock screen ላይ እንዴ ስልክ ቁጥር ፣ ኢሜይል እና ሌሎች መልእክቶችን ማስቀመጥ ትችላላችሁ።
ይህም የሚጠቅመው ስልካችሁ ቢጠፋና ሌላ ሰው አግኝቶት ሊመልስላችሁ ቢፈልግ እናንተን ሊያገኝ ሚችልበትን አድራሻ lock screen ላይ ማስቀመጥ ትችላላችሁ።

በመጀመሪያ የስልካችሁን setting ከከፈታችሁ በኋላ lock screen and security ከዚያ contact information ላይ የፈለጋችችሁትን ነገር ፅፋችሁ done ማለት ነው።

2⃣ ሌላኛው setting ስልካችሁ ላይ ያለን ማንኛውንም ነገር ማጉላት የሚያስችል ሲሆን ይህም ለማየት የሚያስቸግራችሁን ነገር triple click በማድረግ በቀላሉ ለማየት ያስችላችኋል።

setting ውስጥ ከገባችሁ በኋላ Accessibility ከዚያም Magnification ውስጥ Triple tap screen to magnify የሚለውን on ማድረግ ነው።

3⃣ ስልካችሁ ላይ game ሳትጭኑ መጫዎት ከፈለጋችሁ ደግሞ  secret game አለላችሁ። ይህንንም ለማድረግ setting ውስጥ about phone ከዚያም android verssion  የሚለውን ደጋግማችሁ  በመጫን ጌሙን መክፈትና መጫዎት ትችላላችሁ።🙏🙏🙏

ሌሎች ጠቃሚ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናሉን share ማድረግ እንዳይረሱ።

@ethiotecchtalk
@ethiotecchtalk


አንዳንድ ዌብሳይቶች vpn ስትጠቀሙ block እያደረጒችሁ ተቸግራችኋል???👇👇

👉  አንዳንድ ዌብሳይቶች ኢትዮጵያ ውስጥ ካለ vpn አይሰሩም። ታድያ እነዚህን ዌብሳይቶች ለመጠቀም shared vpn አብርታችሁ አንድ ወይም ሁለት ጊዜ ከተጠቀማችሁ በኋላ አካውንታችሁ block ይደረጋል። ምክናየቱ ደግሞ shared vpn connect ባደረጋችሁ ቁጥር ip address እና location ስለሚቀይር ነው።

🔎🔎🔎 ታድያ መፍትሔው ምንድን ነው???

1⃣ የመጀመሪያው መፍትሔ shared vpn ካበራችሁ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ  ዌብሳይቶቹ ላይ ስትገቡ እና አካውንት ስትከፍቱ ከ ቪፒኤኑ ላይ ip address እና location በጥንቃቄ መዝግባችሁ መያዝ እና በቀጣይ login ለማድረግ vpn ስታበሩ አድስ ያገኛችሁት ip address እና location ከመዘገባችሁት ጋር ተመሳሳይ መሆኑን አረጋግጣችሁ login ማድረግ።

2⃣ ሁለተኛው መፍትሔ shared vpn ከመጠቀም ይልቅ dedicated ip vpn መጠቀም ነው። ይህ መፍትሔ አስተማማኝ ነው። ምክናየቱ ደግሞ አንድ ጊዜ ip address እና location መርጣችሁ ካስተካከላችሁ በኋላ እናንተው ካልቀየራችሁት አይቀየርም። dedicated ip ቪፒኤኖችን እንዴ NordVPN እና CyberGhost አይነት ቪፒኤኖችን ካወረዳችሁ በኋላ pro ስለሆነ በትንሽ  $ ገዝታችሁ መጠቀም ትችላላችሁ።

ሌሎች ጠቃሚ መረጃዎችን ለማግኘት ቻናሉን share ማድረግዎን እንዳይረሱ🙏🙏🙏

@ethiotecchtalk
@ethiotecchtalk

Показано 8 последних публикаций.

96

подписчиков
Статистика канала