"የአክሱም ከተማ ሙስሊም ነዋሪዎች ችግር እልባት ያልተሰጠበት እና ወደባሰ ሁኔታ እየሄደ ነው"--- የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የአክሱም ከተማ ሙስሊም ነዋሪዎች ለዘመናት የነበረባቸውን የእምነት ነፃነት፣ የመስገጃ ቦታ ችግር እና የቀብር ቦታ ችግር እልባት ያልተሰጠበት እና ወደባሰ ሁኔታ እየሄደ ነው አለ።
ምክር ቤቱ ዛሬ መግለጫውን ያወጣው በከተማው የሚገኙ ሴት ተማሪዎች ሂጃባቸውን አድርገው ትምህርት መከታተል እንዳልቻሉ ከሰሞኑ መሰማቱን ተከትሎ ነው።
"በዚህ ዘመን በጋራ እምነቶች ተከባብረው በሚኖሩበት አገር እሴቱን የሚሸረሽር ተግባር መፈፀሙን በፅኑ እናወግዛለን" ያለው ምክር ቤቱ የሙስሊሙ ማህበረሰብ መብቶች ሳይሸራረፉ ተግባራዊ እንዲደረጉ እና መንግስትም ይህን እንዲያስፈፅም ጥያቄ አቅርቧል።
የትግራይ ትምህርት ቢሮ በበኩሉ አዲስ የወጣ የአለባበስ መመርያም ሆነ ማስፈፀሚያ ደንብ እንዳልወጣ የጠቀሰበት ደብዳቤ ማውጣቱን ተመልክተናል።
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
https://t.me/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L