በብዛት ኢትዮጵያን የሚኖሩባት የካሊፎርንያ (ሎስ አንጀለስ) ግዛት ከቁጥጥር ውጪ የሆነ ሰደድ እሳት ተከስቷል
ካሊፎርንያ ለእሳት አደጋ አዲስ አይደለችም። የእስካሁኑ በአብዛኛው ከከተማ ወጣ ብሎ የሚከሰት ነው። ከዚህ ቀደም ሆኖ በማያውቅ ሁኔታ ከፍተኛ የሆነውና፣ ከጫካው ይልቅ የከተማ መሰረተ ልማቶችና መኖርያ አካባቢወችን ያጠቃው የካሊፎርኒያ ሰድድ እሳት እስካሁን ከቁጥጥር ውጪ እንደሆነ ነው። ይሄው ሰደድ እሳት ደቡብ ካሊፎርኒያ፣ በተለይ በርካታ ኢትዮጵያውያን በሚኖሩባት የሎስ አንጀለስ ከተማ አካባቢ ላይ ነው የተከሰተው።
እስካሁን ድረስ ከ105 ስኴር ኪሎሜትር (ከ11 ሺህ ሄክታር) በላይ አካባቢወች እየነደዱ ነው። እስካሁን አምስት ሰው ሞቷል፣ ከ70 ሺህ በላይ ነዋሪወች አካባቢወን ለቀው ወጥተዋል፣ ከ1.6 ሚሊዮን በላይ ቤቶች የኤክትሪክ ሃይል አቅርቦት አጥተዋል፣ ከ1000 በላይ ቤቶች፣ ህንጻወችና መሰረተ ልማቶችም ወድመዋል።
ይሄው ሰደድ እሳት ከፍተኛ ሃይል ባለው አውሎ ነፋስና በአካባቢው ከፍተኛ ድርቅ እየታገዘ እየተስፋፋ ነው። በዚህም ሳብያ 157 ሺህ የአካባቢው ነዋሪወች ባስቸኳይ አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ታዘዋል። በርካታ ሰወች በታዘዙበት ወቅት ወድያው ከአካባቢው ለቀው ባለመውጣታቸው ጉዳት እየደረሰባቸው ነው። በዚህም ሳብያ የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ተገልጿል። ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አካባቢውን ከፍተኛ የአደጋ አካባቢ በማለት አውጀው ከፌደራል መንግስት አስቸኳይ የእሳት አደጋ መከላከልና የእርዳት ድጋፍ እንዲሰጥ አዘዋል።
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
https://t.me/ethiotube