የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቅርቡ ከዚህ አለም በሞት ለተለዩት ለቀድሞው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ለካፒቴን መሐመድ አህመድ ቤተሰቦቻቸው፣ የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚዎች ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው፣ የማኔጅመንት አባላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የመታሰቢያ መርሓ ግብር ያካሄደ ሲሆን በአየር መንገዱ ቅጥር ግቢም የመታሰቢያ ሀውልት ቆሞላቸዋል።
ካፒቴን መሀመድ አህመድ በአቪዬሽኑ መስክ ግንባር ቀደም ከሚባሉት አመራሮች አንዱ ሲሆኑ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ሁለንተናዊ ዕድገት ያኖሩት የማይተካ አሻራ በመጪው ትውልድም ሁልግዜ ሲታወስ ይኖራል።
ካፒቴን መሀመድ አህመድ ከኢትዮጵያ አልፈው የአፍሪካ አየር መንገዶች ህብረት ን ለአስር አመታት በመምራት በአፍሪካ አየር መንገዶች መካከል የጠበቀ ግንኙነት እንዲፈጠርና ለአህጉሪቱ የአቪዬሽን ኢንደስትሪ ዕድገት በጋራ የመስራት መንፈስ እንዲጎለብት ትልቅ ሚና ተጫውተዋል። በአለም ዓቀፍ የአየር ትራንስፖርት ማህበር በአመራር ኮሚቴዎች ውስጥ በነበራቸው ሚና የአፍሪካ አየር መንገዶች በአለም መድረክ አድገውና ጎልብተው በአለም መድረክ ላይ እንዲወጡ ከፍተኛ አስተዋፅዖ አድርገዋል።
ካፒቴን መሀመድ የኢትዮጵያ አየር መንገድን በዋና ስራ አስፈፃሚነት በመሩባቸው ዓመታት አየር መንገዱ ዛሬ ለደረሰበት እድገት እና ስኬት ባበረከቱት የላቀ አስተዋፅዖ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አመራር ቦርድ፣ ማኔጅመንት እና ሰራተኞች ምን ጊዜም ያስታውሷቸዋል።
#የኢትዮጵያአየርመንገድ