ሶማሊያ የኢትዮጵያን ኤምባሲ ከፕሬዝዳንቱ ቅጥር ግቢ ልታስወጣ መሆኑን ገለጸች
የሶማሊያ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አህመድ ሞአሊም ፊቂ በአሁኑ ወቅት በፕሬዝዳንቱ ቤተ መንግሥት ውስጥ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ወደ ሌላ ባዶ ቦታ ለማዘዋወር መታቀዱን አስታውቀዋል።
ሚኒስትሩ ትናንት ጥቅምት 24 ቀን 2017 ዓ.ም ለሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ "ውሳኔው የተወሰነው በፕሬዝዳንቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ የውጭ ሀገር ኤምባሲ መገኘቱ፤ ከፍተኛ ሕዝባዊ ተቃውሞ ማስነሳቱን ተከትሎ ነው" ብለዋል።
"የሶማሊያ ሕዝብ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የሚገኝበት ቦታ ላይ ያቀረቡት ቅሬታ ተገቢ ነው።" ያሉት ሚኒስትሩ፤ "በቅርብ ጊዜ ውስጥ ከፕሬዝዳንቱ ቤተ መንግሥት ውጭ ወደሚገኝ አዲስ ቦታ እንዲዛወር ለማድረግ ፈጣን እርምጃ እንወስዳለን" ሲሉ ተናግረዋል።
አክለውም "ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ኤምባሲ ይገኝበት የነበረው አከባቢ በአሁኑ ሰአት ምንም አይነት ጥቅም እየሰጠ አይደለም፤ እሱን አድሰን ኤምባሲው ወደዚያው እንዲዛወር እናደርጋለን" ብለዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ይህ ካልሆነ ግን በተመሳሳይ "በአዲሰ አበባ የሚገኘውን የሶማሊያ ኤምባሲ በኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ግቢ ውስጥ እንዲሆን የሚል ጥያቄ እናቀርባለን" በማለት ተናግረዋል።
ይህ እርምጃ በፕሬዝዳንት አብዱላሂ ዩሱፍ አህመድ መንግሥት ፍቃድ ተሰጥቶታልም ተብሏል።
ይህ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ መግለጫ ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር የመግባቢያ ስምምነትን መፈራረሟን ተከትሎ፤ በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል እየተካረረ የመጣውን ልዩነት የሚያንጸባርቅ መሆኑ ተዘግቧል።
Via Ahadu
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
https://t.me/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L