የኮይሻ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የግንባታ ጥራት በጥብቅ ቁጥጥር እየተመራ ይገኛል
************
(ኢ ፕ ድ)
የኮይሻ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የግንባታ ጥራት ከግብዓት አቅርቦት እስከ ሥራው ሂደት በጥብቅ ቁጥጥር እየተመራ መሆኑ ተገለጸ፡፡
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮይሻ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የሲቪል ሥራዎች ቡድን መሪ ኢንጂነር እሸቱ ወርቁ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የኮይሻ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት የግንባታ ጥራት ከግብዓት አቅርቦት እስከ ሥራው ሂደት ድረስ፤ በግንባታው ላይ የየራሳቸው የሥራ ድርሻ ባላቸው ሦስቱም ባለድርሻ አካላት በጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር እየተመራ ነው፡፡
በሥራ ተቋራጩ “ዊ ቢውለድ”፣ በሥራው ባለቤት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልና በአማካሪው “ስታንቴክ” በኩል የግንባታው የጥራት ደረጃ በተቀመጠው መመዘኛ መሠረት መሠራቱን የመከታተል፣ የመቆጣጠርና የማረጋገጥ ሥራ በመናበብ ይሠራል ብለዋል።
ሦስቱም ባለድርሻ አካላት የግድቡን የጥራት ደረጃ ከማረጋገጥ አንጻር እንደ ተሰጣቸው ኃላፊነት 24 ሰዓት ጥብቅ ክትትል ያደርጋሉ ሲሉ አስረድተዋል፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በይበልጥም የግንባታውን የጥራት ደረጃ የማረጋገጥ ኃላፊነት እንዳለው የተናገሩት ኢንጂነር እሸቱ፤ የግድቡን ሙሌትና የኃይል ማመንጫ ግንባታ 24 ሰዓት እየተከታተለ በጥራት........
ሙሉውን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://press.et/?p=125929