በአምስት ወራት ከወርቅ ወጪ ንግድ ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ
******
(ኢ ፕ ድ)
በ2017 በጀት ዓመት አምስት ወራት ከወርቅ ወጪ ንግድ ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ተናገሩ።
መደበኛውን ነጋዴ መደገፍና ማበረታታት የሚያስፈልገውን ያህል በሕገወጥና ኮንትሮባንድ ንግድ ላይ የሚሳተፍ ነጋዴ እንዳይኖር በየዕለቱ ክትትልና ቁጥጥር እየተደረገ ነው።
በሕገወጥና በኮንትሮባንድ ንግድ ላይ የሚደረገው የቁጥጥር ስራም ተጨባጭ ውጤት እያስገኘ መሆኑን አስታውቀዋል።
የወርቅ ወጪ ንግድን ለአብነት ያነሱት ሚኒስትሩ፣ ባለፈው በሙሉ ዓመት ከወርቅ ወጪ ንግድ የተገኘው ገቢ 350 ሚሊዮን ዶላር መሆኑን ተናግረዋል።
በተያዘው በጀት ዓመት አምስት ወራት ከወርቅ ወጪ ንግድ ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን አመላክተዋል።
ይህ ውጤት ሊገኝ የቻለው በፖሊሲ በመመራት የንግድ ስርዓቱን ማስተዳደር በመቻሉ በመሆኑ በቀጣይም ይበልጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስገንዘበዋል።
በሄለን ወንድምነው
ታህሳስ 22 ቀን 2017 ዓም