የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ጉባዔ የአስተዳደሩ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ሃላፊ የነበሩትን ሂክማ ኬይረዲንን የከተማዋ ዋና ሥራ አስኪያጅ አድርጎ ሹሟል።
ምክር ቤቱ፣ ሂክማን በዋና ሥራ አስኪያጅነት የሾመው፣ ጥራቱ በየነን ከሥልጣናቸው በማንሳት ነው። ጃንጥራር አባይ፣ የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሃካፊነትን ብቻ በመያዝ በምክትል ከንቲባነት ሥልጣናቸው ቀጥለዋል።
ምክር ቤቱ በተጨማሪም፣ ሲሳይ ጌታቸውን የመሬት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ እንዲኹም ጽጌወይኒ ካሳን የቤቶች ልማት ቢሮ ኃላፊ አድርጎ ሹሟል።
ዛሬ በተካሄደው የካቢኔ ሽግሽግ በጠቅላላው 10 የካቢኔ ሹመቶች ተሰጥተዋል።