etv zena


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


For any comment @etv_zena_57_bot

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


ለመጀመሪያ መቶ ሰዎች የ5 ብር ካርድ አለው so please subscribe




በአማራ ክልል የተጣለው የኢንተርኔት እገዳ በአስቸኳይ እንዲነሳ ሲሉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ተቆርቋሪዎች ጠየቁ!!

ጥያቄውን ያቀረቡት ከ150 ሃገራት የተውጣጡ ወደ 300 የሚሆኑ ለሰብአዊ መብቶች መከበር የሚሟገቱ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ናቸው። የእገዳ ተግባሩ ከሌሎች የአፍሪቃ ሃገራት በኢትዮጵያ የከፋ መሆኑ ተገልጿል። እገዳውን በማውገዝም (Access Now) እና (#KeepItOn coalition) የተባሉ ሁለት ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ግልጽ ደብዳቤ ከጻፉ ወራት ተቆጥረዋል። የኢንተርኔት እገዳው ግን እንደቀጠለ ነው ።  

«…በአማራ ክልል ላይ የተጣለውን የኢንተርኔት እገዳ ያለአንዳች ማንገራገር፣ መስመሮቹን በአስቸኳይ እንዲከፍቱ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን አህመድን እንጠይቃለን፡፡ የአፍሪካ ሕብረት ድርጅትም መሠረታዊ የሆኑ ሰበኣዊ መብቶችም በኢትዮጵያ ውስጥ እንዲከበሩና በሥራ ላይ እንዲውሉም ፣ጋዜጠኞችም ሥራቸውን አለ.አንዳች ቁጥጥር ተዘዋውረው እንዲሠሩ፣ ድርጅቱም ጣልቃ ገብቶ -በቻርተሩ ውል መሠረት- ተጽዕኖ እዚያ እንዲያደርግ እኛ እንጠይቃለን፡፡» ይህን ያሉት የኤሲሲኢኤሰ ናው በምጻሩ - ACCESS NOW የተባል ድርጅት ተጠሪ ወይዘሮ ፊሊሲያ አንቶኒዮ ናቸው፡፡

ከ150 አገራት የተወጣጡ፣ወደ 300 የሚጠጉ ለሰበኣዊ መብት መከበር የሚሟገቱ የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተሰባስበው በቅርቡ ያወጡት የጋራ መግለጫ፣ ከሓምሌ ወር ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ በኢትዮጵያ - በአማራ ክልል የኢንተርኔት መስመሮች እዚያ እንደተዘጉ ጽሑፉ መለስ ብሎ በሰነዱ ላይ ያስታውሳል፡፡ በብዙ የሚቆጠሩ ሰዎች እዚያ እንደሞቱ፣ከአንድ ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ በጅምላ ታፍሰው እንደ ታሰሩ - የተባበሩት መንግሥታትን ሰነድ - ማሥረጃ አድርጎ የወጣው መግለጫ የኢትዮጵያን መንግሥት ከሷል፡፡


መንግስት የሴት ተማሪዎች ወሊድ ፈቃድ ረቂቅ መመሪያን እንዲሰርዝ ተጠየቀ፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር የአጠቃላይ ትምህርት ተማሪዎች ምዘናና የክፍል ዝውውር ረቂቅ መመርያ ማዘጋጀቱ ተገልጿል፡፡ ሪፖርተር ጋዜጣ ከአንድ ሳምንት በፊት ባወጣው ዘገባ የአጠቃላይ ትምህርት ተማሪ ከ15 ቀናት በላይ በወሊድ ምክንያት ከትምህርቷ የምትቀር ከሆነ በዚያው የትምህርት ዘመን ትምህርቷን መቀጠል እንደማትችል የሚደነግግ ረቂቅ መመሪያ በትምህርት ሚኒስቴር መዘጋጀቱን ገልጿል፡፡

በዚህ ረቂቅ መመሪያ መሰረትም ተማሪዋ ለ15 ተከታታይ ቀናት በወሊድ ምክንያት የምታርፍ ከሆነ ትምህርቷን መቀጠል አትችልም፡፡ ተማሪዋ ለ16 ቀናትና ከዚያ በላይ ለሆኑ ቀናት የምትቀር ከሆነ በዚያ ዓመት ስትከታተል ከነበረው ትምህርት የምትታገድ መሆኑን ያስረዳል፡፡ ሆኖም ተማሪዋ በቀጣዩ ዓመት ትምህርቷን መቀጠል የምትፈልግ ከሆነ፣ ‹‹ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ›› መቀጠል እንደምትችል ይፈቅዳል ሲል በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡

የኢትዮጵያ የሕግ ባለሙያ ሴቶች ማኅበር ይህን ረቂቅ መመሪያ የተቃወመ ሲሆን መመሪያው ትምህርታቸውን ለሚከታተሉ ሴቶች የወሊድ ፈቃድ መብትን በእጅጉ የሚገድብ እንደሆነ ገልጿል፡፡ ይህ ረቂቅ ሕግ በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት የተደነገጉትን አወንታዊ የድርጊት ድንጋጌዎች የሚንድ ብቻ ሳይሆን የሴቶችን መሠረታዊ የመማር መብቶችም በግልጽ የሚነፍግ ስለሆነ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አቋሙን እንደገና እንዲያጤነው ሲል ጠይቋል፡፡


    


በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ የሚጠይቅ ደብዳቤ ለከንቲባ ጽ/ቤት ማስገባቱን የኢትዮጰያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ ገለጸ፡፡

"ጦርነት ይቁም! ሠላም ይስፈን፣ መከላከያ ሰራዊቱ ባስቸኳይ ወደ ካምፕ ይግባ!" በሚል መሪ ቃል ለህዳር 30 ፣ 2016 ዓ. ም. ታላቅ ህዝባዊ ሠልፍ ለማድረግ ነው ፓርቲው ጥያቄ ያቀረበው፡፡

በዛሬው እለት ህዳር 19 ቀን 2016 ዓ.ም. በሰላማዊ ሰልፉ አስተባባሪዎች በተፈረመ ደብዳቤ፣ ጦርነት እንዲቆም፣ መከላከያ ሠራዊቱ ከዘመተባቸው ክልሎች ወጥቶ ወደ ጦር ካምፑ እንዲመለስና ፖለቲካዊ ውይይቶች እንዲከፈቱ የሚጠይቅ ህዝባዊ የአደባባይ ሠልፍ ለማድረግ እንደሆነ ተሰምቷል፡፡ የኢትዮጰያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ /ኢህአፓ/ እና ሌሎች ዜጎች አስተባባሪነት የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ዙሪያ ዛሬ ለአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት፣ የማሣወቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸውን ለጣብያችን ገልፀዋል፡፡

ከጣብያችን ጋር ቆይታ የነበራቸው የኢህአፓ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር መጋቢ ብሉይ አብርሃም እንደገለፁት ኢህአፓ እና ሌሎች ሁሉን አቀፍ ሀገር ወዳድ አባላት በመሰባሰብ በጋራ በመሆን ሀገርን የማዳን ሰልፍ መጠራቱን ነግረውናል፡፡ ህዝባዊ ሠልፉ መነሻውን አራት ኪሎ የድላችን ኃውልት አድርጎ በተለያዩ ጎዳናዎችንና አደባባዮችን በማለፍ መዳረሻውን መስቀል አደባባይ አድርጎ የዕለቱን መልዕክት በማስተላለፍ ይጠናቀቃልም ተብሏል። በሠላማዊ ሠልፉ ላይም ከመቶ ሺህ ሰው በላይ  እንደሚጠበቅ የገለፁት አስተባባሪዎቹ፣ ለዚህ የሚሆን የፀጥታና ደህንነት የአዲስ አበባ ፖሊስ ህገ-መንግስታዊ ተልዕኮውን እንዲወጣ ጠይቀዋል፡፡

ሠልፉ በተለይም በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች የጦር ሠራዊቱ ከጦርነት አውድ ውጪ የሚፈፅማቸውን ዘመቻዎችን በማቆም ወደ ጦር ሰፈሩ እንደሚለስ የሚጠይቅ መሆኑንም አስተባባሪዎቹ ለጣብያችን ተናገግረዋል፡፡

ሰላማዊ ሰልፉን ከጠሩት አስተባባሪዎች መካከልም እንደ ናትናኤል መኮንን፣የሺዋስ አሰፋ የመሣሠሉ ፖሊቲከኞችና ሌሎችም ሀገር ወዳዶች የተጠራ ነው መባሉን  ያገኘነው መረጃ ያለመክታል፡፡


በመከላከያ ሠራዊት ተሽከርካሪ ሲጓዙ የነበሩ 53 ኤርትራውያን ስደተኞች በደቡብ ኢትዮጵያ ተያዙ

በመከላከያ ሠራዊት ተሽከርካሪ ተጭነው ወደ ኬንያ ሲጓዙ የነበሩ 53 ሕገ-ወጥ ኤርትራውያን ስደተኞችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኧሌ ዞን አስታወቀ።

ሕገ-ወጥ ስደተኞቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት ከትላንት በስቲያ እሁድ ኅዳር 16/2016 ዓ.ም. ምሽት እንደሆነ የዞኑ ሰላም እና የፀጥታ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አምሳሉ አንጋቶም ለቢቢሲ ተናግረዋል። እንደ ኃላፊው ገለጻ በደላሎች አማካኝነት ተሰባስበው ጉዞ የጀመሩት ኤርትራውያኑ አዲስ አበባን ጨምሮ ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች መነሻቸውን ያደረጉ ናቸው።

ከተጓዦቹ መካከል ሴቶችም ያሉበት ሲሆን ስድስት ሕጻናትም መኖራቸውን የገለጹት አቶ አምሳሉ፤ ከእነዚህም ውስጥ በወራት የሚቆጠር ዕድሜ ያላቸው እና ጡት የሚጠቡ ሕጻናት ጭምር እንደሚገኙ አስረድተዋል።

ስደተኞቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት ኧሌ እና ኮንሶ ዞኖች እንዲሁም በና ጸማይ ወረዳን በሚያዋስ አካባቢ ላይ ሲደርሱ መሆኑን አንድ የአካባቢው ምንጭ ለቢቢሲ ገልጸዋል። በወቅቱ ፓስፖርትን ጨምሮ ሌሎች ሕጋዊ ሰነዶችን እንዲያሳዩ የተጠየቁት ስደተኞቹ ይህንን ማድረግ አለመቻላቸውን እኚሁ ምንጭ ተናግረዋል።
የሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ኃላፊው አቶ አምሳሉ በበኩላቸው ስደተኞቹ የተያዙት በአካባቢው የነበሩ የፖሊስ አባላት በጥርጣሬ መኪናውን ካስቆሙ በኋላ መሆኑን አስረድተዋል።

ኤርትራውያኑ የተጫኑት በመከላከያ ሠራዊት “ኦራል” ተሽከርካሪ እንደነበር የገለጹት አቶ አምሳሉ፤ “እነዚህን ያመጣው ደላላ ነው። ደላላው እስከ መከላከያ ሠራዊት ድረስ ገብቶ ጥርጣሬ እንዳይኖር በዚያ መኪና እንዲጫኑ ተደርጓል” ሲሉ ስደተኞቹ በዚህ መኪና እንዲጓዙ ምክንያት ሆኗል ያሉትን ጉዳይ ጠቅሰዋል።

 


የፈረንሳይ ኦሬንጅ ኩባንያ የኢትዮ ቴሌኮምን ድርሻ ከመግዛት ሂደት ራሱን አገለለ!!

የፈረንሳይ ኦሬንጅ ኩባንያ የኢትዮ ቴሌኮምን 45 በመቶ ድርሻ ከመግዛት ሂደት ራሱን ማግለሉን አስታወቀ!

የኢትዮጵያ ፋይናንስ ሚንስቴር የኢትዮ ቴሌኮምን የ45 በመቶ ድርሻ ለመሸጥ ዓለም አቀፍ ጨረታ ማውጣቱ ይታወሳል። ይህንን ተከትሎም የፈረንሳዩ ኦሬንጅ እና የተባበሩት አረብ ኢምሬት ቴሌኮም ኩባንያ የሆነው ኢ ኤንድ የተሰኘው ተቋም የኢትዮ ቴሌኮምን የ45 በመቶ ድርሻ ለመግዛት የመወዳደር ፍላጎት እንዳላቸው አሳውቀው ነበር።

የፈረንሳይ ኦሬንጅ ኩባንያ በትናንትናው እለት ባወጣው መግለጫ የኢትዮ ቴሌኮምን 45 በመቶ ድርሻ ከመግዛት ሂደት ራሱን ለማግለል መወሰኑን ሬውተርስ ዘግቧል። ኦሬንጅ ከጨረታ ሂደቱ ራሱን ለማግለል የወሰነው ስትራቴጂውን በፍጥነት ለመተግበር አስቻይ ሁኔታ እንደሌል መረዳቱን ተከትሎ እንደሆነም አስታውቋል።

የጨረታ ሂደቱን በበላይነት የሚመሩት ኢትዮ ቴሌኮምና የኢትዮጵያ ፋይናንስ ሚኒስቴር በጉዳዩ ላይ እስካን ማብራሪያ አልሰጡም።ኢትዮ ቴሌኮም በፈረንጆቹ በ2018 የመንግስት ልማት ድርጅቶችን በከፊል ወደ ግል ይዞታ ለማዞር በተያዘው እቅድ ውስጥ ከተካተቱ ድርጅቶች አንዱ ነው። ኢትዮጵያ ሙሉ ለሙሉ የመንግስት ድርሻ የሆነው ኢትዮ ቴሌኮምን ለመሸጥ ከወሰነች የቆየች ቢሆንም በሰሜን የሀገሪቱ ክፍል የተከሰተው ጦርነት እንዳዘገየውም ይታወቃል።

    



አሳዛኝ🕯
በኦሮሚያ ክልል በደረሰ በትራፊክ አደጋ የ 20 ሰዎች
ህይወት አለፈ።

በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ተልታሌ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ20 ሰዎች ሕይወት አለፈ።

በአደጋው ከሟቾች በተጨማሪ በ18 ሰዎች ላይ ከባድ እንዲሁም በ14 ሰዎች ላይ ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱን የዞኑ ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታውቋል። አደጋው የደረሰው የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ከሚላሚ ከተማ ወደ ዋዩ ሲጓዝ መንገድ ስቶ በመገልበጡ ምክንያት ሲሆን በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው በተልታሌና ወላይታ ሆስፒታሎች የህክምና እርዳታ እንዲያገኙ ተልከዋል ተብሏል።


Репост из: Неизвестно
brand እና quality የሆኑ ሰአቶችን , ሽቶዎች , smart watches ,የስጦታ package , እና ሌሎች እቃዎችን በርካሽ ዋጋ ለማግኘት ከታች ያለዉን button ነክታቹ join belu


በቻይና መዲና ቤጂንግ እና ላዮኒንግ በተሰኘችው ግዛት የተቀሰቀሰው አዲስ ወረርሽኝ አሳሳቢ ሆኗል።

ህጻናትን የሚያጠቃው “የሳንባ ምች መሰል ወረርሽኝ” ሆስፒታሎችን ማጨናነቅ ከጀመረ ዋል አደር ብሏል።ከቤጂንግ በ804 ኪሎሜትሮች ርቃ በምትገኘው ላዮኒንግ ትምህርት ቤቶች ለመዘጋት ተቃርበዋልም ነው የተባለው።ምንነቱ እስካሁን ባልተለየው በሽታ የተያዙ ህጻናት ከፍተኛ ትኩሳት ቢኖራቸውም የጉንፋን ምልክት አልታየባቸውም፤ ከመተንፈሻ አካላት ጋር የተያያዙ በሽታዎች ምልክቶችም የላቸውም ተብሏል።

የኮቪድ 19 ቫይረስ በውሃን እንደተከሰተ የቻይና ብሎም የአለም ስጋት ይሆናል የሚል ስጋቱን አስቀድሞ የገለጸው “ፕሮሜድ” የተሰኘው የበሽታ ቅኝት ስርአት አዲሱን የቻይና ወረርሽኝ በስጋትነት ጠቅሶታል።የአለም ጤና ድርጅትም በኮቪድ ወረርሽኝ ወቅት ይደረጉ የነበሩ ጥንቃቄዎች ተፈጻሚ እንዲሆኑ አሳስቧል።የፊት መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ፣ የህመሙ ምልክት ካለባቸው ሰዎች መራቅ እና የታመሙ ሰዎችም ከቤታቸው እንዳይወጡ የሚል ማሳሰቢያውንም በድረገጹ ላይ አስፍሯል።ሰዎች ከሚሰበሰቡባቸው ስፍራዎች እንዲርቁና ከቻሉ ከቤታቸው እንዳይወጡም ነው ያሳሰበው።

“ማይኮፕላዝማ ኒሞኒያ” በተሰኘው ባክቴሪያ ምክንያት ሊከሰት እንደሚችል የተገመተው አዲሱ በሽታ ሳንባን ክፉኛ እንደሚጎዳ ተገልጿል።“ፕሮሜድ” ህጻናትን እያጠቃ ያለው “የሳንባ ምች መሳይ በሽታ” መቼ መስፋፋት ጀምሮ ወደ ወረርሽኝነት እንደሚለወጥ ባይገልጽም ህጻናትን በፍጥነት ማዳረሱ አሳሳቢ ሆኗል።የአለም ጤና ድርጅትም ቻይና የበሽተኞቹን መረጃ፣ የስርጭት መጠኑን እንዲሁም በሆስፒታሎች ላይ የፈጠረውን ጫና በተመለከተ ዝርዝር መረጃ እንድታጋራው ጠይቋል።

    


በ2012 ዓ.ም. የወጣው የኤክሳይስ ታክስ ተግባራዊ በሚደረግበት ወቅት ውዝግብ አስነስተው ከነበሩት 297 ተሽከርካሪዎች ውስጥ አብዛኞቹ በጉምሩክ ኮሚሽን እንደገና ለጨረታ በመቅረባቸው፣ በተሽከርካሪዎቹ ባለቤቶች ላይ ቅሬታ መፍጠሩን ሪፖርተር ዘግቧል።

አዋጁ ከመፅደቁ በፊት የባንክ ፈቃድ አውጥተው የማስመጣት ሒደት ጀምረው ለነበሩት የስድስት ወራት ጊዜ ሰጥቶ የማስመጣት ሒደቱን እንዲጨርሱ ደንግጎ ነበር፡፡ በየካቲት ወር 2012 ዓ.ም. ተግባራዊ የሆነው የኤክሳይስ ታክስ ባገለገሉ ተሽከርካሪዎች ላይ ከፍተኛ ታክስ የሚጥል ሲሆን መሆኑ ይታወሳል።

ነሐሴ 5 ቀን 2012 ዓ.ም. የስድስት ወራቱ የጊዜ ገደብ ሲጠናቀቅ በቀናት ልዩነት ወደ አገር ውስጥ የገቡት ተሽከርካሪዎች ጉዳይ ለሦስት ዓመታት ውዝግብ ፈጥሮ ቆይቷል፡፡

    


ተጨማሪ 67 የከተማ አውቶቢሶች ወደ ስራ ገቡ!

የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር የብዙሃን ትራንስፖርት አቅርቦት ለማሻሻል በሚም ተጨማሪ 67 የከተማ አውቶቢሶችን ወደ ስራ ማስገባቱን አስታዉቋል።

ተሽከርካሪዎቹ በአለም ባንክ ድጋፍ የተገዙ መሆናቸዉን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል።

ከንቲባዋ አሁን ወደ ስምሪት የገቡትን ጨምሮ ከዓለም ባንክ በተገኘ ድጋፍ 177 ፣ በከተማው በጀት 200 በጠቅላላዉ 377 አዳዲስና ዘመናዊ የከተማ አውቶቢሶችን ገዝተን ወደ ስራ አስገብተናል ማለታቸዉን ተሰምቷል። ከንቲባዋ አያይዘዉም የዓለም ባንክ ላደረገዉ ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። አዉቶብሶቹ የተገዙበት ዋጋ ግን በከተማ መስተዳድሩ አልተገለጸም።


እንደነዚ አይነት የሚያምምሩ ሰአቶችን ስላስመጣን
የመግዛት ፍላጎት ያላቹ ሰዎች በ 0996988120 እየደወሉ ይጠይቁን አዲስ አበባ ላላቹ ባላቹበት እናደርሳለንወይም ደሞ ሱቃችን መጥታቹ መውሰድ ትችላ

‼️‼️ሌሎች ብራንዶችም ስላሉን ደውላቹ ጠይቁን

‼️በተጨማሪም ብራንድ እና quality ሽቶ ምትፈልጉ ደውላቹ አናግሩኝ እቃዎቻችን 100% ኦርጅናል ናቸው


New arrival
For men

quality ሽቶ በቅናሽ ዋጋ

በ0996988120 ደውሉ


ተጨማሪ 67 የከተማ አውቶቢሶች ወደ ስራ ገቡ

የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር የብዙሃን ትራንስፖርት አቅርቦት ለማሻሻል በሚም ተጨማሪ 67 የከተማ አውቶቢሶችን ወደ ስራ ማስገባቱን አስታዉቋል።

ተሽከርካሪዎቹ በአለም ባንክ ድጋፍ የተገዙ መሆናቸዉን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል።

ከንቲባዋ አሁን ወደ ስምሪት የገቡትን ጨምሮ ከዓለም ባንክ በተገኘ ድጋፍ 177 ፣ በከተማው በጀት 200 በጠቅላላዉ 377 አዳዲስና ዘመናዊ የከተማ አውቶቢሶችን ገዝተን ወደ ስራ አስገብተናል ማለታቸዉን ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ሰምቷል።

ከንቲባዋ አያይዘዉም የዓለም ባንክ ላደረገዉ ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። አዉቶብሶቹ የተገዙበት ዋጋ ግን በከተማ መስተዳድሩ አልተገለጸም።


የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ጉባዔ የአስተዳደሩ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ሃላፊ የነበሩትን ሂክማ ኬይረዲንን የከተማዋ ዋና ሥራ አስኪያጅ አድርጎ ሹሟል።

ምክር ቤቱ፣ ሂክማን በዋና ሥራ አስኪያጅነት የሾመው፣ ጥራቱ በየነን ከሥልጣናቸው በማንሳት ነው። ጃንጥራር አባይ፣ የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሃካፊነትን ብቻ በመያዝ በምክትል ከንቲባነት ሥልጣናቸው ቀጥለዋል።

ምክር ቤቱ በተጨማሪም፣ ሲሳይ ጌታቸውን የመሬት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ እንዲኹም ጽጌወይኒ ካሳን የቤቶች ልማት ቢሮ ኃላፊ አድርጎ ሹሟል።

ዛሬ በተካሄደው የካቢኔ ሽግሽግ በጠቅላላው 10 የካቢኔ ሹመቶች ተሰጥተዋል።


ሞሃ የለስላሳ መጠጦች ኢንዱስትሪ ሙሉ በሙሉ ምርት ሊያቆም መኾነን ከምንጮች ሰምቻለኹ ሲል ሪፖርተር ዘግቧል። ሞሃ፣ ሥራ ለማቆም የተቃረበው በውጭ ምንዛሬ እጥረት እንደኾነና ከስምንት ሺህ በላይ ሠራተኞቹ ሥራ እንዳቆሙ መረዳቱን ዘገባው ጠቅሷል። ፋብሪካው ለረጅም ጊዜ ጠርሙሶችንና መለዋወጫዎችን ጨምሮ የተለያዩ ጥሬ ዕቃዎችን ከውጭ ማስገባት እንዳልቻለና ላንድ ዓመት ያህል ምርት እንዳላመረተ ተገልጧል። የሚድሮክ ኩባንያ ንብረት የኾነውና ከአዲስ አበባ ውጭ አምስት ፋብሪካዎች ያሉት ሞሃ፣ ለበርካታ ዓመታት ፔፕሲ፣ ሚሪንዳ እና 7-አፕ ለስላሳ መጠጦችን በማምረት ይታወቃል።

   


አርሲ ሽርካ🕯🕯

በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ሽርካ(ጎቤሳ) በሚባል ቦታ በትናንትናው እለት ከ20 የሚበልጡ ዜጎች መገደላቸው ተሰማ!

በትናንትናው እለት በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ሽርካ(ጎቤሳ) በሚባል ቦታ በኦነግ ሸኔ ተፈፀመ በተባለው ጥቃት በትንሹ ከ20 የሚበልጡ ዜጎች መገደላቸው ምንጮች ገልፀዋል።

የአከባቢው ነዋሪዎች እንደገለፁት ከሆነ የሟቾች ቁጥር ከዚህም እንደሚበልጥ እና ጥቃቱም በአከባቢው በአሳቻ ሰአት በሚንቀሳቀሰው በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች እንደተፈፀመ የገለፁ ሲሆን ነዋሪዎቹ ከፍተኛ የፀጥታ ስጋት እንዳደረባቸው ገልፀዋል።

የአርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ ዋና ከተማ ጎቤሳ ከአዲስ አበባ 264 ኪ.ሜ ገደማ ርቀት ላይ ስትገኝ፤ ከበቆጂ ከተማ ደግሞ 35 ኪ.ሜ. ትርቃለች። ነዋሪዎቹ ከዚህ ቀደም ታጣቂዎች በአከባቢው እንደሚንቀሳቀሱና መሰል የፀጥታ ስጋትም ሲያዩ እንደነበር ተናግረዋል።(E-M)

   


Репост из: etv zena
🎠 Polo Air mens gift package🎠
♣️ 5 in 1 gift set for #him ♣️

● Polo air Perfume 50 ML
● Polo air Watch
● polo air sunglass
● Card Holder (grey)
● Keychain
With brand box
4500

✅ 21 pc available


contact me at @thewayofnate

Показано 19 последних публикаций.