ተጨማሪ 67 የከተማ አውቶቢሶች ወደ ስራ ገቡ!
የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር የብዙሃን ትራንስፖርት አቅርቦት ለማሻሻል በሚም ተጨማሪ 67 የከተማ አውቶቢሶችን ወደ ስራ ማስገባቱን አስታዉቋል።
ተሽከርካሪዎቹ በአለም ባንክ ድጋፍ የተገዙ መሆናቸዉን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል።
ከንቲባዋ አሁን ወደ ስምሪት የገቡትን ጨምሮ ከዓለም ባንክ በተገኘ ድጋፍ 177 ፣ በከተማው በጀት 200 በጠቅላላዉ 377 አዳዲስና ዘመናዊ የከተማ አውቶቢሶችን ገዝተን ወደ ስራ አስገብተናል ማለታቸዉን ተሰምቷል። ከንቲባዋ አያይዘዉም የዓለም ባንክ ላደረገዉ ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። አዉቶብሶቹ የተገዙበት ዋጋ ግን በከተማ መስተዳድሩ አልተገለጸም።