#ጉዞህን ቀጥል🚶♂️🚶♂️🏃♂️🏃♂️
የቢንቢ ልጅ የመጀመሪያ በረራዋን ስታደርግ ውላ ማታ ላይ ውሎዋን ስትናገር እማ ብታይ ሰዎች ሁሉ ሲያጨበጭቡልኝ፣ #ሲያጨበጭቡልኝ ዋሉ አለች። #ምስኪኗ ቢንቢ አላወቀች ሰዎች ሊያጨበጭቡላት ሳይሆን ሊገድሏት እየሞከሩ እንደሆነ።እንዲሁ አንዳንዴ በልባቸው ውድቀታችንን እየተመኙ ያጨበጨቡልን ሰዎች እያደነቁን መስሎን አሳባቸውን ልንስተው እንችላለን።ነገር ግን እውነታው ሌላ ነው። #አይደለንም እኛ እየሱስ ክርስቶስ እንኳን በዚች ምድር በነበረበት ሰዓት ያጋጠመው ነገር ነበር።"በጌታ ስም የሚመጣ ንጉሥ የተባረከ ነው፤ በሰማይ ሰላም በአርያም ክብር "እያሉ ጨርቃቸውን እያነጠፉለት በውርንጭላ ላይ አስቀምጠውት በክብር እና በሙገሳ ከተቀበሉት በኃላ መልሰው በዛ አፋቸው ይገደል፣ ይሰቀል እያሉ እየተጯጯሁ ወደ ጎልጎታ ተራራ ወስደውታል።
ነገር ግን እሱ ወደ እዚች ምድር የመጣበትን አላማ ጠንቅቆ ስለሚያውቅ የእነሱን ከበባና አጀብታ ከምንም አልቆጠረውም ነበር። #ምክንያቱም የመጣበት አላማ ግቡን መምታት ነበረበትና።ስለዚህም ከእየሱስ ሕይወት ብዙ መማር እንችላለን።
እናም አንባቢዬ ሆይ ለሕይወትህ እጅግ ጠቃሚ የሆነ ነገር ልነግርህ እፈልጋለው። #በዚች ምድር ላይ በምትመላለስበት ሰዓት ትኩረት ማድረግ የሚገባህ በተፈጠርክበት አላማ ላይ ነው እንጂ ሰዎች #በሚያዘንቡልህ ክብርና አድናቆት ላይ አይደለም።የሰዎች ድጋፍ እና ማበረታታት አያስፈልግም እያልኩህ አይደለም። #ነገር ግን የእነሱ ሙገሳ ከግብህ እንዳያስተጓጉልህ እና እንቅፋት ሊሆንብህ እንደማይገባ ላሳውቅህ እንጂ አንዲሁም የእነሱ ትችት፣ማንቋሸሽና ማጥላላት ፍፁም ከመንገድህ ሊያስቀርህ አይገባም። #እንዲያውም እልህና ወኔ በውስጥህ ሊጭርብህ ይገባል።
እነሱ የሚጠሉ እና የሚተቹ ወደው እንዳልሆነም ልትረዳ ይገባል አንተ #እነሱ መሆን የሚፈልጉትን ስለሆንክ እንጂ ጠላታቸው ሆነህ አይደለም ጠላታቸው አንተ ሳትሆን ራዕይህ ነው። #ቢሆንም ግን እመነኝ ማዕበሉ እና ወጀቡ እንዳለፈ ባህር ፀጥ ሲሉ ታያቸዋለ።
#አንድ መዘንጋት የሌለብህ ነገር ቢኖር ደግሞ አሸናፊዎች ትኩረታቸው ማሸነፍ ላይ ነው።ተሸናፊዎች ደግሞ ትኩረታቸው አሸናፊዎች ላይ ነው።ልዩነቱ እዚህ ጋር ነው።ስለዚህ ጉዞህን በፅናት ቀጥል!!!!
ከምታማኝ ቀርቤ ንገሬኝ
@zakiyo