[
❖♥ ከ3 ዓመት የስደት ውጣ ውረድ በኋላ የአምላክ እናት ልጇ አምላካችን ክርስቶስን ይዛ አረጋዊ ዮሴፍና ሰሎሜን አስከትላ ከመዐዲ ወደ ላዕላይ ግብጽ በጀልባ ደግሞ ከካይሮ በስተደቡብ 320 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በላዕላይ ግብጽ በምትገኘው ወደ ደብረ ቊስቋም ገብተው በመንገድ ጒዞ ካገኛቸው ድካም 6 ወር ከ10 ቀናት ዐርፈዋልና ኅዳር 6 በደመቀ መልኩ በዓሏ ይከበራል፡፡
❖ ♥በደብረ ቁስቋም ሳሉ ጨካኙ ሄሮድስ እንደሞተ የጌታ መልአክ በግብፅ ለዮሴፍ በሕልም ታይቶ "የሕፃኑን ነፍስ የፈለጉት ሞተዋልና ተነሣ፥ ሕፃኑን እናቱንም ይዘኽ ወደ እስራኤል አገር ኺድ" ብሎታል (ማቴ 2፡19-20)።
❖ ♥ ይኽቺን ጌታ ከእናቱ ጋር ያረፈባትን የተቀደሰች ቦታን ጌታችን ባርኳት ወደ ናዝሬት ተመልሰዋል። ጌታችን ካረገ ከብዙ ዘመን በኋላ በኅዳር ስድስት ቀን “አስተጋብኦሙ እግዚእነ ለሐዋርያቲሁ ቅዱሳን ውስተ ዝንቱ ደብረ ቊስቋም ወቀደሰ ታቦተ ወቤተ ክርስቲያን ወሠርዐ ቊርባነ ወመጠዎሙ ሥጋሁ ቅዱሰ ወደሞ ክቡረ” ይላል (በዚኽ በደብረ ቊስቋም ቅዱሳን ሐዋርያቱን ሰበሰባቸው ታቦትንና ቤተ ክርስቲያንንም አክብሮ የቊርባን መሥዋዕትንም ሠርቶ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ሰጥቷቸዋል) ይላል፡፡
♥ [“በሊዓ ሕፃናት ሶበ ኀለየ ሄሮድስ አርዌ ሰማይ
ምስለ ዮሴፍ አረጋይ
ነገደት ቊስቋመ ናዛዚተ ሐዘን በብካይ”]
(የሰማዩ አውሬ ሄሮድስ ሕፃናትን መብላት ባሰበ ጊዜ፤ ከሐዘንና ከልቅሶ የምታረጋጋ ማርያም ከአረጋዊዉ ዮሴፍ ጋራ ወደ ቊስቋም ኼደች (ተሰደደች))
❖♥ “አሥረጸት ማርያም አክናፈ ረድኤት አምሳለ ዖፍ ለዐሪገ ቊስቋም
ህየ ከመ ትትዐቀብ ዘመነ ወአዝማነ ወመንፈቀ ዘመን በከመ ይቤ መጽሐፍ”
(ማርያም ወደ ቊስቋም ተራራ ለመውጣት እንደ ዎፍ የረድኤት ክንፎችን አበቀለች በመጽሐፍ እንደተናገረ በዚያ በዘመንና በዘመናት በዘመን እኩሌታም ትጠበቅ ዘንድ)
❖ ♥ “ብጽዐን ለኪ ኦ ደብረ ቊስቋም
እምኲሎን አድያም እምናዝሬት እስከ ቤተልሔም
ዘተጸወነ ላዕሌኪ መድኀኔ ኲሉ ዓለም”
(ከናዝሬት እስከ ቤተ ልሔም ካሉ አውራጆች ኹሉ የዓለም ኹሉ መድኀኒት ወደ አንቺ የተጠጋ የቊስቋም ተራራ ሆይ ክብር ይገባሻል)
❖♥ “በቃለ ውዳሴ ጥዑም ይደሉ ሰላም
ለዕበይኪ ፍጹም አድባረ ቊስቋም
ማኅደረ ልዑል ዘአርያም”
(በአርያም ያለ የልዑል ማደሪያው የኾንሽ የቊስቋም ተራራ ሆይ ፍጹም ለሚኾን ክብርሽ በሚጣፍጥ የምስጋና ቃል ሰላምታ ማቅረብ ይገባል) በማለት ዘርዝሮ ጽፎላታል፡፡
❖♥ ቅዱስ ያሬድም ቅድስት ድንግል ማርያም ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስን ይዛ በስደቷ ወቅት በደብረ ቊስቋም ስለማረፏ በድጓው ላይ ሲጽፍ፡-
❖♥ “መንክር ወመድምም ዘተገብረ በደብረ ቊስቋም
መንክር ወመድምም ዘይሴባሕ በአርያም
አምላክ ፍጹም ኀደረ ውስቴቱ መድኀኔ ዓለም
ዘሀሎ እምቅድም
ኀደረ ውስቴቱ ለዝንቱ ደብር ዘአብ ቃል
ምስለ እሙ ድንግል ደመና ቀሊል”
(በደብረ ቊስቋም የተደረገው የሚያስደንቅ እና የሚያስገርም ነው፤ በአርያም የሚመሰገን ፍጹም የባሕርይ አምላክ መድኀኔ ዓለም በውስጡ ዐደረ፤ ቅድመ ዓለም የነበረ የአብ አካላዊ ቃል ፈጣን ደመና ከተባለች ከድንግል እናቱ ጋር በዚኽ ደብር በውስጡ ዐድሯል) በማለት መስክሮላታል፡፡
❖♥ እኔም ለወንጌል አገልግሎት ወደ ግብጽ ኼጄ በነበረ ጊዜ እመቤታችን ልጇን ይዛ ከስደት ስትመለስ ከአረጋዊ ዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ከድካም ያረፉበት ይኽቺን ቅድስት ቦታ ገዳመ ቁስቋምን ስረግጣትና ጌታችን ከእናቱ ጋ የተቀመጡበት ዋሻ ውስጥ ገብቼ የተቀደሰችውን ቦታ ስስማት መጀመሪያ ያሰብኩት ቅዱሱ አባት አባ ጽጌ ብርሃን በማሕሌተ ጽጌው ላይ፦
”
(ማርያም የግፍሽን ተአምር ለመግለጥ ከጠላት ሄሮድስ ፊት በሸሸሽ ጊዜ ከለመለመች ከልጅሽ እግር ጋር መንገድን በመኼድ የደከሙ እግሮችሽ የቆሙባት ስሟ ቊስቋም የተባለ የተቀደሰች ገዳምሽን እኔም ደርሼ ብሳለማት እመኛለሁ እወዳለሁ) በማለት የጸለያት ጸሎትን ነበር፡፡
♥
@ewuntegna
@ewuntegna
@ewuntegna
የቁስቋም ክብር በኢትዮጵያ ቀደምት ሊቃውንት]
✍በመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ

❖♥ በዚኽ ምክንያት ደብረ ቁስቋምን የእስክንድርያ ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት በግብጽ የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን ይሏታል፤ የግብጽ ኦርቶዶክስ ምእመናን በእጅጉ የሚወዷት የቁስቋም ገዳም ስትኾን በ1993 ዓ.ም. ላይ እመቤታችን በገዳሙ ተገልጣ እንደነበር ይናገራሉ፤ በዚኽችም ገዳም 100 መነኮሳት ይገኙበታል፤ ከቦታዋ ክብር የተነሣ "ዳግሚት ቤተልሔም" ይሏታል፤ በገዳሙም በቅዱሳት መጻሕፍት የተመላ ታላቅ ቤተ መጻሕፍት አለ፨
❖♥ በጌታ በተባረከችው ይኽቺ ቦታ ላይ በ3ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ላይ ቅዱስ ጳኩሚስ ገዳምን የገደመ ሲኾን፤ የእስክንድርያ 23ኛ ፓትርያርክ ቴዎፍሎስ በታናሿ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ምትክ ታላቅ ቤተ ክርስቲያን ለመሥራት ባሰበ ጊዜ እመቤታችን ተገልጻለት የልጇ የክርስቶስ ትሕትናው በገዳሙ እንዲታሰብበት ባለበት እንዲኾን ነግራዋለች።
❖♥ በርካቶች የኢትዮጵያ ሊቃውንት እመቤታችን ከልጇ ጋር ወደ ቊስቋም የመግባቷን ነገር የጻፉ ሲኾን ለምሳሌም አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ በሰዓታት መጽሐፉ ላይ በስፋት ሲዘረዝረው፡-
♥ [“በሊዓ ሕፃናት ሶበ ኀለየ ሄሮድስ አርዌ ሰማይ
ምስለ ዮሴፍ አረጋይ
ነገደት ቊስቋመ ናዛዚተ ሐዘን በብካይ”]
(የሰማዩ አውሬ ሄሮድስ ሕፃናትን መብላት ባሰበ ጊዜ፤ ከሐዘንና ከልቅሶ የምታረጋጋ ማርያም ከአረጋዊዉ ዮሴፍ ጋራ ወደ ቊስቋም ኼደች (ተሰደደች))
❖♥ “አሥረጸት ማርያም አክናፈ ረድኤት አምሳለ ዖፍ ለዐሪገ ቊስቋም
ህየ ከመ ትትዐቀብ ዘመነ ወአዝማነ ወመንፈቀ ዘመን በከመ ይቤ መጽሐፍ”
(ማርያም ወደ ቊስቋም ተራራ ለመውጣት እንደ ዎፍ የረድኤት ክንፎችን አበቀለች በመጽሐፍ እንደተናገረ በዚያ በዘመንና በዘመናት በዘመን እኩሌታም ትጠበቅ ዘንድ)
❖ ♥ “ብጽዐን ለኪ ኦ ደብረ ቊስቋም
እምኲሎን አድያም እምናዝሬት እስከ ቤተልሔም
ዘተጸወነ ላዕሌኪ መድኀኔ ኲሉ ዓለም”
(ከናዝሬት እስከ ቤተ ልሔም ካሉ አውራጆች ኹሉ የዓለም ኹሉ መድኀኒት ወደ አንቺ የተጠጋ የቊስቋም ተራራ ሆይ ክብር ይገባሻል)
❖♥ “በቃለ ውዳሴ ጥዑም ይደሉ ሰላም
ለዕበይኪ ፍጹም አድባረ ቊስቋም
ማኅደረ ልዑል ዘአርያም”
(በአርያም ያለ የልዑል ማደሪያው የኾንሽ የቊስቋም ተራራ ሆይ ፍጹም ለሚኾን ክብርሽ በሚጣፍጥ የምስጋና ቃል ሰላምታ ማቅረብ ይገባል) በማለት ዘርዝሮ ጽፎላታል፡፡
❖♥ ቅዱስ ያሬድም ቅድስት ድንግል ማርያም ልጇ ኢየሱስ ክርስቶስን ይዛ በስደቷ ወቅት በደብረ ቊስቋም ስለማረፏ በድጓው ላይ ሲጽፍ፡-
❖♥ “መንግሥቱ ሰፋኒት ዘእምቅድመ ዓለም
ወልደ ቅድስት ማርያም
ኀሠሠ ምእራፈ ከመ ድኩም
ንጉሥ ዘለዓለም
ግሩም እምግሩማን ብርሃነ ሕይወት ዘኢይጸልም
ኀደረ ደብረ ቊስቋም”
(ቅድመ ዓለም የነበረች ጌትነቱ ምልእት ስፍሕት የኾነች የቅድስት ድንግል ማርያም የባሕርይ ልጅ የዘለዓለም ንጉሥ ሲኾን እንደ ደካማ ማረፊያን ፈለገ፤ ከግሩማን ይልቅ ግሩም፤ የማይጨልም የሕይወት ብርሃን ርሱ በደብረ ቊስቋም ዐደረ)
❖♥ “መንክር ወመድምም ዘተገብረ በደብረ ቊስቋም
መንክር ወመድምም ዘይሴባሕ በአርያም
አምላክ ፍጹም ኀደረ ውስቴቱ መድኀኔ ዓለም
ዘሀሎ እምቅድም
ኀደረ ውስቴቱ ለዝንቱ ደብር ዘአብ ቃል
ምስለ እሙ ድንግል ደመና ቀሊል”
(በደብረ ቊስቋም የተደረገው የሚያስደንቅ እና የሚያስገርም ነው፤ በአርያም የሚመሰገን ፍጹም የባሕርይ አምላክ መድኀኔ ዓለም በውስጡ ዐደረ፤ ቅድመ ዓለም የነበረ የአብ አካላዊ ቃል ፈጣን ደመና ከተባለች ከድንግል እናቱ ጋር በዚኽ ደብር በውስጡ ዐድሯል) በማለት መስክሮላታል፡፡
❖♥ እኔም ለወንጌል አገልግሎት ወደ ግብጽ ኼጄ በነበረ ጊዜ እመቤታችን ልጇን ይዛ ከስደት ስትመለስ ከአረጋዊ ዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ከድካም ያረፉበት ይኽቺን ቅድስት ቦታ ገዳመ ቁስቋምን ስረግጣትና ጌታችን ከእናቱ ጋ የተቀመጡበት ዋሻ ውስጥ ገብቼ የተቀደሰችውን ቦታ ስስማት መጀመሪያ ያሰብኩት ቅዱሱ አባት አባ ጽጌ ብርሃን በማሕሌተ ጽጌው ላይ፦
“ተአምረ ግፍእኪ ለአርእዮ እምገጸ ሄሮድስ መስቴማ
አመ ጐየይኪ ማርያም በሐዊረ ፍኖት እለ ደክማ
ምስለ እግረ ጽጌኪ ልምሉም ኀበ አእጋርኪ ቆማ
ለምድረ ገዳምኪ ቅድስት ቊስቋም ስማ
እምፈተውኩ በጺሕየ በሰጊድ እሰዓማ
”
(ማርያም የግፍሽን ተአምር ለመግለጥ ከጠላት ሄሮድስ ፊት በሸሸሽ ጊዜ ከለመለመች ከልጅሽ እግር ጋር መንገድን በመኼድ የደከሙ እግሮችሽ የቆሙባት ስሟ ቊስቋም የተባለ የተቀደሰች ገዳምሽን እኔም ደርሼ ብሳለማት እመኛለሁ እወዳለሁ) በማለት የጸለያት ጸሎትን ነበር፡፡
♥
የእመቤታችን በረከት ይደርባችኊ፤ ቦታዋን ያላያችሁ ለመሳለም ኹላችኹንም ያብቃችሁ እላለሁ፡፡♥
[ከመጋቤ ሐዲስ ዶክተር ሮዳስ ታደሰ]
@ewuntegna
@ewuntegna
@ewuntegna