👉 ክብር
ክብር ላከበሩን እስካሁንም ላስከበሩን በደምና በአጥንት ለገነቡን ደማቸውን አፍሰው ላለመለሙን
ጀግኖች፣ አርበኞችና አይበገሬዎች አባቶቻችን ይሁን🙏
በዓለም ካሉት ሃይማኖቶች ሁሉ የምትገፋና መከራ የሚበዛባት ሃይማኖት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ናት። እንደዚሁም ሁሉ በዓለም ካሉት ሐገሮች ሁሉ በተለያዩ ሴራዎች የምትናጥ ሐገር ብትኖር ኢትዮጵያ ናት።
ዲያብሎስ አቅም ቢያገኝ ማጥፋት ሚፈልገው ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖትን ብቻ ነው። ሌላው ግን ስለተስማማው ጠፋ አልጠፋ ግዴታው አደለም።
ዓለምም ቢችል በአንድ ቀን ጸጥ ማድረግ የሚፈልጋት ሐገር አለች እስዋም የምስራቋ ኮከብ፣ የድንግል የአሥራት ሐገር፣ የሆነች የፈጣሪ ገጸ በረከት ኢትዮጵያ ናት ።
ለዛም ነው በእየ ጊዜው መንገድ እየቀያየሩ የተለያዩ ሴራዎችን በመጠንሰስ ሐገሪቷን እረፍት የነሷት።
እግዚአብሔር ግን በቸርነቱ እስካሁን ጠብቆ አኑሯታል ምንም የውስጥ ችግር ቢፈጠርም ለጠላት ግን አሳልፎ አልሰጣትም። ችግሩንም የኛ የአስተሳሰብ ድክመት፣ በደል ያመጣው እና የጠባብ ርዮት ያላቸው አዋቂነን ባዮች ያመጡት ነገር ነው እንጂ እግዚአብሔር ሕዝቡን ጠልቶት አይደለም ችግር የመጣው ።
ይህስ ለምንድን ነው እንዲህ የሚያደርጉት ካልን በአድዋ የሽንፈትን ጽዋ ስለተጎነጩ እና። የአሰቡት ቀርቶ ያላሰቡት ነገር ስለመጣባቸው ነው። ለዛም ነው ዳግም አርባ ዘመን ቆይተው የበለጠ ተጠናክረው የመጡት ባይሳካላቸውም። መቼም አይሳካላቸውም 💪 አድዋ
👉 ይህ አድዋ
ይህ አድዋ ለነጭ ሐሣር ለጥቁር ክብር ነው።በሰማይም በምድርም በተለያዩ ብረት ለበስ የጦር መሳሪያ ታጅቦ በእብሪት የመጣውን የእብሪተኛውን ጣሊያን ትዕቢት አስተንፍሰው ምንም ዘመናዊ የጦር መሣሪያ ሳይኖራቸው
በእግዚአብሔር ኃይል በድንግል አማላጅነት በቅዱስ ጊዮርጊስ ተራዳኢነት ታቦት ይዘው ዘምተው ጸሎት አድርገው ኪዳን አድርሰው
ኃይል የእግዚአብሔር ነው።
ማዳን የእግዚአብሔር አንመካም በጉልበታችን። እግዚአብሔር ነው የእኛ ኃይላችን። ብለው ዘምረው በጽናት ተዋግተው እኛ ልጆቻቸው ተሸማቀን በባርነት አንገት ደፍተን እንዳንኖር የደምና የአጥንት ዋጋ ከፍለው ለጥቁር ሁሉ የነጻነትን ፋና አባቶቻችን የአበሩበት ቀን ነው።
👉 አድዋ
የኢትዮጵያ የድል ገድል የአፍሪካ የነጻነት አክሊል ነው ።
ይህ አድዋ የኢትዮጵያ ኩራት የአፍሪካ ነጻነት ነው ።
ይህ አድዋ የነጭን ታሪክ ያጠቆረ
የጥቁርን ታሪክ በጉልህ አንጽቶ ያሳየ ነው ።
ይህ አድዋ ትቁሮችን ሲያነጻ ነጮችን ያጠቆረ የሽንፈት ጥላሸት የቀባ ግዙፍ ታሪክ ነው ።
ይህ አድዋ የዓለምን ፍልስፍና ውድቅ አደረገ።
ይህ አድዋ የዓለምን ፖለቲካ በደቂቃ ውስጥ ቀየረ።
ይህ አድዋ የዓለምን ፍልስፍና አልፈሰፈሰ።
ይህ አድዋ አፍሪካን ቀና አውሮፓን ዝቅ አደረገ።
👉በአድዋ
የባርነት ቀንበር ያጎበጠው ጀርባ ሁሉ ቀጥ አለ።
በጥቁርነቱ ተሸማቆ ባርያ ነኝ ሲል የነበረው ሁሉ እኔ ጥቁር ነኝ ግን ውብ ነኝ ማለት ጀመረ
የነጭ ሞተ ኩነኔ የተፈረደባቸው ሁሉ ነጻ ወጡ።
አፍሪካ ከአድዋ በፊት ለዜጎችዋ ባቢሎን ሆና የመከራ ምድር ነበረች ከአድዋ በኋላ አፍሪካ ከነዓን ሆናለች።
ክብር ወድቀው ላነሱን አባቶቻችን 💪
ክብር ሙተው ላኖሩን አርበኞቻችን💪
ክብር ኮርተው ላኮሩን ኩሩዎቻችን💪
ክብር ከብረው ላስከበሩን ጀግኖቻችን 💪
ክብር ድል አድርገው ድል አድራጊነትን ላወረሱን💪 የኢትዮጵያ ሐገራችን ባለውለታዎች ሁሉ ይህንልን።💪
ermi ✍️ የካቲት.23/2017
@Ewntegna
@Ewntegna
@Edntegna