የሰሙነ ሕማማት ቀናት ስያሜና ምስጢር ከነሥርዓቱ
Zaman 888 ሰኞ ሰኞ ፦ አንጽሖተ ቤተመቅደስና መርገመ በለስ የተፈጸመበት ዕለት ነው። በሆሣዕና ዕለት ቢታንያ ያድራል በማግስቱም ከቢታኒያ ሲመጡ ተራበ። (ማር. 11÷11-14) ቅጠል ያላት በለስ ከሩቅ አይቶ ወደ በለስቱ ቀረበ ነገር ግን ከቅጠል በቀር አንዳች ፍሬ አላገኘባትም ከአሁን ጀምሮ ማንም ከአንች ፍሬ አይብላ ብሎ ረገማት። ፠ በለስ የተባለች ቤተ እስራኤል ናት ፍሬ የተባለች ሃይማኖት እና ምግባር ናት ከእስራኤል ፍቅርን ሃይማኖትን ምግባርን ፈለገ አላገኘም እስ...