ማስታወቂያ
የዓለም አቀፍ አካል ጉዳተኞች ቀን በአለም አቀፍ ደረጃ ለ33ተኛ እና በሀገራችን ደግሞ ለ 32ተኛ ጊዜ “የአካል ጉዳተኞችን የመሪነት ሚና በማጉላት አካታች እና ዘላቂ ልማትን እናረጋግጥ!” በሚል መሪ ቃል በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ በደማቅ ስነስርአት ተከብሯል፡፡
በአሉ ላይ ንግግር ያደረጉት የእለቱ የክብር እንግዳ አቶ ደስታ ሌዳሞ በሲዳማ ክልል የአካል ጉዳተኞችን የመሪነት ሚና ለማጉላት በካቢኔያቸው እና በተለያዩ የአመራርነት ሚናዎች አካል ጉዳተኞችን እንደሚያካትቱ ቃል ገብተዋል፡፡
የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ባደረጉት ንግግር የአካል ጉዳተኞችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ጉዳይ በየአመቱ በሚከበር በዓል ብቻ የሚሸፈን ሳይሆን የእያንዳንዷን ሰከንድ፣ ደቂቃ፣ ሰዓታትና ቀናትን ያላሰለሰ ጥረት የሚጠይቅ መሆኑን ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ሊገነዘበው ይገባል ብለዋል፡፡