ማንቼስተር ዩናይትድ አርሰናልን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ኤፍኤ ካፕ 3ኛ ዙር ጨዋታ ማንቼስተር ዩናይትድ አርሰናልን በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር አለፈ።
ምሽት 12 ሰዓት ላይ በኢምሬትስ ስታዲየም የተገናኙት አርሰናልና ዩናይትድ መደበኛ የጨዋታ ጊዜውን 1 ለ 1 አጠናቅቀዋል፡፡
ጨዋታው በአቻ ውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ ሁለቱ ቡድኖች ወደ ተጨማሪ ሰዓት ያመሩ ሲሆን ፥በዚህም ግብ ሳይቆጠር ቀርቷል።
አሸናፊውን ለመለየት በተሰጠ የፍጹም ቅጣት ምትም ማንቼስተር ዩናይትድ አርሰናልን 5 ለ 3 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፉን አረጋግጧል።
በአንጻሩ አርሰናል ከኤፍኤካፕ ዋንጫ ጨዋታ ውጪ ሆኗል።