ወጣትነቷን በሙሉ ለበጎ ስራ ያዋለችዋ ወ/ሮ ሙዳይ ተሸለመች
ለበርካታ አመታት በርካታ ህጻናትን እየረዳችና እያሥተማረች እንዲሁም ስራ ለሌላቸው እናቶች የስራ እድልን እየፈጠረች እና እያገዘች የቆየችዋ ይህን በጎ ተግባሯን አሁንም በርካቶችን በማቀፍ አየቀጠለች የምትገኛዋ የወጣትነት ዘመኗን በመልካም ስራ ስታሳልፍ የቆየችዋ የድሆች እህትና እናት የሆነችዋ የሙዳይ በጎ አድራጎት መሥራች የሆነችው ወይዘሮ ሙዳይ ምትኩ ታላቅ ሽልማት እና እውቅና ተሰጣት።
ሁሌ በእየ አመቱ ለሀገር ጥሩ የሠሩና በጎ የሰሩ ሴት እህቶቻችንን በመሸለም እና እውቅና በመሥጠት የሚታወቀው እንቁ ኤቨንት በትላንትናው ዕለት በአዲስ አበባ ባካሄደው "እንቁ ሴት, ንቁ ሴት, ጠንካራ ሴት" በተሰኜው 6ኛው ዙር የሽልማት ስነ ስርአቱ ከሸለማቸው ጠንካራ እና ንቁ ኢትዮጵያውያን ሴቶች መካከል ሙዳይ ምትኩ አንዷ ሆናለች።
ወይዘሮ ሙዳይ ይህን ሽልማት የሸለሟትን አዘጋጆች ካመሠገነች በኋላ መላ ኢትዮጵያውያን ድርጅታችን በአሁን ሰአት ካለው የኑሮ ውድነት አንጻር በርካታ በልተው የማያድሩ ህጻኖችና እናቶች እየበዙብን ስለሆነ እና የቤት ኪራያችንን ጨምሮ በርካታ ወጪዎች ስላሉብን ሁሌም ከጎናችን የማይለየው የኢትዮጵያ ህዝብ አሁንም ከጎናችን ይሆን ዘንድ መልዕክቴን አስተላልፋለሁ ብላለች።
ከእዚህ ጋር ተያይዞም ሁሌ በእየአመቱ እንደምናደርገው ሁሉ የገናን በአል ምክንያት በማድረግ ለአንድ ልጅ አንድ እንቁላል እንድታግዙን በማለት መልዕክቷን አስተላልፋለች።