Фильтр публикаций


መምህር አብዱላሂ አማን ይባላሉ የአርሲ / አቦምሳ/ ነዋሪ ሲሆኑ በ34ኛው ዙር የአድማስ ዲጂታል ሎተሪ የ1ኛው ዕጣ የ4 ሚሊየን ብር / አራት ሚሊየን ብር / ዕድለኛ ሆነዋል ፡፡

መምህር አብዱላሂ ባለትዳርና የአራት ልጆች አባት ሲሆኑ በደረሳቸውም ገንዘብ ቤት እንደሚሰሩበት ገልፀዋል ፡፡


የቀድሞ ፕሬዝዳንት መንግሥቱ ኃ/ማርያም በሥልጣን ዘመናቸው የመሠረተ ትምህርት ዘመቻን ተግባራዊ ለማድረግ ላበረከቱት አስተዋፅዖ Ethiopian society partnership የተባለ ድርጅት ዕውቅና ሰጥቷቸዋል። ሽልማቱን ሐራሬ ዚምባብዌ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ተገኝቼ አስረክቤያቸዋለሁ።

በዚሁ ጊዜ ባደረጉት ንግግር ''መሃይምነትን ከሃገራችን ለማጥፋት የተደረገው ጥረት እሳቸው ወደ ሥልጣን ከመምጣታቸው በፊት በንጉሡ ዘመን ''የፊደል ሠራዊት''በሚል ለጎልማሶች ትምህር ይሰጥ እንደነበረ አስታውሰው የመሠረተ ትምህርት ዘመቻ በተጀመረ ጊዜ በመላው አገሪቱ በርካታ ሰዎች ተሠማርተው በሠሩት ሥራ አመርቂ ውጤት የተገኘበት መሆኑን ገልፀዋል።

"ሽልማቱ የኔ ብቻ ሳይሆን በወቅቱ የነበሩ አብዮታውያን ጓዶች፣ተማሪዎች፣ አስተማሪዎች፣ በጎ ፈቃደኞችና መላው ኅብረተሰብ በንቃት የተሳተፈበት ስለሆነ የነሱም ነውና ክብርና ምስጋናውን እነሱም ይውሰዱ'' ብለዋል። አያይዘውም ''በዚያን ጊዜ ይህ መሃይምነትን ለማጥፋት የሠራውን መልካም ሥራ አስታውሰው ዕውቅና ለሰጡት ሁሉ ከፍ ያለ ምስጋናዬን አቀርባለሁ ''ብለዋል።

በዚሁ ሥነ ሥርዓት ላይ የተገኘችው ልጃቸው ዶክተር ትዕግሥት መንግሥቱ ''ለትምህርት ያለህ ጥማትና ፍላጎት ያኔ ገና በወጣትነትህ የተገለጠው የመጀመሪያ ልጅህን ''ትምህርት'' ብለህ ስትሰይማት ነው። ''መማር መማር አሁንም መማር'' የሚለው መፈክር የሁላችንም ትዝታ ነው። ትምህርት ለሁሉም እንዲዳረስ ያደግኸውን ጥረት በዚያ ተጠቃሚ የነበሩት ብቻ ሳይሆኑ ከመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር እኛም ቤተሰቦችህ እናደንቃለን ''ብላለች።

ዘገባው የገነት አየለ ነው።


ስለ ግንቦት 20 በዓል

ነሐሴ 2016 ዓ/ም የሕዝብ በዓላት እና የበዓላት አከባበር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁ. 1334/2016 አንቀጽ 4 እና 5 ግንቦት 20 ታስበውም ሆነ ተከብረው በሚውሉ ብሔራዊ በዓላት ዝርዝር ውስጥ አልተካተተም።

በአዋጁ አንቀጽ 19(2) “ከዚህ አዋጅ ጋር የሚቃረን ማንኛውም አዋጅ፣ ደንብ፣ መመሪያ ወይም ልማዳዊ አሠራር በዚህ አዋጅ በተሸፈኑ ጉዳዮች ላይ ተፈፃሚነት አይኖረውም” በሚል ተደንግጓል።

ይህም ሲከበር የነበረው ግንቦት 20 እንደሚቀር ያመላክታል።

ስለሆነም ግንቦት 20 ካላንደር አይዘጋም።

ሳሙኤልግርማ
የሕግ አማካሪና ጠበቃ


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ቅዱስ ገብርኤል የልባችሁን መልካም መሻት ይሙላላችሁ!!!

ቪዲዮውን ያድምጡት👇


3ኛው «መኖር በጊፍት መንደር» የሽያጭ ኤክስፖ ተከፈተ

#FastMereja I ጊፍት ሪል ስቴት በመንግስትና የግል አጋርነት ልማት ፕሮጀክት 12 ሺህ ቤቶችን ለመገንባት ከተያዘው ስምምነት መካከል የሁለተኛው ምዕራፍ ፕሮጀክት ግንባታ ማስጀመሪያና ማስተዋወቂያ እንዲሁም ሶስተኛው “መኖር በጊፍት መንደር” የሽያጭ ኤክስፖ መርሃ ግብር ተከፈተ።

ለረጅም ዓመታት በኢትዮጵያ የሪል ስቴት ዘርፍ ግንባር ቀደም ተወዳዳሪ የሆነው ጊፍት ሪል ስቴት “መኖር በጊፍት መንደር” በሚል መሪ ቃል ሶስተኛው የሽያጭ ኤክስፖ ከዛሬ ግንቦት 19 እስከ ግንቦት 24 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚያካሄድ አሳወቀ።

የጊፍት ሪልስቴት የሽያጭ እና ማርኬቲንግ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ብርቁ ይርጋ እንደገለጹት ጊፍት ሪል ስቴት ለገዢዎች እስከ 30 በመቶ የሚደርስ የአጭር ጊዜ ቅናሽ ያቀረበ ሲሆን ከ9 በመቶ እስከ 25 በመቶ ቅድመ ክፍያ በመክፈል የቤቶቹ ባለቤት መሆን እንደሚቻል እና የዚህን ታላቅ ቅናሽ ተጠቃሚ እንዲሆኑም ጥሪ አቅርበዋል።

ጊፍት ሪል ስቴት እስካሁን በ165 ሺህ ካሬሜትር ላይ በሲኤምሲ እና ፈረስ ቤት ሦስት ትላልቅ መንደሮችን ገንብቶ ለማኅበረሰቡ ማስረከብ መቻሉ የተመላከተ ሲሆን ዓለም የደረሰበትን የግንባታ ቴክኖሎጂ በመጠቀም ዘመናዊ እና ቅንጡ የመኖሪያና የንግድ አፓርትማ መንደሮችን እየገነባ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።


ቅዱስ ገብርኤል የልባችሁን መልካም መሻት ይሙላላችሁ!!!

በያለንበት ጸንተን እንቁም!

ነቢዩ ዳንኤል የመላእክት አለቃ የቅዱስ ገብርኤልን አስፈሪ ግርማ በተመለከተ ጊዜ “ዐይኖቼንም አነሣሁ “እነሆም በፍታ የለበሰውን ጥሩም የአፌዝን ወርቅ በወገቡ ላይ የታጠቀውን ሰው አየሁ፡፡ አካሉም እንደ ቢረሌ ይመስል ነበር፤ ፊቱም እንደ መብረቅ አምሳያ ነበረ፤ ዐይኖቹም እንደሚንበለበል ፋና፣ ክንዶቹና እግሮቹም እንደ ጋለ ናስ፣ የቃሉም ድምፅ እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ ነበረ፡፡ ይህንም ታላቅ ራእይ አየሁ፤ ኀይልም አልቀረልኝም፤ ክብሬም ወደ ውርደት ተለወጠብኝ ኀይልም አጣሁ፡፡ የቃሉንም ድምፅ ሰማሁ፤ የቃሉን ድምፅ በሰማሁ ጊዜ ደንግጬ በምደር ላይ በግምባሬ ተደፋሁ” አለ፡፡ በዳንኤል 10÷5-9 የተገለጸው የዚህ መልአክ ግርማ የአምላክን ግርማ ይመስላል፡፡ ቅዱስ ገብርኤል የስሙ ትርጓሜ “አምላክ ወሰብእ” ሰውና አምላክ ማለት ሲሆን ከዋነኞቹ የመላዕክት አለቆች አንዱ ነው፡፡

ቅዱስ ጳውሎስም በቈላስያስ 1÷16 በቅዱሳን መላእክት ዘንድ ስላሉት ነገዶች ሲገልጽ “… በሰማይ ያለውን በምድር ያለውን የሚታየውንምና የማይታየውን መናብርትም ቢሆኑ አጋእዝትም ቢሆኑ መኳንንትም ቢሆኑ ቀደምትም ቢሆኑ ሁሉም በእጁ ሆነ፤ ሁሉም በእርሱ ለእርሱ ተፈጠረ” በማለት ነገደ መላዕክትን ይዘረዝራቸዋል፡፡ ቅዱስ ገብርኤልም ከእነዚህ ዐበይት የመላእክት ነገዶች መካከል አንዱ በሆነው አርባብ፣ አጋእዝት ወይም ጌቶች በሚባለው ዐቢይ ነገድ ላይ የተሾመ ሲሆን ከበታቹም የሚመራቸው ዐሥር ነገደ መላእክት አሉ፡፡ ቅዱሳን መላእክት በቅዱስ ሚካኤል ፊት አውራሪነት የሰው ልጆች ጠላት ዲያብሎስን ተዋግተው ድል ከመንሳታቸው አስቀድሞ ቅዱስ ገብርኤል እንደ አምላክ ሊመለክ የወደደውን ሳጥናኤልን በመቃወም“ አይዞአችሁ ፈጣሪያችን ፈጥሮ አይጥለንምና አስክናገኘው፣ እስክናውቀው ድረስ በያለንበት እንቁም፡፡” በማለት መላእክትን ያረጋጋ መልአክ ነው፡፡

ነቢዩ ኢሳይያስ በምዕራፍ 14÷16 በሰማያት የሳጥናኤል ትዕቢትና ውድቀት ምን እንደሚመስል ሲጽፍልን “አንተ በንጋት የሚወጣ አጥቢያ ኮከብ ሆይ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ! ወደ አሕዛብ መልእክትን የላክ አንተ ሆይ እንዴት እስከ ምድር ድረስ ተቀጠቀጥህ! አንተም በልብህ ወደ ሰማይ ዐርጋለሁ ዙፋኔንም ከእግዚአብሔር ከዋክብት በላይ ከፍ ከፍ አደረጋለሁ፤ በልዑልም እመሰላለሁ አልህ፡፡ ዛሬ ግን ወደ ሲኦል ትወድቃለህ፤ ወደ ምደር ጥልቅም ትወርዳለህ” ይለናል፡፡ ቅዱስ ገብርኤል በቅድስና ሕይወት ለተጋውና በገዢዎች ዘንድ የእግዚአብሔር ቅዱስ መንፈስ ያደረበት ሰው ተብሎ ለተመሰገነው ለነቢዩ ዳንኤል ማስተዋልንና ጥበብን የሰጠ፣ እግዚአብሔር አምላክ የሰው ልጆችን ከሰይጣንና ከሞት ባርነት ነጻ ሊያወጣቸው ሰው እንደሚሆንና ሰማይንና ምድርን አሳልፎ በቅዱሳን ላይ ነግሦ እንደሚኖር በምሳሌ ገልጾ ያስተማረው መልአክ ነው፡፡

ቅዱስ ገብርኤል ቅዱሳንን ለእግዚአብሔር በመገዛታቸው ምክንያት ከአላውያን ገዢዎች ከሚደርስባቸው መከራም የሚታደጋቸው መልአክም ነው፡፡ ሦስቱ ሕጻናት አናንያ አዛርያና ሚሳኤል ለጣኦት አንሰግድም ባሉ ጊዜ በንጉሥ ናብከደነፆር ወደ እቶን እሳት ሲጣሉ እስራታቸውን ፈቶ፣ እሳቱን እንደ ውኃ አቀዝቅዞ ያዳናቸው ቅዱስ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣንም ከእሳት ያወጣ እርሱ ነው፡፡ የቅዱስ ገብርኤል ምልጃና ጸሎት ይጠብቀን፡፡ ዛሬም ይህን አማላጅነቱንና ፈጣን ተራዳኢነቱን ያመኑ ገዳማውያ አባቶች በጸሎታቸው ይጠሩታል እርሱም ይራዳቸዋል፡፡ እኛም ገዳማቸውን ስንደግፍ በዓታቸውን ስናጸና የበረከታቸው ተሳታፊ እንሆናለን፡፡


ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444




ሎተሪ የደረሳቸው በማስመሰል ከአንዲት ግለሰብ ላይ ከ70 ሺህ ብር በላይ ያጭበረበረን ግለሰብ ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ፡፡

ወንጀሉ የተፈፀመው ሚያዚያ 20 ቀን 2017 ዓ/ም በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ልዩ ቦታው አርሴማ ክሊኒክ እየተባለ ከሚጠራ ስፍራ ነው፡፡ አንድ በእድሜያቸው ገፋ ያሉ ሽማግሌ ወደ ግል ተበዳይ በመቅረብ ሎተሪ ቆርጠው  75 ሚሊዮን ብር እንደደረሳቸው ነገር ግን ሽልማቱን ለማውጣት አዲስ አበባ ዘመድ እንደሌላቸው ለሌሎች ሰዎች ቢናገሩ  ሎተሪውን እንደሚወስዱባቸው መጠራጠራቸውን በመንገር ሽልማቱን ለማውጣት  እንድትረዳቸው ይጠይቋታል፡፡

ሽልማቱ የሚሰጠው ልደታ አካባቢ መሆኑን ገልፀውላት በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 1 አ/አ 30405 ተሳፍረው  ይመጣሉ፡፡ ብሩንና ሽልማቱን እሷ እንድታወጣ  ሽማግሌውና አሽከርካሪው ካግባቧት በኋላ ለመተማመኛ የሚሆን ብር ወይም ንብረት  እንደትሰጣቸው ይጠይቋታል፡፡

የግል ተበዳይ ክፍለ ሀገር ከሚገኙ ወላጅ አባቷ በባንክ 50 ሺህ ብር አስልካ በእጇ ላይ ያለውን 6ሺ ብር ጨምራ  በጥሬ 56ሺ ብር፣ ግምቱ 15 ሺህ ብር የሚያወጣ ሞባይል ስልክ እና 5ሺ ብር የሚገመት ሀብል በአጠቃለይ 76 ሺ ብር በጥሬ 56ሺ ብር እና 20ሺ ብር ዋጋ ያላቸውን ንብረት ትሰጣለች፡፡

አጭበርባሪዎቹ ገንዘቡንና ንብረቱን ከተቀበሉ በኋላ በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ልዩ ቦታ አርሴማ ክሊኒክ አካባቢ ወደሚገኝ ህንፃ ገብታ ሽልማቱን  እንድትረከብ ይልኳታል፡፡ ህፃው ላይ ያሉ ሰዎችን ስትጠይቅ ውሸት መሆኑን ሲገልፁላት ወደ ወረደችበት መኪና ብትሄድ ሰዎቹን በቦታው የሉም፡፡

ጉዳዩ በልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ጦር ኃይሎች አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ይደሰርሳል፤ ፖሊስ ባደረገው ክትትል እና በልዩ ልዩ መንገድ ያሰባሰበውን መረጃ መነሻ በማድረግ ወንጀሉን ከፈፀሙት መካከል ሹፌሩን ከእነ ተሽከርካሪው በቁጥጥር ስር ማዋል ችሏል፡፡ ግለሰቡም አንድ ሽጉጥ ከሦስት ጥይት ጋር ይዞ መገኘቱን ፖሊስ አስታውቋል፡፡

አንደኛውን ተጠርጣሪ ለመያዝ ፖሊስ ክትትሉን መቀጠሉን ገልፆ ወንጀል ፈፃሚዎቹ አሳዛኝ እና ሽማግሌ መስለው በመቅረብ ሎተሪ  ደርሷቸው መታወቂያ ስለሌላቸው  ወይም የአዲስ አበባ ነዋሪ ባለመሆናቸው  ሽልማቱን ለማውጣት እንደተቸገሩ በማስመሰል የማታለል ወንጀል እንደሚፈፅሙ ህብረተሰቡ ተገንዝቦ  ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባ ፖሊስ መልእክቱን አስተላፏል፡፡




ጋዜጠኛ አንዱዓለም ጌታቸው የታላላቆቹ አትሌቶች መፍለቂያ ቦቆጂ ከተማ አምባሳደር ሆኖ ተመርጧል።

በ4ኛው የቦቆጂ ታላቁ ሩጫ ላይ ከአርሲ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ኢብራሂም ከድር እና ከቦቆጂ ከተማ ም/ከንቲባ አቶ በዙ አበበ እጅ አደራውን ተረክቧል።


ኢትዮጵያ የተቀቀለ ስጋ ለቻይና ልትልክ ነው

#FastMereja I ኢትዮጵያ የተቀቀለ ስጋ ለቻይና ልትልክ መሆኑን የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን አስታወቀ።

የኢፌደሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በኢትዮጵያ የግብርና ባለስልጣን የእንስሳት ቄራዎች አደረጃጀት እና የስጋ ምርት አገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነት በተመለከተ የተከናወነ ክዋኔ ኦዲት ሪፖርትን መነሻ በማድረግ ውይይት አካሂዷል።

በውይይቱ ወቅት የግብርና ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ድሪባ ኩማ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ ሞጎሊያን ጨምሮ ከተለያዩ ሀገራት ተሞክሮ በመውሰድ የተቀቀለ ስጋ ለቻይና ለማቅረብ እየሰራች ነው።

ኢትዮጵያ የቻይናን ትልቅ የስጋ ምርት ገበያ ለመጠቀም ዝግጅቷን ማጠናቀቋን አመላክተዋል።

ኢትዮጵያ የስጋ ምርትን ቻይና መላክ ከጀመረች ከቻይና የገበያ መስፈረት ጋር ተመሳሳይ ለሆኑት የአውሮፓና ኤዥያ ገበያ ማቅረብ እንደምትችልም ገልጸዋል።

በቻይና ሀገር የምርት ጥራትና ደህንነት በሚቆጣጠረው ተቋም የሚሰሩ ባለሙያዎች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው የኢትዮጵያን የስጋ አመራረት መመልከታቸውን አስታውቀዋል።

የቻይናው ተቋም ለኢትዮጵያ የላከው ከአንድ ሺህ በላይ ገጽ ያለው ዶክመንት በኢትዮጵያ ባለሙያዎች ተሞልቶ መላኩን ገልጸው፤ በቅርቡ ምላሽ ይልካሉ ተብሎ ይጠበቃል ነው ያሉት።

ኢትዮጵያ የተቀቀለ ስጋን ወደ ቻይና ስትልክ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ማግኘት እንደምትችል ተናግረዋል።

ቻይናዎች የሚፈልጉት ከበሽታ ነጻ የሆነ የእንስሳት አረባብ መሆኑን ገልጸው፤ በኢትዮጵያ ከበሽታ ነጻ የሆኑ እንስሳትን ለማርባት እየተሰራ ነው ብለዋል።

በሌላ በኩል የቻይናን ገበያ በስፋት ለመጠቀም ብዙ ቄራዎችን መገንባት እንደሚገባ ተናግረዋል።

Via: Gazette Plus ጋዜጣ ፕላስ

#ቢዝነስ


ነቢዩ ቅዱስ ሕዝቅኤልም “ወደ ምሥራቅ ወደሚመለከተው በስተውጭ ወዳለው ወደ መቅደሱ በር አመጣኝ፤ ተዘግቶም ነበር። እግዚአብሔርም ይህ በር ተዘግቶ ይኖራል እንጂ አይከፈትም፣ ሰውም አይገባበትም፤ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ገብቶበታልና ተዘግቶ ይኖራል፤” ብሎአል። ሕዝ፡44፥1። የተዘጋ የመቅደስ በር የተባለች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት። “ይህ በር ተዘግቶ ይኖራል እንጂ አይከፈትም፤” የሚለው ኃይለ ቃል በድንግልና ጸንታ እስከ ዘለዓለሙ እንደምትኖር ይነግረናል። “ሰው አይገባበትም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ገብቶበታልና ተዘግቶ ይኖራል” ሲልም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በድንግልና ፀንሳ፥ በድንግልና የወለደችው ኢየሱስ ክርስቶስ የባህርይ አምላክ በመሆኑ ከእርሷ በተዋህዶ ሰው የሆነ የባህርይ አምላክ እንጂ ዕሩቅ ብእሲ አይወለድምና በድንግልና እንደጸናች ትኖራለች።

በጳጳስ ወንበር ቄስ፣ በንጉሥ ዙፋን ራስ ደፍሮ እንደማይቀመጥ ሁሉ በአምላክ ዙፋን በቅድስት ድንግል ማርያም ማኅፀን ማን ያድራል? ለዚህም ነው እግዚአብሔር ለነቢዩ ለሕዝቅኤል አስቀድሞ የነገረው። ጠቢቡ ሰሎሞንም “እኅቴ ሙሽራ የተቈለፈ ገነት፣ የተዘጋ ምንጭ፣ የታተመ ፈሳሽ ናት፤” ብሎአል። በሥላሴ አኗኗር ወልድ ለአብ ተቀዳሚና ተከታይ የሌለው አንድ ልጅ እንደሆነ ሁሉ ለእናቱ ለቅድስት ድንግል ማርያምም ተቀዳሚና ተከታይ የሌለው አንድ ልጇ ነው። መኃ 4÷12። እንደተቆለፈች አምላክ ብቻ አድሮባት የወጣባት ገነት፣ እንደተዘጋች የዘለዓለምን ሕይወት ክርስቶስን ያመነጨች፣ እንደታተመች የሕይወትን ውኃ ክርስቶስን በአራቱም ማዕዝን አፍስሳ የተጠሙ ነፍሳትን ያረካች፣ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ብቻ ናት። “እግዚአብሔር አንድ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወድዶአልና።

በዮሐንስ 3÷17፣ ወንጌላዊው “ፍቅርም እንደዚህ ነው፤ እግዚአብሔር እርሱ ራሱ እንደ ወደደን ስለ ኃጢአታችንም ማስተስረያ ይሆን ዘንድ ልጁን እንደ ላከ እንጂ እኛ እግዚአብሔርን እንደ ወደድነው አይደለም፤” ይላል።  ይህን መውደድ ይህን ፍቅር የገለጸው ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በድንግልና በመወለድ ነው። የእመቤታችን ድንግልና በሦስት ወገን በሥጋዋ በነፍሷና በልቡናዋ ነው። ይህ ድንግልና የዘለዓለም ድንግልና ነው። ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ኢሳይያስ በትንቢቱ ምዕራፍ 7÷14 “ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ ድንግል ትፀንሳለች፣ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፣ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች፤” ብሎአል። እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከመጽነሷ በፊት፣ በጸነሰችም ጊዜ፣ ከጸነሰችም በኋላ ድንግልናዋ የጸና ነው፤ ከመውለዷ በፊት፣ በወለደችም ጊዜ፣ ከወለደችም በኋላ ኅትምት በድንግልና ናት።

የውዳሴ ማርያም አንድምታ ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል አንቺ ከሴቶች ሁሉ ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ ያላትን አብራርቶ ይነግረናል፡፡ እመቤታችን መልአኩ ሲያበስራት “ወንድ ሳላውቅ ይህ ነገር እንደምን ይሆንልኛል?” የሚል ጥያቄ አንስታ ነበር፡፡ ይህን ያለችው ክብር ይግባትና የወንድ ሀሳብ በአእምሮዋ ፈጽሞ ተመላልሶ ስለማያውቅ ነው፡፡ ሌሎች ሴቶች ስለወንድ ከመናገርና በሕጋዊ ሩካቤ ከመገናኘት ቢታቀቡ ከማሰብ ግን አይነጹም፡፡ እምቤታችን ግን ከመናገር ከማድረግ ከማሰብ ንጽህት ናትና ይህን አለች፡፡ ይሕን ንጽህናዋን መሰረት አድርገው ከዓለም ፍቅርና ከስጋ ገበያ የራቁ ገዳማውያን አባቶችና እናቶች ቅድስት ሆይ ለምኝልን ሳይሏት አይውሉም፡፡ የጸሎታቸው ማረግ፣ የቅድስናቸው ዘውግ እርሷ ናትና፡፡ እኛም ገዳማቸውን ስንደግፍ በዓታቸውን ስናጸና የበረከታቸው ተካፋይ እንሆናለን፡፡


ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444




በኤምፖክስ ቫይረስ የተያዘ ሰው በሞያሌ ተገኘ

የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት በኦሮሚያ ክልል ሞያሌ ከተማ እስተዳደር ከሚገኙ በህመሙ መያዛቸው ከተጠረጠሩ ታማሚዎች በወሰደው ናሙና በMpox ቫይረስ የተያዘ ሰው ማግኘቱን አረጋግጧል።

ቫይረሱ እንደተገኘበት የተረጋገጠው የ21 ቀን እድሜ ያለው ህፃን ልጅ ሲሆን እናቱም በተደረገው ቀጣይ ምርመራ ለቫይረሱ እንደተጋለጠች ለማረጋገጥ ተችሏል

ከጤና ሚኒስቴር እና ከኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት MPox አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት በኦሮሚያ ክልል ሞያሌ ከተማ እስተዳደር ከሚገኙ በህመሙ መያዛቸው ከተጠረጠሩ ታማሚዎች በወሰደው ናሙና በMpox ቫይረስ የተያዘ ሰው ማግኘቱን አረጋግጧል።

ቫይረሱ እንደተገኘበት የተረጋገጠው የ21 ቀን እድሜ ያለው ህፃን ልጅ ሲሆን እናቱም በተደረገው ቀጣይ ምርመራ ለቫይረሱ እንደተጋለጠች ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡ የህፃኑ አባትም ወደ ጎረቤት ሀገር ሄዶ የነበረ መሆኑ መታወቁና የሄደባቸውን አካባቢዎች እንዲሁም ከግለሰቡ ጋር የቅርብ ንክኪ የነበራቸው ግለሰቦችን የመለየትና ክትትል የማድረግ ስራ ተጀምሯል።

ታማሚው ህፃን እና እናቱ፣ አስቀድሞ በተዘጋጀው የለይቶ ማከሚያ፣ ተገቢው የሕክምና ክትትል እየተደረገላቸው ሲሆን፣ እስካሁን ባለው ሁኔታ የከፋ የጤና እክል አልገጠማቸውም፡፡

የጤና ሚኒስቴር፣ በሽታው በአህጉራችን ከተከሰተበት ወቅት ጀምሮ ወደ አገር ውስጥ እንዳይገባና ከገባም ጉዳቱን ሳይከፋ በቁጥጥር ውስጥ ለማድረግ እንዲቻል በርካታ ስራዎችን ሲያከናውን መቆየቱ የሚታወቅ ሲሆን ለዚሁ በሽታ መካላከል ሲባል በኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ውስጥ የድንገተኛ አደጋዎች ማስተባበርያ ማዕከል ተቋቁሞ እየሰራ ይገኛል።

ከዚህም ባሻገር በዚህ ቫይረስ ለመያዛቸው የተጠረጠሩ ግለሰቦች ማቆያ የሚሆኑ የተለዩ የጤና ተቋማት የተዘጋጁ ሲሆን በዚህ በሽታ የታመሙ ሰዎችን ለማከምና ተገቢውን አገልግሎት ለመስጠት የተለያዩ የጤና ተቋማት አስፈለጊውን ዝግጅት አጠናቅቀዋል።

የMpox በሽታ በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት እየተከሰተ ያለ ህመም ሲሆን ዋና መስሪያ ቤቱን በአዲስ አበባ ያደረገው የአፍሪካ የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር ማዕከል እና የዓለም አቀፍ የጤና ድርጅት በመተባበር በሽታውን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የተለያዩ መጠነ ሰፊ ስራዎችን በጋራ እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ የጤና ሚኒስቴርም ከነዚህና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር በሽታውን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር እያከናወናቸው የነበሩና ያሉ ስራዎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ለመግለፅ እንወዳለን።

የMpox በሽታ ቫይረሱ ካለባቸው ግለሰቦች ጋር ንክኪ ያለው ሰው የሚከተሉት ምልክቶች በሚታዩበት ወቅት ማለትም ሽፍታ፡ ሳል፣ ትኩሳት፣ ፣ የራስ ምታት፣ ድካም እና የጀርባ ህመም ሲያስተውል በአፋጣኝ ወደ ጤና ተቋማት በመሄድ ተገቢውን የምርመራና ህክምና አገልግሎት እንዲያገኝ አንዲሁም የግል እና የእጅ ንፅህና በመጠበቅና ከላይየተገለፁት ምልክቶች ባሉባቸው ታማሚዎች አካባቢ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛዎችን በመጠቀም ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ጥሪ እናቀርባለን። በአሁኑ ወቅት ይህ በሽታ በተወሰነ ቦታ ብቻ የታየ በመሆኑ ህብረተሰባችን ሳይደናገጥ የተለመደውን አኗኗር መቀጠል የሚችል ሲሆን ከጤና ሚኒስቴር እና ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሚወጣውን ወቅታዊ መረጃዎች በአግባቡ በመከታተል ራሱን እና ቤተሰቡን ከዚህ በሽታ እንዲጠብቅ እናሳስባለን።

ዶ/ር መቅደስ ዳባ
የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር




ኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ የመኪና ስጦታ ተበረከተለት!

የየሲር ለና በጎ አድራጎት ድርጅት መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት ኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ የቲሞችን በመንከባከብ እና ሙስሊሙን ማህበረሰብ በማስተማር ላበረከቱት አስተዋጽኦ የመኪና ስጦታ ተበርክቶላቸዋል።

የተሽከርካሪ ስጦታው የተበረከተው የበጎ አድራጎት ሥራዎቻቸውን በሚደግፉ አካላት እና በሥም ባልተጠቀሱ የቅርብ ወዳጆቻቸው አነሳሽነት መሆኑን ሚንበር ቲቪ ዘግቧል።


የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ በ34ኛው የኤርትራ ነጻነት በዓል ላይ ባደረጉት ንግግር በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ጠንካራ ትችት ሰነዘሩ።

"የውሃ ጉዳይ፣ አባይ እና ቀይ ባሕር፣ የባሕር በር ማግኘት፣ የኦሮሞ ሕዝብን የማይወክል የኦሮሙማ አስተሳሰብ፣ የኩሽ እና የሴም ግጭት፣ የአፋር ሕዝብ እና መሬትን ለዚህ አጀንዳ መጠቀም እንዲሁም ጦርነት በሰፊው መቀስቀስ" ነው በማለት ከስሰዋል።

ይህንን ለማሳካት ፕሬዚደንት ኢሳያስ የውጭ ኃይሎች ባሏቸው እገዛ የኢትዮጵያ መንግሥት "የጦር መሳሪያ ግዢ እና የወታደራዊ ዝግጅት" ላይ እንደሆነ ባደረጉት ንግግር ጠቅሰዋል።


የተወለደው ክርስቶስን ከሚጠሉ ከአንድ አህያ በቀር ምንም ከሌላቸው ድኆች አይሁዳውያን ቤተሰቦች ነው፡፡ ይባስ ብሎ በልጅነቱ አባቱ በመሞቱ ከእናቱና ከአንዲት እህቱ ጋር በረኃብ ሊያልቁ ሆነ፡፡ ሕጻኑ ኤጲፋንዮስ በአህያው እንዳይሠራ ክፉ ነበርና በእናቱ ምክር ሊሸጠው ገበያ ይዞት ሲጓዝም ፊላታዎስ ከሚባል ጻድቅ ክርስቲያን ጋር ተገናኘ፡፡ ሊገዛው ሲደራደሩም አህያው የኤጲፋንዮስን ኩላሊቱን ረግጦት ለሞት አደረሰው፡፡ በዚህ ጊዜ አብሮት ያለው ጻድቁ ክርስቲያን ፊላታዎስ በስመ ሥላሴ በትእምርተ መስቀል አማትቦ በቅፅበት አዳነው፡፡ አህያውንም ስለ እኛ በተሰቀለው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ትሞት ዘንድ ይገባሃል ሲለው አህያው ወዲያው ሞተ፡፡ ኤጲፋንዮስም ሁለቱን ተአምራት ካየ በኋላ “በስሙ ተአምራት የምታደርግበት የተሰቀለው ኢየሱስ ክርስቶስ ማነው?” አለው፡፡ ፊላታዎስም ክርስቶስን ሰበከለትና ኤጲፋንዮስ እያደነቀ ሄደ፡፡

ከወራት በኋላ ሀብታም አይሁዳዊ አጎቱ ኤጲፋንዮስን ወሰደውና ገንዘቡን ሁሉ አውርሶት ሞተ፡፡ ኤጲፋንዮስም ገና በ16 ዓመቱ ባለጸጋ ሆነ፡፡ የኦሪትን ሕግ ሁሉ እየተማረ ቢያድግም ያቺ ገበያ ላይ ያያት ተአምር ግን በልቡ ውስጥ ትመላለስ ነበር፡፡ በአንዲት ዕለትም ስሙ ሉክያኖስ ከሚባል ጻድቅ መነኩሴ ጋር ተገናኘ፡፡ አብረው ሲሔዱም አንድ ነዳይ አገኙና ምጽዋት ጠየቃቸው፡፡ ሉክያኖስም ገንዘብ ስለሌው የሚለብሰውን የጸጉር ዐፅፉን አውልቆ ለድኃው መጸወተው፡፡ በዚያን ጊዜ መላእክት የብርሃን ልብስ ከሰማይ አውርደው ሲያለብሱት ኤጲፋንዮስ ተመለከተ፡፡ ይህን ጊዜ ኤጲፋንዮስ ከመነኩሴው እግር ሥር ሰግዶ ክርስቲያን እንዲያደርገው ለመነው፡፡ መነኩሴውም ወስዶ ለኤጲስቆጶሱ ሰጠውና አስተምሮ አጠመቀው፡፡ መመንኮስም እንደሚፈልግ ቢነግረው ሀብት ንብረት እያለህ መነኩሴ መሆን አይገባህም አሉት፡፡

ኤጲፋንዮስ እኅቱን አምጥቶ አስጠመቃትና ገንዘቡን ሁሉ ሸጦ ለድኆችና ጦም አዳሪዎች መጸወተው፡፡ በተረፈው ደግሞ ቅዱሳት መጻሕፍትን ገዛቶ መነኮሰና ለእርሱም ለእኅቱም ለጥምቀት ምክንያት ወደሆነው ሉክያኖስ ወደተባለው መነኮስ ገዳም ገና በ16 ዓመቱ ገባ፡፡ በዚያም ከሽማግሌውን አባ ኢላርዮስን ሕግጋትን ሁሉ ተማረ፡፡ መናንያኑ እስኪያደንቁት ድረስም በፍጹም ትጋትና ቅድስና በተጋድሎ ኖረ፡፡ በርካታ ድንቅና ተአምራትንም አደረገ፡፡ ድውያንን ፈወሰ፣ በጸሎቱ ሙታንን አስነሣ፣ ከደረቅ መሬት ላይ ውኃን አፈለቀ፡፡ ያለጊዜውም ዝናም አዘነመ፡፡ ብዙ አይሁዶችንም ተከራክሮና በተአምሩ እያሳመነ አጠመቃቸው፡፡ ከዚህም በኋላ መምህሩ ኢላርዮስ በነገረው ትንቢት መሠረት በቆጵሮስ ደሴት ላይ ጳጳስ ሆኖ ተሾመ፡፡ ብሉይን ከሐዲስ የወሰነ እጅግ ምጡቅ ሊቅ ነውና ብዙ መጻሕፍትን ተረጎመ፡፡

ሃይማኖተ አበው ዘኤጲፋንዮስ፣ መጽሐፈ ቅዳሴውንና ስነ ፍጥረትን በዝርዝር የሚተነትነውን መጽሐፈ  አክሲማሮስን  ጨምሮ በሺሕ የሚቆጠሩ ድርሳናትን ደረሰ፡፡ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ በአፍም በመጽሐፍም እየጠቀሰ መናፍቃንንና አይሁድን ምላሽ በማሳጣቱ ሊቃውንት የቤተ ክርስቲያን ጠበቃ ይሉታል።፡ የከበረና የተመሰገነ ሊቁ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ በመልካም እረኝነትና በሚደነቅ ቅድስና ሲያገለግል ኖሮ ግንቦት 17 406 ዓ.ም ዐርፏል፡፡ ታላላቅ የቅድስና ማዕረጋት ላይ የደረሱ ቅዱሳን አባቶችና እናቶች ያላቸውን ሁሉ ሸጠው ለድሆች በመመጽወት ዓለምን ትተው ጋታችንን ተከትለውታልና ጸሎታቸው ኃይልን ታደርጋለች። ገዳማቸውን ስንደግፍ በዓታቸውን ስናጸና የበረከታቸው ተሳታፊ እንደምለን። የቅዱስ ኤጲፋንዮስ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን፡፡


ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444




ትውልዱ የመጥሪያ ካርድ ሁላ ለማንበብ የሚሰላች ሆኗል

#FastMereja I በሰላማዊት አድማሱ የተፃፉ ሁለት የግጥም መድብሎች ተመረቁ። “ነብር እና ነባር” የተሰኘ በአማርኛ የተፃፉ ስብስቦች እንዲሁም “Call for peace” የተሰኘ በእንግሊዘኛ የተፃፉ የግጥም መድብሎች ናቸው።

ሁለቱም መጽሐፎች በሀገራችን እና በዓለም ላይ የሰው ልጅ ስላለው ፍቅር፣ አንድነት፣ ጭካኔ፣ ርህራኄ የህይወት ውጣ ውረድ ላይ የሚያጠነጥን መፅሐፍ መሆኑን ሰላማዊት ገልጻለች።

ነብር እና ነባር 167 የገፅ ብዛት ሲኖረው፣ እንግሊዘኛው በ152 የገጽ ብዛት ታትሞ ቀርቧል።

መጽሐፍ ይታተማል የሚገዛ የለም ያለችው ደራሲዋ ሰው ወደ ሶሻል ሚዲያ እየሄደ ነው፣ የመጥሪያ ካርድ ሁላ ለማንበብ የሚሰላች ትውልድ ነው አሁን ያለው ህዝቡ በማንበብ እንዲነቃቃ የደራሲያን ማህበረን መንግስት እንዲደግፍ ሰላማዊት ጥሪ አቅርባለች።

በቀጣይ አጫጭር ልቦለዶችን ለማሳተም እንዲሁም የቴአትር ጽሁፎችን ወደ መድረክ ለማውጣት እንደምትሰራ ተናግራለች።

Показано 20 последних публикаций.