በኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የተሠጠ መግለጫ
“የሃይማኖት ንጽጽር - በከፍተኛ የሃይማኖት ሊቃውንቶች መካከል በሕግ፣ በሥርዓት እና በጥብቅ ዲሲፕሊን የሚመራ በዶግማዊ ጉዳዮች ላይ የሚደረግ የሰከነ ውይይት ነው፤ በአማኞች መካከል የሚደረግ ሥርዓት የለሽ እና አንዱ ሌላውን የሚያውገዝ፣ የሚያጠልሸ እና ክብረ-ነክ መሆን ወንጅል ነው፤” ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የማኅበራዊ ሚዲያውን እድገትና ተደራሽነት መስፋትን ተከትሎ በተለያዩ ርዕሠ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩሩ አጀንዳዎች ላይ በአወንታዊነት እና በአሉታዊነት የሚፈረጅ ይዘት ያላቸው ሥራዎች ተሠርተው አየር ላይ ሲውሉ እናያለን፤
አንዳንዶች ደግሞ የራሳቸውን የማኅበራዊ ሚዲያ መድረክ በመክፈት የተለያዩ ግለሰቦችን ወደመድረካቸው በመጋበዝ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ በደጋፊነት እና በነቃፊነት ላይ ተሰልፈው የጦፈ ክርክር ሲደርጉም እንመለከታለን፡፡
ዘርፉና የመገናኛ መድረኩ የራሱ የሆነ የአጠቃቀም መመሪያ ያለውና በጥብቅ ዲሲፕሊን እንዲመራ የሚጠበቅ ቢሆንም አንዳንድ ግለሰቦችና ቡድኖች መድረኩን ከዓላማው ውጪ ለሆነና ለግልና ቡድናዊ ፍላጎታቸው መጠቀሚያ በማድረግ በተለያዩ ሃይማኖት/እምነት ተከታዮች መካከል መተማመኑ እና መከባበሩን የሚሸረሽሩ ይዘቶችን፣ ክብረ ነካዊ በሆነ አቀራረብ ግልፅ ጥላቻን የመስበኩ ልምምድ ከጊዜ ወደጊዜ እየተባባሰ ይገኛል፡፡
ይህ ዓይነቱ አቀራረብና ልምምድ አልፎ አልፎ በአንዳንድ የሃይማኖት ተቋማት ውስጥ በመደበኛ የአምልኮ መርሀ ግብር ላይ በፊት ለፊት መድረኮች ሲቀርብ አይተናል፡፡ ልምምዱና አቀራረቡ ከወዲሁ ሊታረምና በሕግና ሥርዓት ሊከናውን እንደሚገበው ጉባኤያችን በጽኑ ያምናል፡፡ ከዚህ አንፃር ከሰሞኑ የሁለቱ ታላላቅ ሃይማኖቶች የተቀደሰ የጾም፣ የጸሎትና በከፍተኛ ደረጃ የመንፈሳዊ እነፃ ላይ በሚገኙበት ጊዜ ከመንፈሳዊነትና ከሃይማኖቶች መሠረታዊ ዕሴት ጋር የሚቃረን ተግባር በማኅበራዊ ሚዲው በስፋት እየተሠራጨ ይገኛል፡፡
በተለይም አንዳንድ የኦርቶዶክስ ክርስትና አማኝ ነን የሚሉ ግለሰቦች፣ የእስልምና ሃይማኖት ነቢይ በሆኑት በነቢዩ መሐመድ (የአላህ እዝነትና ሰላም በእሳቸው ላይ ይሁንና) ላይ ድፍረት የተሞላበት ክብረ ነክና ጽያፍ ንግግር ሲያደርጉ ታየረተዋል፡፡ ይህም ሙስሊሙን ወገን ብቻ ሳይሆን ሰላም ወዳዱን ወገን ሁሉ አሳዝኗል፡፡
ጉባኤችንም ይህ ዓይነቱ ኢ-ሥነምግባራዊ እና ሕገ ወጥ ተግባር የትኛውንም የሃይማኖት ተቋም የማይወክል፣ ይልቁንም የሚወገዝ ተግባር መሆኑን ለመግለጽ ይወዳል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘም አንዳንድ የኦርቶዶክስ አማኝ ነን የሚሉ ወንድሞችና እህቶች የግለሰቡን ሕገ-ወጥ ተግባር ተቋማዊ ለማድረግ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ እንዲያጤኑና ግለሰብንና ተቋምን እንዲለዩ እንመክራለን፡፡
በአንፃሩ አንዳንድ ሙስሊም ነን የሚሉ ግለሰቦች ተደፈርን በሚል ስሜት የክርስትና አስተምህሮንና የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር የሚነቅፍና የሚያጠለሽ፣ መላውን ክርስቲያን በሚያዋርድ መልኩ ምላሽ ሲሠጡ እና ድርጊቱን በፈፀመው ግለሰብ ላይ የደቦ ፍርድ ሲያስተላልፉ ይታያሉ፡፡
ይህም ሕገ-ወጥነትን ከማስፋፋት ባለፈ ጥፋትን በሌላ ጥፋት ማረም ፈጽሞ የማይቻል መሆኑን ተገንዝበው ከድርጊታቸው በመታረም የሕግ የበላይነትን እንዲስቀድሙ ጉባኤያችን በአጽንኦት ይመክራል፡፡ በየትኛውም አካል የተፈፀሙትና የሚፈፀሙት ይህን መሠል ሕገ-ወጥ ተግባራት በሁሉም ሃይማኖቶች አስተምህሮ ተቀባይነት
የሌላቸው ብቻ ሳይሆን የሚወገዙ ተግባራት መሆናቸውን ጉባኤያችን እያስገነዘበ ድርጊቱ በወንጀል የሚስጠይቅ ስለመሆኑም ለማስታወስ ይወዳል፡፡
ሀገራችን ኢትዮጵያ የብዝሀ ሀይማኖት መገኛና መኖሪያ ከመሆኗ አንፃር የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የትኛውንም ዓይነት የሃይማኖት ተቋማትን፣ አስተምህሯቸውንና መገለጫዎቻቸውን የሚያንቋሽሹና የሚያዋርዱ ንግግሮችንም ሆነ ተግባራትን በጽኑ ያወግዛል። እንዲህ ያሉት ክብረ-ነክ የሆኑ ተግባራትና አስተያየቶች ሁሉ ድርጊቱ ለተፈፀመባቸው እምነት ተከታዮችን በእጅጉ የሚያስቆጡ ብቻ ሳይሆኑ መላ ኢትዮጵያዊያንን በእጅጉ የሚያስቆጡ ናቸው፡፡ የመከባበርና የአብሮነት እሴቱን በመሸርሸር በሀገራችን የሰላምና የሰላማዊ ማህበረሰብ ግንባታ ሂደቱንና ጥረቱን እንዳይያሳካ ያደርጋሉ፡፡
ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት አንዱ የሌላውን እምነት ለመስደብ ወይም ለማዋረድ በፍፁም ጥቅም ላይ መዋል የለበትም። የእምነት ነፃነት እና የማምለክ መብት ለሁሉም ማህበረሰቦች የተጠበቀ ሲሆን ይህ መብት የሌሎች አማኞችን መብት በመጋፋና ስሜት በመንካት ለጠብ ማነሳሽነት ሲውል በዝምታ ሊታለፍ አይገባውም፡፡
ይህንን ከባድ ጥፋት በዘላቂነት እንዲታረም የሚመለከታቸው አካላት አግባብነት ባላቸው ሕጎች መሰረት ይህንንና ተመሳሳይ ተግባር በፈፀሙና በሚፈጽሙ አካላት ላይ አፋጣኝ ሕጋዊ እርምጃ እንዲወስዱ እንጠይቃለን። ለእንደዚህ አይነት ወንጀሎች ተጠያቂነትን ማረጋገጥ ለወደፊቱ የሃይማኖትን ስም ማጥፋት ለመከላከልና የሁሉም እምነት ተከታዮች ክብርን ለመጠበቅና
ለማስጠበቅ በእጅጉ ይረዳል።
በተጨማሪም የሃይማኖት መሪዎች፣ የሃይማኖት ምሁራን እና መላ ሕብረተሰቡ በሃይማኖቶች መካከል መከባበር፣ መግባባትና መረዳዳት ይበልጥ ሊያጠናክሩ በሚያስችሉ የጋራና የተመረጡ አጀንዳዎች ላይ በሕግ፣ በሥርዓትና በጥብቅ ዲሲፕሊን የሚመሩና ግልጽ ዓላማና ግብ የተቀመጠላቸው ውይይቶችና ምክክሮች በተጠናከረ መልኩ በማከናውን በሃይማኖቶች መካከል ትብብራቸውንና አጋርነታቸውን እንደ ሚያጠናክሩ ይጠበቃል፡፡
በቅርቡ ጉባኤያችን ወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታዎችን በመዳሰስና በመተንተን ሀገራዊ ዓውዱንና ተግዳሮቶች ታሳቢ በማድረግ፣ እንዲሁም ተቋሙ ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆን ለማስቻል የመተዳደሪያ ደንቡን አሻሽሏል፡፡ የተሻሻለው ደንብም በተቋማት መካከል አለመከባበርን፣ አለመቻቻልን የሚሰብኩ፣ ጥላቻን የሚቀሰቅሱና ግጭትን የሚያባብሱ ተንኳሽና ክብረ-ነክ ንግግሮችንና ተግባራትን የሚፈፅሙ ግለሰቦችና ቡድኖች በራሳቸው ተቋም ተጠያቂ የሚያደርግ ሥርዓት እንዲኖር የሚያደርግ ድንጋጌ በደንቡ ላይ እንዲካተት ተደርጓል፡፡
የችግሩ ስፋትና ጥልቀት እየጨመረ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞም ችግሮን በዘላቂነት ለመፍታትም ከአባል የሃይማኖት ተቋማት የሚወከሉ የሕግና አግባብነት ያላቸው ባለሙያዎች የሚካተቱበት የተከላካይ ግብር-ኃይል አደረጃጀት በጊዜያዊነትና በቋሚነት በማደራጀት የቅደመ መከላከል ሥራዎች ለመስራት ተዘጋጅቷል፡፡
ግብር-ኃይሉም ችግሮችንና የችግር አዝማሚያዎችን በማሰባሰብ፣ በመተንተንና የመፍትሔ ሀሳቦችን በመስጠት ሙያዊ እገዛ በማድረግ ሕግና ሕጋዊነትን የማስጠበቅ ሥራ በመስራት የሀገር ሰላምንና የሃይማኖት ተቋማትን ክብርና ልዕልና የማስጠበቅ ኃላፊነቱን ይወጣል፡፡
የሁለቱም እምነት ተከታዮች እና አማኞች በማኅበራዊ ሚዲያው ባለው አሉታዊ ዘመቻና በተፈጠረው ወቅታዊ ችግር ሳይረበሹ የጾም፣ ጸሎትና የንስሀና ተግባሮቻቸው ላይ እንዲያተኩሩ ጉባኤያችን ይመክራል፡፡
የሕግ አስከባሪ አካሉም፣ በአማኞች መካከል ያለው ሰላምና መከባበር የሚያውኩ፣ ሕገ-ወጥ ግለሰቦችና ቡድኖች ከድርጊታቸው እንዲታረሙ በማድረግ ሕግና ሥርዓት የማስጠበቅ የተለመደ ሕጋዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጉባኤያችን ጥሪውን ያቀርባል፡:
በመጨረሻም ሁላችንም የሃይማኖት ተቋሞቻችንንና የአስተምህሯችንን ክብር፣ ልዕልናና ቅድስና እንጠበቅ በማለት ጉባኤያችን የአደራ መልዕክቱንና ጥሪውን ያቀርባል፡፡