#እመቤታችን ሰማያትን ያሳየችው ቅዱስ
የትውልድ ሃገሩ ሶርያ ውስጥ ሮሃ አካባቢ ነው፡፡ ተወልዶ ባደገባት ሃገር ይህ ቀረው የማይባል ኃጢአተኛ ሰው ቢሆንም እመቤታችን ቅድሰት ድንግል ማርያምን በፍፁም ልቡ ይወዳት ነበርና በመዳን ቀን ጥሪ ለንስሐ አበቃችው፡፡ ከዚያች ዕለት ጀምሮም ቅዱስ የእግዚአብሔር ሰው፣ ንጹሕ የቤተ ክርስቲያን መስዋዕት፣ ጽኑዕ የበርሃ ምሰሶ ሆነ፡፡ ድንግል እመቤታችንም ከነሥጋው ወደ ሰማያት ወስዳ ገነትና ሲዖልን አሳይታ፣ ከአዳም ኖኅ፣ ከአብርሃም እስከ ሙሴና ዳዊትን ከመሰሉ ቅዱሳን ጋር አገናኘችው፡፡ ከዚህም በላይ የሆነና በሰብአዊ አንደበት የማይነገር ብዙ ምሥጢር አሳይታ ወደ ምድር መልሳዋለች፡፡ ይህም በቅድስት ቤተክርስቲያናችን ቅዱስ ጎርጎርዮስ ረዓዬ ኅቡዓት ምሥጢራትን የተመለከተ እየተባለ እንዲጠራ አድርጎታል፡፡
ቅዱስ ጎርጎርዮስ በሰማይ በነበረው ቆይታ ክብረ ቅዱሳንን ተመልክቶ አድንቋል:: በተለይ በፍጹምነት ድንግልናቸውን የጠበቁ ቅዱሳንና ቅዱሳት ደናግል አኗኗራቸው ከአምላክ እናት፣ ከሰማይ ንግሥት፣ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋር መሆኑን አይቷል፡፡ "የለበሱት ልብስም በፍጡር አንደበት ተከናውኖ ሊነገር የሚቻል አይደለም" ይላል፡፡ የደናግል ፊታቸው ከፀሐይ 7 እጅ ያበራልና ግርማቸው ያስፈራል፡፡ ቅዱስ ጎርጎርዮስ በዚያው በሰማይ ሳለ ደግሞ ይህንን ተመለከተ፡፡ አንድ አረጋዊ፣ ጽሕሙ ተንዠርግጐ፣ የብርሃን ካባ ላንቃ ለብሶ ይመጣል፡፡ ቅዱሳን መላእክት በፊት በኋላ፣ በቀኝ በግራ ከበውት ሳለ እግዚአብሔርን በበገናው ሊያመሰግን ጀመረ፡፡ "አቤቱ ጌታችን በምድር ሁሉ ስምህ የተመሰገነ ሆነ" ሲል መላእክቱ በዝማሬ አጀቡት::
በዚህ ጊዜም ታላቅ መናወጥ ሆነ፡፡ ደናግሉም የቅዱሱን ሽማግሌ በረከቱን ተሳተፉ፡፡ ይህ አመስጋኝ ሽማግሌ ልበ-አምላክ፣ ጻድቅ፣ የዋህና የእሥራኤል ንጉሥ ዳዊት ነበር፡፡ አንድም እመቤታችን "አባቴ ዳዊት!" ብላ ስትጠራው ቅዱስ ጎርጎርዮስ ሰምቷልና፡፡ በመጨረሻም እመቤታችንን በፍጹም ክብርና ግርማ ተመልክቷት ሐሴትን አድርጓል፡፡ እመ-ብርሃንም "ተወዳጅና ንጹሕ ሰው ነህ" ስትል ቅዱስ ጎርጎርዮስን አመስግናዋለች፡፡ ስለዚህ ዓለምም እንዲህ የሚል መልእክትን ልካለች:: "ልጆቼ ሆይ! ከብርሃን ጨለማን፣ ከደግነት ክፋትን፣ ከጽድቅ ይልቅ ኃጢአትን ምነው መምረጣችሁ? እኔ ስለ እናንተ በየቀኑ እየለመንሁ እነሆ አለሁ:: ወደ ጨለማ ገሃነም እንዳትወርዱ እባካችሁ ንስሐ ግቡ!"
ቅድስት ድንግል ማርያም ይህንን ለቅዱሱ ሰው ነግራው፣ ቅዱስ ዳዊትን አስከትላ በግሩማን መላእክት ታጅባ የእሳት መጋረጃዎች ወደ ተተከሉበት ድንኳን ገባች፡፡ በዚያም ተመሰገነች፡፡ ታላቁ አባት አባ ጊዮርጊስ ዘጋሰጫም "ይዌድስዋ መላእክት ለማርያም በውስተ ውሳጤ መንጦላዕት፣ ወይብልዋ፣ በሐኪ ማርያም ሐዳሲሁ ጣዕዋ"፤ “መላእክት ማርያምን በመጋረጃዎች ውስጥ ላንቺ ምስጋና ይገባሻል እያሉ አመሰገኗት” የሚለንም ለዚህ ነው፡፡ ቅዱስ ጐርጐርዮስም ከሰማይ ቆይታው መልስ ያየውን ሁሉ ጽፎ ለአበው ሰጥቷል፡፡ ስለዚህም ረዓዬ ኅቡዓት “ምሥጢራትን ያየ” ይሰኛል፡፡ ቅዱሱ ተረፈ ዘመኑን በተጋድሎ ፈጽሞ በመጋቢት ሁለት ቀን አርፏል፡፡ የቅዱሱ እመቤት ድንግል እመ ብርሃን መዓዛ ፍቅሯን ታብዛልን፡፡ በቅድስና ሕይወት፣ በገዳማዊ ኑሮ ያሉትን እየረዳንና በዓታቸውን እያጸናን የበረከታቸው ተሳታፊ እንሁን፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444