በርካታ ዓመት በትዳር የቆዩ ባለትዳሮች ሊሸለሙ ነው! የጠቆመም ይሸለማል ተብሏል።
#FastMereja I የጥንዶችን የጋብቻ ቀን በማክበር ዕውቅና ሽልማት ሊሰጥ ነው። ያሜንት ሃ/የተ/የግል/ ማህበር በ2017 ዓ.ም ለ500 ኢትዮጵያውያን ጥንዶች የጋብቻ ቀናቸውን በድምቀት ማክበር ሲሆን ይኸውም የ10፣ 15፣ 25፣ 50 እና ከዚያም በላይ ጊዜ የቆዩ ባለትዳሮችን ያካትታል፡፡
በተጨማሪም 10 ጥንዶች በሁነቱ ላይ የጋብቻ ቀለበታቸውን የሚያስሩ ይሆናል፡፡
በመሆኑም በጠቅላላው 495 ባለትዳር ጥንዶችና 10 እጮኛሞች ግንቦት 17 ቀን 2017 ዓ.ም የኩነቱ ታዳሚዎች ይሆናሉ፡፡
ሐምሌ 6 ቀን 2017 ዓ.ም ልዩ ልዩ ሚዲያዎችን በመጠቀም ከተጋቡ ረጅም ዘመናት ያስቆጠሩ 20 ጥንዶች መሳጭና ትምህርት ሰጭ የሆኑ የህይወት ተሞክሮዎቻቸውን በሁነቱ ለታደሙና በሚዲያ ለሚከታተሉ የማህበረሰብ ክፍሎች እንዲያደርሱ ይመቻቻል።
በሀምሌ ወር 2017 ዓ.ም ሁለት የምክክር መድረኮችን (ወርክሾፖች) በማዘጋጀት በጋብቻ በተሳሰሩ ጥንዶች መካከል ሊኖር ስለሚገባው መሠረታዊ የተግባቦት ሥርዓት በተለይም በባለትዳሮች መካከል ግጭትና አለመግባባት ስለሚፈታበት ሁኔታ እንዲሁም የማህበረሰብን ትስስር ማጎልበት በሚቻልበት ዙርያ በምሁራንና ልምድ ባካበቱ ጥንዶች የታገዘ ውይይት ይካሄዳል፡፡
ለ50 ዓመትና ከዚያ በላይ ትዳራቸውን በስኬት የመሩ 3 ጥንዶችን የጋብቻ ህይወት ተሞክሮ በመገናኛ ብዙሃን (በምስል/በፎቶ አውደርዕይ፣ በምስልወድምጽ/በቪዲዮ፣ በልዩ ልዩ ብዙሃን መገናኛ መንገዶች) አማካኝነት የህይወት ልምዳቸውን እንዲያካፍሉ በማድረግ ህብረተሰቡን ማስተማር፣ በጋብቻ ህይወት ለረጅም ዘመናት በፍቅርና በመከባበር የኖሩ የ5 ጥንዶችን ልምድ በመጽሄት፣ በምስል፣ በድምጽ/በቪዲዮ፣ በድረገጽ መጣጥፎች ይቀርባሉ።
📌 በርካታ ዓመት የቆዩ ባለትዳሮች የጠቆመ ይሸለማል፣ ጥንዶቹም ይሸለማሉ። ከዛሬ ጀምሮም ምዝገባ ይጀመራል ተብሏል።