ኢትዮፒካር መኪና አስመጪ ከአሚጎስ የገንዘብ ቁጠባ እና ብድር ህብረት ስራ ማህበር ጋር በመተባበር በኤሌክትሪክ የሚሰሩ መኪኖችን ለተጠቃሚዎች አስረከበ።
ዛሬ ሚያዚያ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ኢትዮፒካር መኪና አስመጪ ከአሚጎስ ቁጠባ እና ብድር ተቋም ጋር በገባው ስምምነት መሰረት የቁጠባ ተቋሙ ለ15 የኢትዮፒካር ደንበኞች ለሆኑ እና ቁጠባቸውን በአግባቡ ላጠናቀቁ ደንበኞች የኤሌክትሪክ መኪኖችን ርክክብ አድርጓል፡፡
አሚጎስ ከኢትዮፒካር ጋር ውል ከተዋዋለ ጊዜ አንስቶ ቅድመ ቁጠባውን ላሟሉ 100 ደንበኞች የኤሌክትሪክ መኪና ባለቤት አድርጓል፡፡ በቀጣይም እስከ 50 ለሚደርሱ ደንበኞች እስከ ሰኔ 30 ለማስረከብ እቅድ ተይዞ እየተሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል።
ኢትዮፒካር መኪና አስመጪ በቀጥታ ግዢ እንዲሁም በባንክ ብድር አማራጭ እየቀረቡ የሚገኙት የኤሌክትሪክ መኪኖች የፋብሪካ ዋስትና ያላቸው ሲሆን እስካሁንም ከ1000 በላይ ለሚሆኑ ፈላጊዎች ከባንክ እንዲሁም ከብድርና ቁጠባ የፋይናንስ ተቋማት ጋር ውል በመግባት መኪኖቹን አስረክቧል፡፡