የተወለደው ክርስቶስን ከሚጠሉ ከአንድ አህያ በቀር ምንም ከሌላቸው ድኆች አይሁዳውያን ቤተሰቦች ነው፡፡ ይባስ ብሎ በልጅነቱ አባቱ በመሞቱ ከእናቱና ከአንዲት እህቱ ጋር በረኃብ ሊያልቁ ሆነ፡፡ ሕጻኑ ኤጲፋንዮስ በአህያው እንዳይሠራ ክፉ ነበርና በእናቱ ምክር ሊሸጠው ገበያ ይዞት ሲጓዝም ፊላታዎስ ከሚባል ጻድቅ ክርስቲያን ጋር ተገናኘ፡፡ ሊገዛው ሲደራደሩም አህያው የኤጲፋንዮስን ኩላሊቱን ረግጦት ለሞት አደረሰው፡፡ በዚህ ጊዜ አብሮት ያለው ጻድቁ ክርስቲያን ፊላታዎስ በስመ ሥላሴ በትእምርተ መስቀል አማትቦ በቅፅበት አዳነው፡፡ አህያውንም ስለ እኛ በተሰቀለው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ትሞት ዘንድ ይገባሃል ሲለው አህያው ወዲያው ሞተ፡፡ ኤጲፋንዮስም ሁለቱን ተአምራት ካየ በኋላ “በስሙ ተአምራት የምታደርግበት የተሰቀለው ኢየሱስ ክርስቶስ ማነው?” አለው፡፡ ፊላታዎስም ክርስቶስን ሰበከለትና ኤጲፋንዮስ እያደነቀ ሄደ፡፡
ከወራት በኋላ ሀብታም አይሁዳዊ አጎቱ ኤጲፋንዮስን ወሰደውና ገንዘቡን ሁሉ አውርሶት ሞተ፡፡ ኤጲፋንዮስም ገና በ16 ዓመቱ ባለጸጋ ሆነ፡፡ የኦሪትን ሕግ ሁሉ እየተማረ ቢያድግም ያቺ ገበያ ላይ ያያት ተአምር ግን በልቡ ውስጥ ትመላለስ ነበር፡፡ በአንዲት ዕለትም ስሙ ሉክያኖስ ከሚባል ጻድቅ መነኩሴ ጋር ተገናኘ፡፡ አብረው ሲሔዱም አንድ ነዳይ አገኙና ምጽዋት ጠየቃቸው፡፡ ሉክያኖስም ገንዘብ ስለሌው የሚለብሰውን የጸጉር ዐፅፉን አውልቆ ለድኃው መጸወተው፡፡ በዚያን ጊዜ መላእክት የብርሃን ልብስ ከሰማይ አውርደው ሲያለብሱት ኤጲፋንዮስ ተመለከተ፡፡ ይህን ጊዜ ኤጲፋንዮስ ከመነኩሴው እግር ሥር ሰግዶ ክርስቲያን እንዲያደርገው ለመነው፡፡ መነኩሴውም ወስዶ ለኤጲስቆጶሱ ሰጠውና አስተምሮ አጠመቀው፡፡ መመንኮስም እንደሚፈልግ ቢነግረው ሀብት ንብረት እያለህ መነኩሴ መሆን አይገባህም አሉት፡፡
ኤጲፋንዮስ እኅቱን አምጥቶ አስጠመቃትና ገንዘቡን ሁሉ ሸጦ ለድኆችና ጦም አዳሪዎች መጸወተው፡፡ በተረፈው ደግሞ ቅዱሳት መጻሕፍትን ገዛቶ መነኮሰና ለእርሱም ለእኅቱም ለጥምቀት ምክንያት ወደሆነው ሉክያኖስ ወደተባለው መነኮስ ገዳም ገና በ16 ዓመቱ ገባ፡፡ በዚያም ከሽማግሌውን አባ ኢላርዮስን ሕግጋትን ሁሉ ተማረ፡፡ መናንያኑ እስኪያደንቁት ድረስም በፍጹም ትጋትና ቅድስና በተጋድሎ ኖረ፡፡ በርካታ ድንቅና ተአምራትንም አደረገ፡፡ ድውያንን ፈወሰ፣ በጸሎቱ ሙታንን አስነሣ፣ ከደረቅ መሬት ላይ ውኃን አፈለቀ፡፡ ያለጊዜውም ዝናም አዘነመ፡፡ ብዙ አይሁዶችንም ተከራክሮና በተአምሩ እያሳመነ አጠመቃቸው፡፡ ከዚህም በኋላ መምህሩ ኢላርዮስ በነገረው ትንቢት መሠረት በቆጵሮስ ደሴት ላይ ጳጳስ ሆኖ ተሾመ፡፡ ብሉይን ከሐዲስ የወሰነ እጅግ ምጡቅ ሊቅ ነውና ብዙ መጻሕፍትን ተረጎመ፡፡
ሃይማኖተ አበው ዘኤጲፋንዮስ፣ መጽሐፈ ቅዳሴውንና ስነ ፍጥረትን በዝርዝር የሚተነትነውን መጽሐፈ አክሲማሮስን ጨምሮ በሺሕ የሚቆጠሩ ድርሳናትን ደረሰ፡፡ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ በአፍም በመጽሐፍም እየጠቀሰ መናፍቃንንና አይሁድን ምላሽ በማሳጣቱ ሊቃውንት የቤተ ክርስቲያን ጠበቃ ይሉታል።፡ የከበረና የተመሰገነ ሊቁ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ በመልካም እረኝነትና በሚደነቅ ቅድስና ሲያገለግል ኖሮ ግንቦት 17 406 ዓ.ም ዐርፏል፡፡ ታላላቅ የቅድስና ማዕረጋት ላይ የደረሱ ቅዱሳን አባቶችና እናቶች ያላቸውን ሁሉ ሸጠው ለድሆች በመመጽወት ዓለምን ትተው ጋታችንን ተከትለውታልና ጸሎታቸው ኃይልን ታደርጋለች። ገዳማቸውን ስንደግፍ በዓታቸውን ስናጸና የበረከታቸው ተሳታፊ እንደምለን። የቅዱስ ኤጲፋንዮስ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444