ሎተሪ የደረሳቸው በማስመሰል ከአንዲት ግለሰብ ላይ ከ70 ሺህ ብር በላይ ያጭበረበረን ግለሰብ ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ፡፡
ወንጀሉ የተፈፀመው ሚያዚያ 20 ቀን 2017 ዓ/ም በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ልዩ ቦታው አርሴማ ክሊኒክ እየተባለ ከሚጠራ ስፍራ ነው፡፡ አንድ በእድሜያቸው ገፋ ያሉ ሽማግሌ ወደ ግል ተበዳይ በመቅረብ ሎተሪ ቆርጠው 75 ሚሊዮን ብር እንደደረሳቸው ነገር ግን ሽልማቱን ለማውጣት አዲስ አበባ ዘመድ እንደሌላቸው ለሌሎች ሰዎች ቢናገሩ ሎተሪውን እንደሚወስዱባቸው መጠራጠራቸውን በመንገር ሽልማቱን ለማውጣት እንድትረዳቸው ይጠይቋታል፡፡
ሽልማቱ የሚሰጠው ልደታ አካባቢ መሆኑን ገልፀውላት በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 1 አ/አ 30405 ተሳፍረው ይመጣሉ፡፡ ብሩንና ሽልማቱን እሷ እንድታወጣ ሽማግሌውና አሽከርካሪው ካግባቧት በኋላ ለመተማመኛ የሚሆን ብር ወይም ንብረት እንደትሰጣቸው ይጠይቋታል፡፡
የግል ተበዳይ ክፍለ ሀገር ከሚገኙ ወላጅ አባቷ በባንክ 50 ሺህ ብር አስልካ በእጇ ላይ ያለውን 6ሺ ብር ጨምራ በጥሬ 56ሺ ብር፣ ግምቱ 15 ሺህ ብር የሚያወጣ ሞባይል ስልክ እና 5ሺ ብር የሚገመት ሀብል በአጠቃለይ 76 ሺ ብር በጥሬ 56ሺ ብር እና 20ሺ ብር ዋጋ ያላቸውን ንብረት ትሰጣለች፡፡
አጭበርባሪዎቹ ገንዘቡንና ንብረቱን ከተቀበሉ በኋላ በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ልዩ ቦታ አርሴማ ክሊኒክ አካባቢ ወደሚገኝ ህንፃ ገብታ ሽልማቱን እንድትረከብ ይልኳታል፡፡ ህፃው ላይ ያሉ ሰዎችን ስትጠይቅ ውሸት መሆኑን ሲገልፁላት ወደ ወረደችበት መኪና ብትሄድ ሰዎቹን በቦታው የሉም፡፡
ጉዳዩ በልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ጦር ኃይሎች አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ይደሰርሳል፤ ፖሊስ ባደረገው ክትትል እና በልዩ ልዩ መንገድ ያሰባሰበውን መረጃ መነሻ በማድረግ ወንጀሉን ከፈፀሙት መካከል ሹፌሩን ከእነ ተሽከርካሪው በቁጥጥር ስር ማዋል ችሏል፡፡ ግለሰቡም አንድ ሽጉጥ ከሦስት ጥይት ጋር ይዞ መገኘቱን ፖሊስ አስታውቋል፡፡
አንደኛውን ተጠርጣሪ ለመያዝ ፖሊስ ክትትሉን መቀጠሉን ገልፆ ወንጀል ፈፃሚዎቹ አሳዛኝ እና ሽማግሌ መስለው በመቅረብ ሎተሪ ደርሷቸው መታወቂያ ስለሌላቸው ወይም የአዲስ አበባ ነዋሪ ባለመሆናቸው ሽልማቱን ለማውጣት እንደተቸገሩ በማስመሰል የማታለል ወንጀል እንደሚፈፅሙ ህብረተሰቡ ተገንዝቦ ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባ ፖሊስ መልእክቱን አስተላፏል፡፡