ቅዱስ ገብርኤል የልባችሁን መልካም መሻት ይሙላላችሁ!!!
በያለንበት ጸንተን እንቁም!
ነቢዩ ዳንኤል የመላእክት አለቃ የቅዱስ ገብርኤልን አስፈሪ ግርማ በተመለከተ ጊዜ “ዐይኖቼንም አነሣሁ “እነሆም በፍታ የለበሰውን ጥሩም የአፌዝን ወርቅ በወገቡ ላይ የታጠቀውን ሰው አየሁ፡፡ አካሉም እንደ ቢረሌ ይመስል ነበር፤ ፊቱም እንደ መብረቅ አምሳያ ነበረ፤ ዐይኖቹም እንደሚንበለበል ፋና፣ ክንዶቹና እግሮቹም እንደ ጋለ ናስ፣ የቃሉም ድምፅ እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ ነበረ፡፡ ይህንም ታላቅ ራእይ አየሁ፤ ኀይልም አልቀረልኝም፤ ክብሬም ወደ ውርደት ተለወጠብኝ ኀይልም አጣሁ፡፡ የቃሉንም ድምፅ ሰማሁ፤ የቃሉን ድምፅ በሰማሁ ጊዜ ደንግጬ በምደር ላይ በግምባሬ ተደፋሁ” አለ፡፡ በዳንኤል 10÷5-9 የተገለጸው የዚህ መልአክ ግርማ የአምላክን ግርማ ይመስላል፡፡ ቅዱስ ገብርኤል የስሙ ትርጓሜ “አምላክ ወሰብእ” ሰውና አምላክ ማለት ሲሆን ከዋነኞቹ የመላዕክት አለቆች አንዱ ነው፡፡
ቅዱስ ጳውሎስም በቈላስያስ 1÷16 በቅዱሳን መላእክት ዘንድ ስላሉት ነገዶች ሲገልጽ “… በሰማይ ያለውን በምድር ያለውን የሚታየውንምና የማይታየውን መናብርትም ቢሆኑ አጋእዝትም ቢሆኑ መኳንንትም ቢሆኑ ቀደምትም ቢሆኑ ሁሉም በእጁ ሆነ፤ ሁሉም በእርሱ ለእርሱ ተፈጠረ” በማለት ነገደ መላዕክትን ይዘረዝራቸዋል፡፡ ቅዱስ ገብርኤልም ከእነዚህ ዐበይት የመላእክት ነገዶች መካከል አንዱ በሆነው አርባብ፣ አጋእዝት ወይም ጌቶች በሚባለው ዐቢይ ነገድ ላይ የተሾመ ሲሆን ከበታቹም የሚመራቸው ዐሥር ነገደ መላእክት አሉ፡፡ ቅዱሳን መላእክት በቅዱስ ሚካኤል ፊት አውራሪነት የሰው ልጆች ጠላት ዲያብሎስን ተዋግተው ድል ከመንሳታቸው አስቀድሞ ቅዱስ ገብርኤል እንደ አምላክ ሊመለክ የወደደውን ሳጥናኤልን በመቃወም“ አይዞአችሁ ፈጣሪያችን ፈጥሮ አይጥለንምና አስክናገኘው፣ እስክናውቀው ድረስ በያለንበት እንቁም፡፡” በማለት መላእክትን ያረጋጋ መልአክ ነው፡፡
ነቢዩ ኢሳይያስ በምዕራፍ 14÷16 በሰማያት የሳጥናኤል ትዕቢትና ውድቀት ምን እንደሚመስል ሲጽፍልን “አንተ በንጋት የሚወጣ አጥቢያ ኮከብ ሆይ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ! ወደ አሕዛብ መልእክትን የላክ አንተ ሆይ እንዴት እስከ ምድር ድረስ ተቀጠቀጥህ! አንተም በልብህ ወደ ሰማይ ዐርጋለሁ ዙፋኔንም ከእግዚአብሔር ከዋክብት በላይ ከፍ ከፍ አደረጋለሁ፤ በልዑልም እመሰላለሁ አልህ፡፡ ዛሬ ግን ወደ ሲኦል ትወድቃለህ፤ ወደ ምደር ጥልቅም ትወርዳለህ” ይለናል፡፡ ቅዱስ ገብርኤል በቅድስና ሕይወት ለተጋውና በገዢዎች ዘንድ የእግዚአብሔር ቅዱስ መንፈስ ያደረበት ሰው ተብሎ ለተመሰገነው ለነቢዩ ዳንኤል ማስተዋልንና ጥበብን የሰጠ፣ እግዚአብሔር አምላክ የሰው ልጆችን ከሰይጣንና ከሞት ባርነት ነጻ ሊያወጣቸው ሰው እንደሚሆንና ሰማይንና ምድርን አሳልፎ በቅዱሳን ላይ ነግሦ እንደሚኖር በምሳሌ ገልጾ ያስተማረው መልአክ ነው፡፡
ቅዱስ ገብርኤል ቅዱሳንን ለእግዚአብሔር በመገዛታቸው ምክንያት ከአላውያን ገዢዎች ከሚደርስባቸው መከራም የሚታደጋቸው መልአክም ነው፡፡ ሦስቱ ሕጻናት አናንያ አዛርያና ሚሳኤል ለጣኦት አንሰግድም ባሉ ጊዜ በንጉሥ ናብከደነፆር ወደ እቶን እሳት ሲጣሉ እስራታቸውን ፈቶ፣ እሳቱን እንደ ውኃ አቀዝቅዞ ያዳናቸው ቅዱስ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣንም ከእሳት ያወጣ እርሱ ነው፡፡ የቅዱስ ገብርኤል ምልጃና ጸሎት ይጠብቀን፡፡ ዛሬም ይህን አማላጅነቱንና ፈጣን ተራዳኢነቱን ያመኑ ገዳማውያ አባቶች በጸሎታቸው ይጠሩታል እርሱም ይራዳቸዋል፡፡ እኛም ገዳማቸውን ስንደግፍ በዓታቸውን ስናጸና የበረከታቸው ተሳታፊ እንሆናለን፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444