ፍኖተ ሳዊሮስ መንፈሳዊ ማኅበር


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана



Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


ፆመ ፍልሰታ
(ጾመ ፍልሰታ) ፍልሰታ ፆም(ጾመ ለማርያም) ሞት በጥር በነሀሴ መቃብር የፍልሰታ ፆም ከነሀሴ 1እስከ15 ነው ቤተ ክርስትያናችን እደሚገለፀው "እመቤታችን ያረፈችው ጥር 21ቀን ነው ሐዋርያት በድኗን ሊቀብሯት ወደ ጌቴሰማኒ ይዘዋት ሲሄዱ አይሁድ አይተዋቸው በተኗቸው በዚህ ጊዜ መላእክት የእመቤታችንን አስክሬን ወስደው በገነት አኑረውታል በ8ወር በነሀሴ ሐዋርያት አስክሬኗን እንደገና ከጌታ ተቀብለው በፀሎትና በምህላ ቀብረዋታል በዚህ የቀብር ስነስርዓት ላይ ከ12 ሐዋርያት አንዱ ቶማስ አልነበረም

ቅዱስ ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ በደመና ተጭኖ ወደ እየሩሳሌም ሲመጣ ያገኛታል በዚህ ጊዜ ትንሳኤዋን ሌሎች ሐዋርያቶች አይተው ለእሱ የቀረበት መስሎት ተናዶ በፊት የልጅሽን ትንሳኤ ሳላይ ቀረው አሁን ደግሞ የአንቺን ትንሳኤ ሳላይ ቀርቼ ነበር ብሎ ከደመና ሊወረወር ቃጣው በዚህ ጊዜ እመቤታችን ቶማስን አፅናንታ ከእሱ በቀር ሌላ ትንሰኤዋን እንዳላየ ነገረችው

ቶማስም ሐዋርያት ወዳሉበት እየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ እመቤታችንን ቀበርናት ብለው ነገሩት እሱም አውቆ ምስጥሩን ደብቆ አይደረግም ሞት በጥር በነሀሴ መቃብር አላቸው ለማሳየትም መቃብር ሲከፍቱ አጧት በዚህ ጊዜ"እመቤታችን ተነስታ አርጋለች ብሎ ሁኔታውን ተረከላቸው ለምስክርም ይሆናል ብሎ የሰጠችውን (ሰበኗን) አሳያቸው

ሰበኗንም ለበረከት ቆራርጠው ተከፋፍለው ወደ ሀገረ ስብከት ተበታትነዋል በዓመቱ ትንሳዬሽን ቶማስ አይቶ እንዴት እኛ ይቅርብን ብለው ከነሀሴ 1 ጀምሮ ሱባዬ ገቡ በነሀሴ14ቀንም ትኩስ በድን አድርጕ አምጥቶ ሰጣቸው ከቀበሯትም በጟላ በነሀሴ16 ተነስታለች በዚህ ቀን ጌታ ቀድሶ እመቤታችንም በልጇ እጅ ቆርባለች ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የሐዋርያት ቤተክርስትያን የእመቤታችንን በረከት ለማግኘት ይህች ጊዜ ትፆማለች

የእመቤታችን በረከቷ አማላጅነቷ ከሁላችንም ጋር ይሁን እናትነቷ ይብዛብን አሜን መልካም የፍልሰታ ፆም ይሁንልን ሀገራችንን ሰላም ታድርግልን አሜን


💛 @fnotesawiros 💛


ምንተ ንነግረኪ ውስተ ልብነ ዘሀሎ
እስመ አንቲ ተአምሪ ኀዘንነ ኩሎ
(በልባችን ካለው ምኑን እንነግርሻለን
አንቺው ኀዘናችንን ሁሉ ታውቂዋለሽ)

ጾመ ፍልሰታ ሐዋርያት የእመቤታችንን ሥጋዋን ሽተው የጾሙት ጾም በኁዋላም ትንሣኤዋን ያዩበት ጾም ነው::
ዘንድሮ የምንጾመው ከብዙ ብሶትና ኀዘን ጋር ነው:: እመቤታችንን ሐዋርያት ሥጋዋን ይዘው ሊቀብሩ ባሉ ጊዜ አይሁድ የላኩት አንድ ታውፋንያን ነበር:: ዘንድሮ የሰማዕታት አስከሬን ላይ የሚሆነው ታውፋንያ ምን አደረገ የሚያስብል ሆነብን:: ወላዲተ አምላክ የልባችንን ኀዘን ለማን እንነግራለን? ከአንቺ በቀር ማን ያጽናናል?
ዘንድሮ ፍልሰታን ከሞቀ ቤታቸው ፈልሰው በደጅ ፈስሰው
በዚህ አጥንት የሚሰብር ብርድ ከደጅ የሚያድሩ ሱባኤያተኞችሽን ተመልከቺ:: በልጅሽ ያመኑ ባለማተቦችሽን እመብርሃን ሆይ ተመልከቺ::
ከአንቺ በቀር የልባችን ኀዘን ለማን እንነግራለን?
ሱባኤያችንን የኢትዮጵያ ሰላም የቤተ ክርስቲያን ዕረፍት የኃጢአታችን ሥርየት ሱባኤ አድርጊልን::
በጾመ ፍልሰታ ንስሓ እንግባ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን እንቀበል::

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

@fnotesawiros


ቅዱስ ኤፍሬም የእመቤታችን ምስጋና እንደ ሰማይ ኮከብ እንደ ባሕር አሸዋ በዝቶልኝ፣ እንደ ምግብ ተመግቤው፣ እንደ ውሓ ጠጥቼው፣ እንደ ልብስ ተጎናጽፌው ምነው በኖርኩ እያለ ሲመኝ ይኖር ነበር።

መንፈስቅዱስም የተመኙትን መግለጽ ልማዱ ነውና ገልጾለት ፻፻ ከ፬ ሺህ ድርሰት ደርሷል “አኃዝ እግዚኦ መዋግደ ጸጋከ” እስኪል ድረስ። ከዕለታት በአንዱ ቀን ዕለተ ሠኑይ ጊዜው ነግህ ነው። የነግህ ተግባሩን አድርሶ ከመካነ ግብሩ ተቀምጦ ሳለ እመቤታችን ትመጣለች የብርሃን ምንጣፍ ይነጠፋል፣ የብርሃን ድባብ ይዘረጋል፣ ከዚያ ላይ ሆና “ሰላም ለከ ኦ ፍቁርዬ ኤፍሬም” ትለዋለች።እሱም ታጥቆ እጅ ነስቶ ይቆማል። “ወድሰኒ” ትለዋለች “እፎ እክል ወድሶተኪ ዘኢይክሉ” ፣“ሰማያውያን ወምድራውያን ምድራውያን ጻድቃን ሰማያውያን መላእክት አንችን ማመስገን የማይቻላቸው ለኔ እንደምን ይቻለኛል” አላት “በከመ አለበወከ መንፈስቅዱስ ተናገር” አለችው። በተረቱበት መርታት ልማድ ነውና “እፎኑ ይከውነኒ እንዘ ኢየአምር ብእሴ” ብትለው መልአኩ “መንፈሰ እግዚአብሔር ቅዱስ ይመጽእ ላዕሌኪ” ብሏት ነበር። ከዚህ በኋላ ባርክኒ ይላታል በረከተ ወልድየ ወአቡሁ ወመንፈስቅዱስ ይኅድር በላዕሌከ ትለዋለች። ተባርኮ ምስጋናዋን ይጀምራል።

ምንጭ፦ውዳሴ ማርያም ትርጓሜ
እንኳን ለጾመ ፍልሰታ በሰላም አደረሳችሁ!

@fnotesawiros


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

ሐምሌ 26

አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን

ቅዱሱ በትውልዳቸው ግሪካዊ ቢሆኑም ሶርያ አካባቢ እንዳደጉ ይታመናል:: በቀደመ ስማቸው ፍሬምናጦስ የሚባሉት አቡነ ሰላማ ወደ ኢትዮዽያ የመጡት በአደጋ ምክንያት (በድንገት) ቢመስልም ውስጡ ግን ፈቃደ እግዚአብሔር ነበረበት::

በድንበር ጠባቂዎች (በአደጋ ጣዮች) ከባልንጀራቸው ኤዴስዮስ ጋር ተይዘው ወደ አክሱም የመጡት በንጉሥ ታዜር (አይዛና) እና በሚስቱ ሶፍያ (አሕየዋ) ዘመን ነው:: ጊዜው በውል ባይታወቅም በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው::

ፍሬምናጦስ ምንም የመጡበት ዓላማ ስብከተ ወንጌል ባይሆንም በአክሱም ቤተ መንግስት አካባቢ ይሰበኩ ነበር:: ያን ጊዜ በጃንደረባው ቅዱስ ባኮስ የተቀጣጠለው የክርስትና ችቦ ውስጥ ውስጡን በሃገሪቱ ነበረና ፍሬምናጦስ አልተቸገሩም:: በተለይ ሕጻናቱን (ኢዛናና ሳይዛናን) ገና ከልጅነት ስላስተማሯቸው ነገሮች የተሳኩ ሆኑ::

ልክ ንጉሥ ታዜር እንደ ሞተ ሁለቱ ሕጻናት በመንበሩ ተቀመጡ:: ፍሬምናጦስንም ወደ ግብፅ ዻዻስና ጥምቀት ከመጻሕፍት ጋር እንዲመጣላቸው ላኩ:: ሐዋርያዊ ቅዱስ አትናቴዎስም ፍሬምናጦስን "ሰላማ" ብሎ ሰይሞ : ጵጵስና : በንዋየ ቅድሳትና በመጻሕፍት ሸልሞ መለሳቸው::

አቡነ ሰላማ ወደ ኢትዮዽያ እንደተመለሱ ከነገሥታቱ ጀምረው ለሕዝቡ ጥምቀትን አደሉ:: ኢዛናና ሳይዛናም አብርሃ (አበራ) እና አጽብሃ (አነጋ) ተብለው ስማቸው ተደነገለ:: ከዚያ በሁዋላ ድንቅ በሚሆን አገልግሎት ነገሥታቱ : ዻዻሱ ሰላማና ሊቀ ካህናቱ እንበረም ለክርስትና መስፋፋት በጋራ ሠርተዋል::

የአቡነ ሰላማ ትሩፋቶች:-
1.ጵጵስናና ክህነትን ከእውነተኛ ምንጭ አምጥተዋል::
2.ክርስትናና ጥምቀትን በሃገራችን አስፋፍተዋል::
3.ቅዱሳት መጻሕፍትን ከውጭ ልሳኖች ተርጉመዋል::
4.ገዳማዊ ሕይወትን ጀምረዋል::
5.አብያተ ክርስቲያናትን አንጸዋል::
6.ግዕዝ ቋንቋን አሻሽለዋል::
ሀ.ከግራ ወደ ቀኝ እንዲፃፍ
ለ.እርባታ እንዲኖረው
ሐ.ከ"አበገደ" ወደ "ሀለሐመ" ቀይረዋል::
ባላቸው ንጹሕ የቅድስና ሕይወት ለሕዝቡ ምሳሌ ሆነዋል::
"ወበእንተዝ ተሰይመ ከሳቴ ብርሃን" እንዲል ገድላቸው በነዚህ ምክንያቶች "ከሣቴ ብርሃን" (ብርሃንን የገለጠ) ሲባሉ ይኖራሉ:: በመጨረሻም ከመልካሙ ገድል በሁዋላ በ352 ዓ/ም ዐርፈው ተቀብረዋል::

ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ

በሐዲስ ኪዳን መጀመሪያ አካባቢ ስም አጠራራቸው ከከበረ ደጋግ እሥራኤላውያን አንዱ የእመቤታችን ጠባቂ ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ ነው:: ትውልዱ ከነገደ ይሁዳ ሲሆን አባቱ ያዕቆብ ይሰኛል::

በጉብዝናው ወራት የእመቤታችንን አክስት ማርያምን አግብቶ ብዙ ልጆችን ወልዶ አርጅቷል:: ከልጆቹም ዮሳ: ያዕቆብ: ይሁዳ: ስምዖን እና ሰሎሜ በቅዱስ መጽሐፍ ተዘክረዋል:: ቅዱስ ዮሴፍ እድሜው 75 ሲሆን ሚስቱ ማርያም ሞተችበት::

ከጥቂት ወራት በሁዋላም በመንፈስ ቅዱስ ድንግል ማርያምን ሊያገለግል ተመረጠ:: "እጮኛ" የሚለውም ለዛ ነው:: (ለአገልግሎት ነው የታጨው) እመቤታችን ለአረጋዊ ዮሴፍ በ2 ወገን ልጁ (ዘመዱ) ናት::
1.የሚስቱ ማርያም የእህት (የሐና) ልጅ ናት::
2.የቅድመ አያቱ የአልዓዛር የልጅ ልጅ ናት::

ደጉ ሽማግሌ ቅዱስ ዮሴፍ ምን ቢያረጅ እመቤታችንን ለማገልገል አልደከመውም:: አብሯት ተሰደደ:: ረሃብ ጥማቷን: ጭንቅና መከራዋን: ሐዘንና ችግሯን ተካፍሏል:: ከእመ ብርሃንና አምላክ ልጇ ጋር ለ16 ዓመታት ኑሯል::

ከእነዚህ ዘመናት በሁዋላም በ16 ዓ/ም : በተወለደ በ91 ዓመቱ ሲያርፍ ጌታችን "ሥጋሕ አይፈርስም" ብሎ ቃል ኪዳን ገብቶለታል::
"ኢየሱስ ክርስቶስ በከመ አሠፈዎ ኪዳነ::
ኢበልየ በመቃብር ወኢሂ ማሰነ::
እስከ ዮም በድኑ ሐለወ ድኁነ::" እንዳለ መጽሐፈ ስንክሳር::

ቅዱስ ጢሞቴዎስ ዘአልቦ ጥሪት

ይህ ቅዱስ አባት በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን የእስክንድርያ ፓትርያርክ የነበረ አባት ነው:: ዘመነ ሲመቱም ከ377 እስከ 387 ድረስ ለ10 ዓመታት ነው:: በእነዚህ ዘመናቱ "ዘአልቦ ጥሪት" (ገንዘብ የሌለው / ነዳዩ አባት) ነበር የሚባለው:: ገንዘብንና ዓለምን የናቀ አባት ነበር::

ቅዱስ ጢሞቴዎስ የቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ደቀ መዝሙር እንደ መሆኑ ከመንፈሳዊ አባቱ መልካም ሕይወትን ወርሷል:: ምሥጢራትንም አጥንቷል:: በዘመኑ የአርዮስ ውላጆች ቤተ ክርስቲያንን ያስቸግሩ ነበርና ከእነርሱ ጋር ተዋግቷል:: ምዕመኑንም ከተኩላዎች ይጠብቅ ዘንድ ተግቷል::

በ381 ዓ/ም በቁስጥንጥንያ ጉባዔ በተደረገ ጊዜ ማሕበሩን በሊቀ መንበርነት መርቷል:: ለመቅዶንዮስ : ለሰባልዮስና ለአቡሊናርዮስ ኑፋቄዎችም ተገቢውን ምላሽ ሰጥቶ አውግዟል:: ቅዱስ ጢሞቴዎስ ዘአልቦ ጥሪት በቅድስና ተመላልሶ በ387 ዓ/ም በዚህች ቀን ዐርፏል::

ፈጣሪአቡነ ሰ ከላማ : ከአረጋዊ ዮሴፍና ከቅዱስ ጢሞቴዎስ በረከትን ያሳትፈን::

ሐምሌ 26 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን
2.ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ (የድንግል ማርያም ጠባቂ)
3.ቅዱስ አባ ጢሞቴዎስ (ዘአልቦ ጥሪት)
4.አባ ሮዲስ

ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
2.አቡነ ሐብተ ማርያም ጻድቅ
3.አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ
4.ቅዱሳን ሰማዕታተ ናግራን

"እናንተ የምድር ጨው ናችሁ . . . እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ:: በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሠወር አይቻላትም:: መብራትንም አብርተው በዕንቅብ በታች አይደለም እንጂ በመቅረዙ ላይ ያናሩታል:: በቤት ላሉት ሁሉም ያበራል:: መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ::"
(ማቴ. 5:13-16)

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

ሐምሌ 25

ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕተ ሮሜ

ቅዱሱ ከቀደምት ሰማዕታት አንዱ ሲሆን በ200 ዓ/ም አካባቢ እንደ ተወለደ ይታመናል:: ወላጆቹ ከጣዖት አምልኮ ወደ ክርስትና የመጡት በተአምር ነው:: ስማቸውም #ታቦትና_ኖኅ ይባላሉ:: ቅዱሱ መጀመሪያ " #ፒሉፓዴር" ይባል ነበር:: ትርጉሙ "የአብ ወዳጅ" እንደ ማለት ነው::

ቀጥሎም " #መርቆሬዎስ" ተብሏል:: ይኸውም " #የኢየሱስ_ክርስቶስ_አገል ጋይ" እንደ ማለት ነው:: በጦርነት ኃይለኛ: በመልኩ ደመ ግቡና ተወዳጅ የነበረው ቅዱስ መርቆሬዎስ ስለ ክርስትናው መከራን የተቀበለው በ20 ዓመቱ ነው:: ዘመኑም በዳኬዎስ ቀዳማዊ ነው::

ስለ ሃይማኖቱም ለ5 ዓመታት መከራን ታግሦ በ25 ዓመቱ (ማለትም በ225 ዓ/ም) ሕዳር 25 ቀን አንገቱን ተከልሏል:: በዓለማቀፍ ደረጃም ቅዱስ መርቆሬዎስ ክብሩ ከሊቀ ሰማዕታት ቀጥሎ የሚገኝ ነው::

በተለይ ዛሬ ሐምሌ 25 ቀን ቅዳሴ ቤቱ ሲሆን ቤቱ በታነጸበት ሁሉ ተአምራትን ያደርጋል:: ስለዚህ ነገር ታሪክ ብቻ ሳይሆን እኛ ኃጥአንም ምስክሮች ነን:: ጋሹ አምባን ጨምሮ ዛሬም ቅዱሱ ድንቆችን ይሠራል::

ቅዱስ ኄኖክ ነቢይ

ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ኄኖክ
ከአባታችን አዳም 7ኛው ደግ ሰው ሲሆን አባቱ #ያሬድ ይባላል:: በእርግጥ ቅዱሱ ሚስት አግብቶ #ማቱሳላና ሌሎች ልጆችን ወልዷል:: አካሔዱ ግን ከእግዚአብሔር ጋር ነበርና ሞትን አላየም::

ነቢዩ ኄኖክ በ1486 ዓ/ዓ የመጀመሪያውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ( #መጽሐፈ_ኄኖክን) ጽፏል:: የዚሕ መጽሐፍ ባለቤት ደግሞ ሃገራችን ናት:: ቅዱሱ ብዙ ሰማያዊ ምሥጢሮችን ተመልክቷል::

የእርሱ ሞትን አለመቅመስ በአቤል ሞት የፈሩትን ውሉደ አዳም በተስፋ አነቃቅቷቸዋል::
"በአቤል አፍርሆሙ:
ወበኄኖክ አንቅሆሙ" እንዳለው ሊቁ:: (ዘፍ. 5:24, ኄኖክ. 4:1)

ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት

እናታችን ቅድስት ቴክላ በኒቆምድያ ተወልዳ ያደገች: ከአሕዛባዊ እምነት ወደ ክርስትና በሐዋርያው ቅዱስ ዻውሎስ አማካኝነት የመጣች እናት ናት:: እርሷ ክርስትናን ከልብ ለሚሹ ሴቶች ሁሉ መሪና ትልቅ ት/ቤት ናት:: ወንጌልን ከሐዋርያው ስትማር ምሥጢሩ እየመሰጣት አንዳንዴ ለ3 ቀናት ምግብ አትቀምስም ነበር::

እጅግ ቆንጆ ወጣትና የሃብታሞች ልጅ ብትሆንም ስለ ክርስቶስ ሁሉን ለመናቅና መስቀሉን ለመሸከም አልተቸገረችም:: ከኒቆምድያ እስከ አንጾኪያ ወንጌልን ሰብካለች:: ወላጆቿን ጨምሮ ብዙ ነፍሳትን አድናለች:: በፈንታውም ብዙ መከራን ተቀብላ በዚህ ቀን ዐርፋለች:: ቤተ ክርስትያን " ሐዋርያዊት" ብላ ታከብራታለች::

ቅዱስ አበከረዙን ጻድቅ ወሰማዕት

ስም አጠራሩ የከበረ ታላቁ አባ አበከረዙን ወደ ክርስትና የተጠራው ከሽፍታነት (ስርቆት) ሕይወት ነው:: ከአጋሮቹ ጋር ገዳም ለመዝረፍ ሒደው አንድ ባሕታዊ ከማታ 12:00 እስከ ጧት 12:00 ሲጸልይ አይተው ተጸጽተው ንስሃ ገብተዋል::

አበከረዙን ግን ዓለምን ንቆ በምናኔ ለ7 ዓመታት ተጋድሏል:: ነገር ግን ሰማዕት ለመሆን ከነበረው ፍቅር የተነሳ ከገዳም ወደ ከሃድያን ነገሥታት ሃገር ሔዶ ስመ ክርስቶስን ሰብኩዋል:: በእርሱ ላይ ከደረሱ ስቃዮች ብዛት የተነሳ ከሥጋው: ከአጥንቱና ከደሙ የተረፈለት የለም::

እንዲያውም አንዴ በዓየር ላይ ዘቅዝቀው ሰቅለው ደሙ በአፍና በአፍንጫው እየጐረፈ ለ10 ቀናት ቆይቷል:: በወቅቱ የመኮንኑ ሴት ልጅ እየመጣች ያለ ርሕሪሔ ታሰቃየው ነበርና እርሷን መልአክ ወርዶ ቀሥፎ ገደላት::

እርሱ በተሰቀለ በ22ኛው ቀን: እርሷ በተቀበረች በደግሞ በ12ኛው ቀን ከተሰቀለበት አውርደውት ከሞት አስነስቷታል:: ታላቁ አበከረዙንን በዚህች ቀን ብዙ አሰቃይተው: ወገቡን ሰብረው: አንገቱንም ሰይፈው ገድለውታል::

ቅዱስ ዱማድዮስ ሶርያዊ

ለቤተ ክርስቲያን
በንጹሕ ሕይወታቸው ካበሩላት ዐበይት ቅዱሳን አንዱ ቅዱስ ዱማድዮስ ነው:: እርሱ ወደ ክርስትና የመጣው ከባዕድ አምልኮ ሲሆን መሪው መንፈስ ቅዱስ ነው:: ጣዕመ ሕይወቱን ሲሰሙት ዕዝነ ልቡናን ደስ ያሰኛል::

ገና በወጣትነቱ እንደ ሐዋርያት ሰብኮ አሕዛብን አሳምኗል:: እንደ ጻድቃን አካሉ አልቆ አጥንቶቹ እስኪታዩ ተጋድሏል:: እርሱ ድንግል: ንጹሕ: መነኮስ: ባሕታዊና ካህን ነው:: ግን ውዳሴ ከንቱን አምርሮ ይጠላል:: በዚህ ምክንያት ካደረበት አይውልም: ከዋለበትም አያድርም::

እርሱ በጸሎቱ የተዘጉ ማሕጸኖችን ከፍቷል:: ዕውራንን አብርቷል:: ለምጻሞችን አንጽቷል:: አንካሶችን አርትቷል:: በፈጣሪው ኃይል ፈሳሽ ወንዝን አቁሟል:: እንደ ገናም እንደ ነበረው መልሶታል::

የቅዱስ ዱማድዮስ መጨረሻው ደግሞ ሰማዕትነት ነው:: በበዓቱ ውስጥ ሳለ ከደቀ መዝሙሩ ጋር ክፉዎች በድንጋይ ወግረው ገድለውታል:: ድንጋዩም የኮረብታ ያህል ነበር:: ልክ በዓመቱ በዚህች ዕለት ምዕመናን ሥጋውን አፍልሠዋል::

ቸር አምላክ ከነቢያት: ሐዋርያት: ጻድቃንና ሰማዕታት ክብርን ያሳትፈን::

ሐምሌ 25 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕት (ቅዳሴ ቤቱ)
2.ቅዱስ ኄኖክ ነቢይ (ዕርገቱ)
3.ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት
4.ቅዱስ አበከረዙን ታላቁ (ጻድቅና ሰማዕት)
5.ቅዱስ ዱማድዮስ ሶርያዊ (ጻድቅና ሰማዕት)
6.ቅድስት ኢላርያ ሰማዕት
7.ቅዱሳት ቴክላ ወሙጊ ሰማዕታት
8.ቅዱስ እንዲኒና ሰማዕት
9.አባ ይስሐቅ ሰማዕት
10.አባ ሕጻን ሞዐ ዘደብረ ሊባኖስ
11."25,000" ሰማዕታት (የአትሪብ /ግብፅ/ ሰዎች)

ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ይሁዳ ሐዋርያ (ከ72ቱ አርድእት)
2.አቡነ አቢብ (አባ ቡላ)
3.ቅዱስ አባ አቡፋና ጻድቅ

"እግዚአብሔር ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ: እስከ አሁንም ስለምታገለግሏቸው ያደረጋችሁትን ሥራ: ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዓመጸኛ አይደለምና:: በእምነትና በትእግስትም የተስፋውን ቃል የሚወርሱትን እንድትመስሉ እንጂ ዳተኞች እንዳትሆኑ ተስፋ እስኪሞላ ድረስ እያንዳንዳችሁ ያን ትጋት እስከ መጨረሻ እንድታሳዩ እንመኛለን::"
(ዕብ. 6:10-13)

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

—- @fnotesawiros —-


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

ሐምሌ 24

አቡነ ዘዮሐንስ ጻድቅ

ኢትዮጵያዊው ጻድቅ የተወለዱት በ13ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ሲሆን ሃገረ ሙላዳቸው ሸዋ (መርሃ ቤቴ) ነው:: ወላጆቻቸው ዘካርያስ እና ሶፍያ እግዚአብሔርን የሚፈሩ : እመ ብርሃንን የሚወዱና ለነዳያን የሚራሩ ነበሩ::

ደጉ ዘካርያስ መስፍን ሲሆን እርሱ በሌለበት የሸዋ ገዢ ሊያገባት በመሞከሩ ቅዱስ ገብርኤል ቀስፎታል:: ሕዝቡ ገዢነቱን ለዘካርያስ ሰጥተውታል:: ከቆይታ በኋላም ድንግል ማርያም የተባረከ ፍሬ ሰጠቻቸው:: ስሙን "ዮሐንስ" አሉት:: በሒደት ግን ዘዮሐንስ (የዮሐንስ) ተብሏል::

ቅዱሱ ዘዮሐንስ እስከ ሰባት ዓመቱ ድረስ በእናቱ እቅፍ ቆይቶ ወደ ትምሕርት ገብቷል:: ጸጋ እግዚአብሔር ጠርቶታልና በአጭር ጊዜ ብሉይ ከሐዲስ ጠነቀቀ:: አደን ይወድ ነበርና ሊያድን ሲወጣ 'ብርሕት ደመና' ድንገት ነጥቃ ከኢትዮጵያ (ሽዋ) ወደ ኢየሩሳሌም (ጐልጐታ) አደረሰችው::

ደስ ብሎት ቅዱሳት መካናትን ተሳልሞ ደመናዋ ወደ ሃገሩ መለሰችው:: ከጥቂት ጊዜ በኋላም ከሰማይ ነቢዩ ኤልያስና መጥምቁ ወርደው ባረኩትና "ክፍልህ ከእኛ ጋር እንዲሆን መንን" አሉት::

ዘዮሐንስ ወላጆቹንና ቤተ ክርስቲያንን እያገለገለ (ዲቁና ነበረውና) ሃያ አምስት ዓመት ሞላው:: ያን ጊዜ ወላጆቹ "እንዳርህ" ቢሉት "የለም! አይሆንም" አላቸው:: አርጅተው ነበርና ስለእነርሱ ዕረፍት ጸለየ:: ፈጣሪም ሰምቶታልና ሁለቱም በክብር ተከታትለው ዐረፉ::

ሕዝቡ በወላጆቹ ፈንታ "እንሹምሕ" ቢሉት "እንቢ" ብሎ ወርቁን : ብሩን : ርስቱን : ቤቱን ሁሉ ለነዳያን አካፍሎ ወደ ደብረ ሊባኖስ ገባ::
ጊዜው አቡነ ተክለ ሃይማኖት ባረፉ በሃምሳ ዓመት አካባቢ ሲሆን አባ ሕዝቅያስ አበ ምኔት ነበሩ::
(ከዚህ በኋላ አንቱ እያልን እንቀጥል)

አባ ዘዮሐንስ ለሰባት ዓመታት ገዳሙን ረድተው መነኮሱ:: እንደ ልማዱ ደመና ነጥቆ ወስዷቸው ከኢየሩሳሌሙ ሊቀ ጳጳሳት ቅስና ተቀብለዋልና በደብረ ሊባኖስ ለሃያ አምስት ዓመታት አገለገሉ:: ቤተ መቅደሱን በመዓልት ሰባት ጊዜ በሌሊት ሰባት ጊዜ ያጥኑ : እልፍ እልፍ ይሰግዱ : ተግተው ይጸልዩ : ይታዘዙም ነበር::

ከዚያም በፈጣሪ ትዕዛዝ በትግራይና በሌሎቹ የሃገራችን ክፍሎች ወንጌልን ሰብከዋል:: እድሜአቸው ሰባ በሆነ ጊዜ ወደ ጌታ መቃብር (ጐልጐታ) ሔደው ተሳልመው በእርሱ (በጌታ) ትዕዛዝ ወደ ደራ (ጣና ዳር) ተመለሱ::

በአካባቢውም ገብርኤልና መስቀል ክብራ የሚባሉ ደጋግ ባለ ትዳሮች ነበሩና በእንግድነት ከቤታቸው አደሩ:: ቤቱ በቅጽበት በበረከት ሞላ:: እነርሱም የጻድቁን አምላክ አመሰገኑ::

ቀጥሎም በመስቀል ክብራ መሪነት ጻድቁ ዘዮሐንስ ወደ ክብራን ገብርኤል ደሴት ገቡ:: (በነገራችን ላይ ደሴቱ ክብራን የተባለ መስቀል ክብራ በምትሰኘው ደግ ሴት ስም ነው:: እርሷና ባሏ ገብርኤል የተቀደሱ ሰዎች ነበሩና::)

ጻድቁ አቡነ ዘዮሐንስ ወደ ደሴቶቹ (ክብራንና እንጦንስ ኢየሱስ) እንደ ገቡ ደሴቶቹ በግማሹ የስውራን ቤት : እኩሉ ደግሞ የጣዖት (ዘንዶ) አምላኪዎች መኖሪያ ነበር:: ጻድቁ ክብራን ገብርኤልንና እንጦንስ ኢየሱስን የመሠረቱት በ1315 ዓ/ም አካባቢ በዐፄ ዓምደ ጽዮን ዘመን ነው:: በአካባቢው ዘንዶ ይመለክ ነበርና ያንን በጸሎታቸው አጥፍተው ሕዝቡን አጥምቀዋል::

በዚያም ገዳሙን የወንድና የሴት ብለው ከፈሉ:: የወንዶች ክብራን ሲሆን ሴት አይገባበትም:: አበ ምኔቱም ራሳቸው ጻድቁ ነበሩ::
የሴቶች እንጦንስ ኢየሱስ ከካህናት በቀር ወንድ አይገባበትም:: እመ ምኔቷም እናታችን ቅድስት ክብራ (መስቀል ክብራ) ሆነች::

ጻድቁ አቡነ ዘዮሐንስ በክብራን ለሰላሳ አምስት ዓመታት ተጋድለዋል:: ለጸሎት ከመቆማቸው ብዛት እግራቸው አብጦ : ቆሳስሎ ነበር:: የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዘወትር ይገለጽላቸው : ያነጋግራቸውም ነበር::

እጅግ ድንቅ የሆኑ ተአምራትን ሠርተው: ለወንጌል እንደሚገባ ኑረው: በተወለዱ በመቶ አምስት ዓመታቸው በዚህች ቀን ዐርፈዋል:: ጌታችንም በስማቸው ለተማጸነና ገዳማቸውን ለሳመ የምሕረት ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል:: ልደታቸው ደግሞ ኅዳር 13 ቀን ይከበራል:: ገዳማቸው (ክብራን ገብርኤልና እንጦንስ ኢየሱስ) ድንቅ ነውና እንድታዩት ተጋብዛቹሃል::

ቅዱስ አባ ኖብ ሰማዕት

በምድረ ግብጽ ከታዩ ታላላቅ ከዋክብት አንዱ ቅዱስ ኖብ በሃገረ ንሒሳ ተወልዶ ያደገ ሲሆን ዘመኑም ዘመነ ሰማዕታት (3ኛው መቶ ክ/ዘመን) ነው:: ወላጆቹ በልጅነቱ ብዙ ሃብት ትተውለት ያርፋሉ:: ወደ ቤተ ክርስቲያን ሔዶ ካህኑ ስለ ምናኔና ሰማዕትነት ሲሰብክ ይሰማዋል::

ገና በአሥራ ሁለት ዓመቱ በቤቱ የነበረውን ሁሉ ለነዳያን አካፍሎ መስቀለ ክርስቶስን ሊሸከም ወደ ዐውደ ስምዕ (የምስክርነት አደባባይ -የክርስቲያኖች መገደያ ቦታ) ተጓዘ:: በዚያም በጉባዔ መካከል ክርስቶስን ሰበከ:: በዚህ ምክንያት በሰብዓዊ አካል ሊሸከሙት የማይችሉትን መከራ በልጅ ገላው ተቀብሏል::

በዚያው ልክም ብዙ ተአምራትን ሰርቷል:: በተአምራቱና በጣዕመ ስብከቱም ከመቶ ዘጠና ሺህ በላይ አሕዛብን ወደ ክርስትና መልሶ ሁሉም ተሰይፈዋል:: በእሳት: በስለት: በሰይፍ: በባሕርና በየብስ መከራን ከተቀበለ በኋላ በዚህች ቀን አክሊለ ክብርን ይቀበል ዘንድ አንገቱን ተከልሏል::

ጌታችን የገባለት ቃል ኪዳኑ ግሩም ነውና ዛሬ በግብጽ በድምቀት ይከበራል:: ምንም በእድሜ ልጅ ቢሆን ቤተ ክርስቲያን አባ (አባታችን) ኖብ ትለዋለች::

ቸር ጌታ መድኃኔ ዓለም በጻድቁና በሰማዕቱ ጸሎት ይማረን:: ከበረከታቸውም ይክፈለን::

ሐምሌ 24 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.አቡነ ዘዮሐንስ ጻድቅ ዘክብራን (ኢትዮጵያዊ)
2.ቅዱስ አባ ኖብ ሰማዕት
3.መቶ ዘጠና ሺህ ሰማዕታት (የአባ ኖብ ማኅበር)
4.አባ ተክለ አዶናይ ዘደብረ ሊባኖስ
5.አቡነ ተወልደ መድኅን (ኢትዮጵያዊ)
6.አባ ስምዖን ጻድቅ ሊቀ ጳጳሳት
7.ቅድስት ክብራ (መስቀል ክብራ) ዘእንጦንስ ኢየሱስ

ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት
2.ቅዱስ አጋቢጦስ (ጻድቅ ኤጲስቆጶስ)
3.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
4.ቅዱስ ቶማስ ዘመርዐስ
5.ቅዱስ አብላርዮስ ታላቁ
6.ሃያ አራቱ ካኅናተ ሰማይ (ሱራፌል)
7.ቅዱስ አባ ሙሴ ጸሊም (ኢትዮጵያዊ)

"ስለዚህ እኔ ደግሞ በእናንተ ዘንድ ስለሚሆን በጌታ በኢየሱስ ስለማመንና ለቅዱሳን ሁሉ ስለሚሆን መውደድ ሰምቼ ስለ እናንተ እያመሰገንሁ ስጸልይ ስለ እናንተ ማሳሰብን አልተውም::" †††
(ኤፌ. ፩፥፲፭)

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

—- @fnotesawiros —-


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

ሐምሌ 23

ታላቋ ቅድስት መሪና ሰማዕት (SAINT MARINA THE GREAT)

እናታችን ቅድስት መሪና ስም አጠራራቸው ከከበረ : ተጋድሏቸው ካማረ ታላላቅ ሴት ሰማዕታት አንዷ ናት:: ተወልዳ ያደገችው ከዋናው ዘመነ ሰማዕታት በፊት በ2ኛው መቶ ክ/ዘመን ሶርያ አካባቢ ነው:: አባቷ ዳኬዎስ የሚባል ጣዖት አምላኪ ቢሆንም እናቷ ግን ክርስቲያን ነበረች::

ነገር ግን እናቷ ገና በ5 ዓመቷ ሞተችባትና ለሞግዚት ተሰጠች:: የእግዚአብሔር ጥበብ ሆኖ ሞግዚቷ ደግ ክርስቲያን ነበረችና ለ10 ዓመታት ሃይማኖተ ክርስቶስን እና ምግባረ ጽድቅን አስተማረቻት:: ዕድሜዋ 15 ዓመት ሲሆን አባቷ ዳኬዎስ አረፈ::

በዘመኑ ዳኬዎስ የሚሉት (ቅዱስ መርቆሬዎስን የገደለው) ክፉ ንጉሥ ነበርና ክርስቲያኖችን አሳደዳቸው:: ይህን ዜና ቅድስት መሪና ስትሰማ ደስ አላት:: እጅግ ባማረ ንጽሕና እንደ ኖረች ሁሉ በክርስቶስ ስም ደሟን ለማፍሰስ አስባ ወደ ንጉሡ መኮንን ሔደች::

አበው እንዳስተማሩን ከሴቶች ሰማዕታት በውበትና ደም ግባት እንደ ቅዱሳት:-
*መሪና
*አርሴማ
እና
*ጣጡስ የሚያክል የለም:: ዐይንን ማፍዘዝ የሚችል ውበት ነበራቸው::

መኮንኑ መልኩዋን ዐይቶ ሰውነቱ ተናወጠ:: "ጣዖት አምልኪና የእኔ ሚስት ሁኚ" አላት:: እርሷ ግን መኮንኑን ከነ ጣዖቱ አቃለለችው:: "እኔ የክርስቶስ ሙሽራ ነኝ" አለችው::

መኮንኑ ካነጋገሯ የተነሳ ተቆጥቶ ይገርፏት ዘንድ አዘዘ:: መሬት ላይ ጥለው በብረት ዘንግ ቢመቷት አካሏ እየተቆረጠ ብዙ ደም ፈሰሰ:: ወስደውም ጨለማ ውስጥ ጣሏት:: ቅዱስ ሚካኤል ከሰማይ ወርዶ አድኗት: አጽንቷትም ዐረገ::

በማግስቱ በመጋዝ አካሏን ቆራርጠው ጣሉ:: ዳግመኛ ሊቀ መላእክት አዳናት:: ወደ ጨለማ ክፍል ወስደው ሲጥሏት ትልቅ ዘንዶ መጣባት:: እጆቿ ተዘርግተው እጸለየች ዋጣት:: እርሷ ግን ጸሎቷን ቀጠለች:: ከደቂቃዎች በሁዋላ ግን ዘንዶው ለ2 ተሰነጠቀና እጆቿ እንደተዘረጉ ወጣች::

በሌላ ቀን ግን ሰይጣን ፊት ለፊት መጥቶ ታገላት:: ከሰማይ ነጭ ርግብና መስቀል ወርዶላታልና አልቻላትም:: ከእግሯ በታች ጥላ ደጋግማ ረገጠችው:: ሰይጣንም በሐፍረት እየጮኸ ሔደ::
"ለሰይጣን ኬደቶ ከመ አሣዕን በእግር" እንዲል:: (እንዲህ ነበሩ የቀደመው ዘመን እናቶቻችን)

መኮንኑ ከክርስትና ያስወጣት ዘንድ በትልቅ ጋን ውሃ አስፈልቶ "በዚያ ላይ ቀቅሏት" አለ:: ድንገት ግን ከሰማይ ነጭ ርግብ ወርዳ: ውሃውን አቀዝቅዛ: 3 ጊዜ በውሃው አጠመቀቻት:: (እስከዚህ ሰዓት ድረስ አልጠመቀችም ነበርና)

ርግቧ የብርሃን ልብስ አልብሳ: አክሊለ ክብር ደፋችላት:: መኮንኑ ተስፋ ስለ ቆረጠ "አንገቷን በሰይፍ ምቱ" አለ:: በዚያች ሰዓት የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወርዶ "ብጽዕት መሪና ብጽዐን ይገባሻል" አላት::

"ስምሽ በሚጠራበት: መታሰቢያሽ በሚደረግበት ሁሉ በዚያ ረድኤት: በረከት ይበዛል:: አንቺን ያከበረውን አከብረዋለሁ:: ከርስትሺም አስገባዋለሁ" ብሏት ጌታችን ዐረገ::

ወታደሮቹ አንገቷን በሰየፉ ጊዜ ታላቅ መነዋወጽ ሆነ:: ድውያን ተፈወሱ: ዕውሮች አዩ: አንካሶች ረቱ: የማይሰሙትም ሰሙ:: ቅዱሳን መላእክትም ከሰማያት ወርደው የቅድስት መሪናን ነፍስ በዝማሬ አሳረጉ::

ቅዱስ ለንጊኖስ ሰማዕት

ለንጊኖስ
ማለት በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የስብከት ዘመን የዺላጦስ ወታደር የነበረ ሰው ነው:: ስለ ጌታችን ተአምራት በየጊዜው ይሰማ ነበር:: ሔዶ እንዳያገኘው ግን አይሁድን ይፈራ ነበር:: እነርሱ "በክርስቶስ ያመነ ሁሉ ከምኩራብ ይባረር" ብለው ነበርና:: (ዮሐ. 9:22)

ጌታችን በተሰቀለባት ዕለተ ዐርብ ግን ጭንቅ ሆነበት:: ጌታን እንዲሰቅሉ ከታዘዙ ወታደሮች እንደ አንዱ ተመርጦ ነበርና በዘዴ "አሞኛል" ብሎ እስከ 9 ሰዓት ድረስ ቆየ::

በሁዋላ ግን አይሁድ "በክርስቶስ ሞት ያልተባበረ ሁሉ ወንጀለኛ ነው" የሚል አዋጅ በማስነገራቸው እየፈራ ቀራንዮ ሲደርስ "ጐኑን ውጋው" ብለው ረዥምና ጥቁር ጦር ሰጡት:: ለንጊኖስ ወደ ጌታችን ዐይን ተመለከተ:: እያየው እንዳልሆነ ገመተ::

ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው በባሕርይ ሥልጣኑ ለይቷልና ጦሩን ጨብጦ ወደ ጌታ ጐን ልኮ ወጋው:: ከጌታ ቀኝ ጐንም በ"ለ" አምሳል ትኩስ ደምና ውሃ ፈሰሰ:: አንዷ ፍንጣቂ ሔዳ የታወረች ዐይኑ ላይ ዐርፋ ዐይኑን አበራች::

ለለንጊኖስ ታላቅ ደስታ ሆነ:: ለእኛ ግን ማየ ገቦና ደመ ገቦ ፈለቀልን:: የጌታችን ትእግስቱና ቸርነቱ ግን ይደንቃል::
"ከመ ኢየሐስብ ቦቱ ዘኩናተ እዱ ርግዘቶ::
በኃጣውኢሁ ለዘኢፈቀደ ሞቶ::
ምሕረቶ እሴብሕ ወዐዲ ትዕግስቶ
::" እንዳሉ ሊቃውንት::

ጌታችን ከተነሳ በሁዋላ ለንጊኖስ ወደ ቅዱስ ዼጥሮስ ዘንድ ሒዶ ስለ እውነት : ስለ ሃይማኖትም ተማረ:: ተጠምቆ: ምድራዊ ወታደርነቱን ትቶ እየሰበከ ከኢየሩሳሌም ወደ ቀዸዶቅያ ወረደ:: ለዘመናትም ጌታችን ክርስቶስን በሥርዓተ ወንጌል አገለገለ::

በመጨረሻም በጢባርዮስ ቄሣር ዘመን አይሁድ አሳደዱት: አንገላቱት:: የነርሱ ወገን ስለነበረም መከራ አጸኑበት:: የጽድቅ አርበኛና የክርስቶስ ሐዋርያ ቅዱስ ለንጊኖስ ግን ጸና:: በዚህች ዕለትም አይሁድ አንገቱን ቆርጠውት ለሰማዕትነት በቃ:: ቅዱሱ በሕይወቱም በዕረፍቱም ተአምራትን ሠርቷል::

እግዚአብሔር በቸር ጥሪው ሁላችንም ወደ ቀናው የጽድቅ ጐዳና ይጥራን:: ከሰማዕታቱም ረድኤት በረከት ይክፈለን::

ሐምሌ 23 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅድስት መሪና እናታችን (ታላቋ ሰማዕት)
2.ቅዱስ ለንጊኖስ ሐራ (ሐዋርያና ሰማዕት)
3.ቅዱስ አብጥልማዎስ

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት
2.ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት
3.ነቢየ ጽድቅ ቅዱስ ሰሎሞን (ንጉሠ እሥራኤል)
4.አባ ጢሞቴዎስ ገዳማዊ
5.ቅዱስ ዳንኤል ነቢይ
6.አባ ሳሙኤል
7.አባ ስምዖን
8.አባ ገብርኤል

"ወደ ጌታ ኢየሱስ በመጡ ጊዜ ግን እርሱ ፈጽሞ እንደ ሞተ አይተው ጭኑን አልሰበሩም:: ነገር ግን ከጭፍሮች አንዱ ጐኑን በጦር ወጋው:: ወዲያውም ደምና ውሃ ወጣ:: ያየውም መስክሯል : ምስክሩም እውነት ነው:: እናንተም ደግሞ ታምኑ ዘንድ : እርሱ እውነት እንዲናገር ያውቃል:: ይህ የሆነ:-
"ከእርሱ አጥንት አይሰበርም" የሚል የመጽሐፍ ቃል እንዲፈጸም ነው:: ደግሞም ሌላው መጽሐፍ:-
"የወጉትን ያዩታል" ይላል::"
(ዮሐ. 19:33)

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

—- @fnotesawiros —-


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

ሐምሌ 22

ታላቁ ኢትዮጵያዊ ሰማዕት አቡነ ጴጥሮስ

ሰማዕቱ
አቡነ ጴጥሮስ ምንም እንኳ ለሃገራቸውና ሃይማኖታቸው ያን ያህል ዋጋ ቢከፍሉም ትውልዱም : መንግስቱም : ራሷ ቤተ ክርስቲያናችንም ተገቢውን ክብር ሰጥተው እያሰቧቸው አይደለም:: እስኪ እንዲያው ቢያንስ እንደ ክርስቲያን : አንድም እንደ ኢትዮጵያዊ እነዚህ ነገሮቻቸውን እናስብ::

ሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስ ከልጅነታቸው ጀምረው ትምሕርት : ትሕርምትና ደግነት ወዳጅ እንደ ነበሩ ይነገራል:: ወቅቱ ኢትዮጵያ የራሷን ጳጳሳት የምትሻበት ጊዜ ነበርና በፈቃደ እግዚአብሔር ለመጀመሪያ ጊዜ የሃገራችን አራት አባቶች ጵጵስናን ተሾሙ::

እነርሱም ሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስ እና አበው አባ ሚካኤል: አባ አብርሃም እና አባ ይስሐቅ ናቸው:: የተሾሙትም ግንቦት 18 ቀን 1921 ዓ/ም ነው:: አቡነ ጴጥሮስ ከተሾሙ በኋላ በሐዋርያዊ አገልግሎትና በጸሎት ተግተው ኑረዋል::

በ1928 ዓ/ም ፋሺስት ጣልያን ሃገራችንን በወረረች ጊዜ ቆራጡ ጳጳስ በዱር በገደል ለመሔድ ተነሱ:: በየበርሃው እየሔዱ አርበኞችን ሲያጽናኑ : ሲናዝዙ : ሲባርኩም ቆይተዋል:: ለሃገራቸውና ለሃይማኖታቸው ረሃብ : ጥም : እንግልትን ታግሰዋል::

በተያዙባት በዚያች ሌሊትም በጣልያኖች ለሮም እምነትና ለአገዛዙ እንዲያጐበድዱ ተጠየቁ:: ቆራጡ ሰው ግን እንቢ ቢሉ የሚደርስባቸውን እያወቁ "አይደረግም" አሉ:: በማግስቱ በአደባባይ መትረየስ ተደግኖባቸው አሁንም ጥያቄ ቀረበላቸው::

አቡነ ጴጥሮስ አፋቸውን ከፍተው ሊናገሩ ጀመሩ:- "የሃገሬ ሕዝብ ሆይ! ለሃገርህ : ለሃይማኖትህ ባትጋደል ትውልድ ይፋረድህ:: ለጣልያን ግን እንኳን ሰው ዛፍ ቅጠሉ መሬቱ እንዳይገዛለት አውግዣለሁ" አሉ:: በደቂቃዎች ልዩነት በግራዚያኒ ትዕዛዝ የመትረየስ ጥይት ዘነበባቸው::

አካላቸው ተበሳስቶ በሰንሰለት እንደ ታሠሩ መሬት ላይ ወደቁ:: አንዱ ወታደር ቀርቦ ቢመለከት ትንሽ ትንፋሽ ነበረቻቸው:: "ይሔ ቄስ አልሞተም" ብሎ ጭንቅላታቸው ላይ ተኮሰባቸው::

አቡነ ጴጥሮስ ለሃገራቸውና ሃይማኖታቸው ተሠው:: ነገሩ በአርበኞች ዘንድ ሲሰማ ትግሉ ተቀጣጠለ:: ይሄ የተደረገው ሐምሌ 22 ቀን በ1928 ዓ/ም ነው:: አቡነ ጴጥሮስም በተ/መ/ድ (UN) የሺህ ዓመቱ ምርጥ ሰማዕት (MARTYR OF THE MILLENIUM) በመባል ይታወቃሉ::

ቅዱስ መቃርስ ሰማዕት

ሰማዕቱ ተወልዶ ያደገው በአንጾኪያ (ሶርያ) በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን ሲሆን የታላቁ ቅዱስ ፋሲለደስ እና የቅድስት ሶፍያ ልጅ ነው:: ምንም በቤተ መንግስት ውስጥ ቢያድግም ከወላጆቹ ፍቅረ ክርስቶስን : ንጽሕናንና ደግነትን ወርሷል::

በተለይ ነዳያንን ሰብስቦ ዕለት ዕለት ያበላ ነበር:: (መቃርስ ማለት በልሳነ ዮናኒ ብጹዕ : ንዑድ : ክቡር ማለት ነው::) ቅዱሱ ያ የመከራ ዘመን ሲመጣ ሁሉም ቤተሰብ ስለ ክርስቶስ መሞትን በመምረጡ እርሱም ደስ እያለው የመከራው ተካፋይ ሆኗል::

ያን የመሰለ የቤተ መንግስት ክብር ስለ ክርስትና ናቀው:: ተገረፈ:: ተሰቃየ:: በእሳትም ተቃጠለ:: አንድ ጊዜም በአደባባይ የሞተ ሰው በጸሎቱ አስነስቶ "መስክር" አለው:: ከሞት የተነሳውም የክርስቶስን አምላክነት በመመስከሩ በአደባባይ የነበሩ ብዙ አሕዛብ በክርስትና አምነው ተሰይፈዋል::

ቅዱስ መቃርስን ግን ብዙ አሰቃይተው በዚህች ቀን አንገቱን ቆርጠውታል:: ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ አጽሙን አፍልሶ በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን በስሙ ቤተ ክርስቲያን አንጾለታል::

ቅዱስ ለውንትዮስ ሰማዕት

ቅዱሱ የተወለደው በተመሳሳይ ዘመን (በቅዱስ መቃርስ) ሲሆን ሃገሩ ጠራብሎስ ትባላለች:: በወቅቱ በወታደርነት ነገሥታቱን ያገለግል ነበር:: ድንግል : ደም ግባት የሞላለት ወጣት ስለ ነበር በሰዎች ፊት ሞገስ ነበረው::

እርሱ ግን ምንም ወታደር ቢሆን ጾምና ጸሎትን ያዘወትር ነበር:: በተለይ ደግሞ የዳዊትን መዝሙር እየመላለሰ ይጸልየው : ይወደው ነበር:: ንግግሩ ሁሉ በመንፈስ ቅዱስ ጨውነት የታሸ ነውና ብዙ ጓደኞቹን ከክህደት ወደ ሃይማኖት : ከክፋት ወደ ደግነት መልሷል::

የመከራ ዘመን በደረሰ ጊዜም በገሃድ ስመ ክርስቶስን ይሰብክ ነበር:: ክፉ ሰዎች ከሰውት በመኮንኑ ፊት በቀረበ ጊዜም አልፈራም:: ወታደሮቹ መሬት ላይ ጥለው እየደበደቡት : ደሙ እንደ ጐርፍ እየተቀዳ እርሱ ግን ይዘምር ነበር::

በመጨረሻም ስለ ክርስቶስ ፍቅር በዚህች ቀን አንገቱን ተሰይፏል:: ቅዱስ ለውንትዮስ እጅግ ተአምረኛ ሰማዕት ነውና በእምነት እንጥራው::

እግዚአብሔር ዐጽመ ሰማዕታትን ይጠብቅልን:: ከሰማዕታቱ ጽናትን : ጸጋ በረከትን ይክፈለን::

ሐምሌ 22 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.አቡነ ጴጥሮስ ሰማዕት (ኢትዮጵያዊ)
2.ቅዱስ መቃርስ ሰማዕት (የፋሲለደስ ልጅ)
3.ቅዱስ ለውንትዮስ (ክቡር ሰማዕት)
4.አባ እንጦንስ አበ መነኮሳት (ቅዳሴ ቤታቸው)
5.ቅዱስ መርካሎስ

ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ዑራኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ሉቃስ ወንጌላዊ
3.ቅዱስ ደቅስዮስ (የእመቤታችን ወዳጅ)
4.አባ ጳውሊ የዋህ

"እንግዲህ አትፍሯቸው:: የማይገለጥ የተከደነ: የማይታወቅም የተሠወረ ምንም የለምና:: በጨለማ የምነግራችሁን በብርሃን ተናገሩ:: በጆሮም የምትሰሙትን በሰገነት ላይ ስበኩ:: ሥጋንም የሚገድሉትን: ነፍስን ግን መግደል የማይቻላቸውን አትፍሩ:: ይልቅስ ነፍስንም: ሥጋንም በገሃነም ሊያጠፋ የሚቻለውን ፍሩ::"
(ማቴ. ፲፥፳፮)

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
—- @fnotesawiros -—


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ሐምሌ 21
ድንግል እመቤታችን እና ቅዱስ ዑራኤል

ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ትውፊት መሠረት በዚህች ቀን ከሰባቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ የሆነው ቅዱስ ዑራኤል:-
1.ድንግል ማርያም በአካለ ሥጋ እያለች ወደ ሰማይ አሳርጓታል:: በሠረገላ ብርሃን ጭኖ: በክንፎቹም ተሸክሞ: አስቀድሞ ገነትን ቀጥሎም ሲዖልን አስጐብኝቷታል:: በዚህም ምክንያት ስለ ኃጥአን የምታለቅስ: የምትለምንና የምትማልድ ሆናለች:: ለምናም አልቀረች የምሕረት ቃል ኪዳን ተቀብላለች::

2.ቅዱሱ መልአክ እመ ብርሃንን በስደቷ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ መርቶ አምጥቷታል:: በክንፉ ተሸክሞ: በአራቱም አቅጣጫ አዙሮ አሳይቶ አሥራት እንድትቀበል አድርጓል::

3.ጌታችን በተሰቀለ ጊዜ ደሙን በጽዋዕ አድርጐ በኢትዮጵያ ወንዞች ላይ አፍስሷል::

4.ለብዙ ቅዱሳን (አባ ጊዮርጊስን ጨምሮ) ጽዋዐ ልቡናን አጠጥቷል::

አቡነ በጸሎተ ሚካኤል ኢትዮጵያዊ

ወላጆቻቸው ማርቆስ እና እግዚእ ክብራ ይባላሉ:: ተአምራትን ገና ከእናታቸው ማኅጸን ጀምሮ ይሠሩ የነበሩት ጻድቁ በልጅነታቸው መጻሕፍትን ተምረው መንነዋል:: በስብከተ ወንጌልም ትግራይና አካባቢውን አድርሰዋል:: በነዚህም ጊዜያት ብዙ አርድእትን አፍርተዋል::

በጋስጫ ገዳም መስርተው የወንድና የሴት ብለውም ለይተዋል:: ሲጸልዩም ሆነ ሲያስተምሩ ተደሞ ይመጣባቸው የነበረ ሲሆን አንድ ቀን እባቡን ዓሣ አድርገው ደቀ መዛሙርትን አስደንቀዋል::

ከጾም: ከጸሎትና ከስግደት ባሻገር ከወቅቱ ንጉሥ ዓምደ ጽዮን መከራ በመቀበላቸው እንደ ሰማዕትም ይቆጠራሉ:: ከብዙ የገድል ዓመታት በኋላም በ1330 ዓ/ም በዚህች ቀን ትግራይ ውስጥ ዐርፈዋል:: በቆይታ ግን ወደ ጋስጫ ዐጽማቸው ፈልሷል::

ቅዱስ ላዕከ ማርያም ኢትዮጵያዊ

ቅዱሱ የአፄ ናዖድ የልጅ ልጅ : የቅድስት ሮማነ ወርቅ ልጅ : የልብነ ድንግል የእህት ልጅና የገላውዴዎስ አጐት ነው:: በግራኝ አህመድ ዘመን ተማርኮ ወደ የመን : ከዛም ቱርክ ተወስዷል::

ሃይማኖቴን አልክድም ስላለ ብዙ አሰቃይተው : አባለ ዘሩን ቆርጠው ጃንደረባ አደረጉት:: በድንቅ ተአምር ግን ወደ ሃገሩ ተመለሰ:: እስከ ዕለተ ሞቱም ነዳያንን ሲያበላ ኑሮ ዛሬ ዐርፏል::

ቅዱስ ሱስንዮስ

በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበረ የኤፌሶን ሰው ሲሆን ጃንደረባም ነበር:: በ431 ዓ/ም ሁለት መቶውን የጉባዔ ኤፌሶን ሊቃውንት አገልግሎ በዛው ዓመት አርፏል:: ቅዱስ ቄርሎስ ገንዞ ቀብሮታል::

ብጹዕ አወ ክርስቶስ

ከተባረከች ሚስቱ ጋር በአንድ ቤት ውስጥ : ግን ደግሞ በድንግልና ኑረዋል:: ቀን ቀን እንግዳ ሲቀበሉ: ነዳያንን ሲያበሉ ውለው ሌሊት ሲገሰግዱና ሲጸልዩ ያድሩ ነበር:: ጌታችን ከሰማይ መስክሮላቸው ዛሬ ዐርፈዋል::

ቅዱስ ዮራኖስ

በሉቃስ ወንጌል ላይ (ሉቃ. 23:47) የምናገኘው የመቶ አለቃው ሲሆን በጌታችን ትንሣኤ ቀን የጠፋች ዓይኑ በርታለት በክርስቶስ አምኖ ለሰማዕትነት በቅቷል::

ከእመቤታችን ድንግል ማርያም ጣዕሟን ፍቅሯን : ከቅዱሳኑ ሁሉ ጸጋ በረከትን እግዚአብሔር ያድለን::

ሐምሌ 21 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅድስት ድንግል እግዝእትነ ማርያም ወላዲተ አምላክ
2.ቅዱስ ዑራኤል ሊቀ መላእክት
3.አቡነ በጸሎተ ሚካኤል ጻድቅ (ኢትዮጵያዊ)
4.ቅዱስ ላዕከ ማርያም ሔር (ኢትዮጵያዊ)
5.አቡነ ኤዎስጣቴዎስ (ኢትዮጵያዊ) ልደታቸው
6.ብጹዕ አወ ክርስቶስና ሚስቱ (ጻድቃን)
7.ቅዱስ ሱስንዮስ ጻድቅ
8.ቅዱስ ዮራኖስ መኮንን (የመቶ አለቃው)

ወርኀዊ በዓላት
1.አበው ጎርጎርዮሳት
2.አቡነ ምዕመነ ድንግል
3.አቡነ አምደ ሥላሴ
4.አባ አሮን ሶርያዊ
5.አባ መርትያኖስ ጻድቅ

"እንግዲህ ምን እላለሁ? ስለ ጌዴዎንና ስለ ባርቅ: ስለ ሶምሶንም: ስለ ዮፍታሔም: ስለ ዳዊትና ስለ ሳሙኤልም: ስለ ነቢያትም እንዳልተርክ ጊዜ ያጥርብኛልና:: እነርሱ በእምነት መንግሥታትን ድል ነሡ:: ጽድቅንም አደረጉ:: . . ."
(ዕብ. ፲፩፥፴፪)

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

—- @fnotesawiros —-


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ሐምሌ 20
በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም

ለስም አጠራሯ ክብር ይሁንና እመ ብርሃን ድንግል ማርያም በዚህች ቀን ወደ ቤተ መቅደስ ገብታለች:: በዓሉ ከሰላሳ ሦስቱ የእመቤታችን በዓላት እንደ አንዱ አይቆጠርም:: ምክንያቱም ቅዱሳን ሊቃውንት በዓታ ከበዓታ ጋር ይስማማል ብለው የታኅሣሥ ሦስትን በዓል ከሰላሳ ሦስቱ ደምረውታል::

እመቤታችን ወደ ቤተ መቅደስ የገባችው ሁለት ጊዜ ሲሆን:-
1.ዛሬ የምናከብረውና በተወለደች በሰማንያ ቀኗ የገባችበት ነው:: (ከግንቦት 1 ጀምረን እናስላው: 80 ቀን ይመጣል::)
ኦሪት እንዳዘዘው ቅዱሳን ኢያቄምና ሐና ንጽሕት ሕፃን ድንግል ማርያምን ታቅፈው: የርግብ ልጆች (ግልገሎች): ዋኖስም ይዘው ወደ ቤተ መቅደስ ሒደዋል::
ካህናቱ ዘካርያስና ስምዖን ወጥተው በደስታ ተቀብለዋቸዋል:: እመቤታችን ለወላጆቿ ማኅጸን የከፈተች በኩር ናትና በእግዚአብሔር ፊት አቅርበዋታል::

2.ከሦስት ዓመታት በኋላ እንደ ስዕለታቸው ወደ ቤተ መቅደስ ወስደው ለእግዚአብሔር ሰጥተዋት ተመልሰዋል::

እግዚአብሔር ዛሬ ያልቃል: ነገ ይደቃል የማይባለውን የድንግል እናቱን ፍቅር አብዝቶ ያድለን:: በረከቷም በእኛ ላይ ጸንቶ ይኑር::

ቅዱስ ቴዎድሮስ ሰማዕት

በቤተ ክርስቲያን
የሰማዕታት አለቅነት ከተሰጣቸው ሰማዕታት አንዱ የሆነው ማር ቴዎድሮስ የተወለደው በምድረ አንጾኪያ (ሶርያ) በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: አባቱ ዮሐንስ በትውልድ ግብጻዊ የሆነ ክርስቲያን ነው:: እናቱ ግን አስቸጋሪና ጣዖት አምላኪ ሶርያዊት ነበረች::

ባልና ሚስት አብረው ሲኖሩ ሚስት ባሏ ክርስቲያን መሆኑን አታውቅም ነበር:: ቴዎድሮስ (የእግዚአብሔር ስጦታ ማለት ነው) በተወለደ ጊዜ ግን ጠብ ተነሳ:: እሱ ክርስትና ለማስነሳት: ሚስት ደግሞ ወደ ጣዖት ቤት ለመውሰድ ተጋጩ:: ሚስት ወገኖቿ ባለስልጣኖች ናቸውና ልጁን ቀምታ ባሏን ዮሐንስን ወደ ግብጽ አሳደደችው::

ዮሐንስ በስደት ባለበት ሃገር ስለ ልጁ ፈጽሞ ይጸልይ: ያለቅስም ገባ:: እግዚአብሔር ደግሞ ልመናውን ሰማ:: ማር ቴዎድሮስ ወጣት በሆነ ጊዜ ማንም ሳይጠራው ወደ ቤተ ክርስቲያን ሔዶ ተማረ: ተጠመቀ:: ዕለት ዕለትም ጾምና ጸሎትን ከምጽዋት ጋር ያበዛ: ድንግልናውን ለመጠበቅ ይተጋ ነበር::

በዛው ልክ ደግሞ ገና በሃያ ዓመቱ በጉልበቱ ኃያል: በውበቱም ደመ ግቡ: በጠባዩም ገራገር ነበርና ተወዳጅ ነበር:: ነገሥታቱም የአንጾኪያ የጦር ሠራዊት አለቃ አድርገው ሾሙት:: እነሆ እስከ ዛሬ "የሠራዊት አለቃ" ተብሎ ይጠራል::

ማር ቴዎድሮስ በተሳተፈባቸው ጦርነቶች ሁሉ ተሸንፎ አያውቅም:: ይልቁኑ የነገሥታቱን (የጠላት) ልጆች በመማረክ ነው የሚታወቀው:: እንዲያውም አንድ ጊዜ ከአሕዛብ ጋር በተደረገ ጦርነት ብቻውን አሸንፏቸዋል::

የፋርስ ሰዎች ሊዋጉ ሲመጡ መልአክ ከሰማይ ወርዶ ሰይፍ ሰጠው:: ፋርሶችን "በከንቱ ከምትጠፉ ወደ ሃገራችሁ ተመለሱ" አላቸው:: እነርሱ ግን ተሳለቁበት:: ከፈረሱ ወርዶ ወደ ምስራቅ ዙሮ ጸልዮ በመስቀል አማተበ:: በመካከላቸው ገብቶም በመልአኩ ሰይፍ ለወሬ ነጋሪ ሳያስቀር አጠፋቸው::

አንድ ቀን ወደ አንድ ከተማ ቢገባ ዘንዶ ሲመለክ አገኘ:: ይባስ ብሎ የአንዲት ክርስቲያን ልጆችን ለመስዋዕትነት ሲያቀርቧቸው ተመለከተ:: በስመ ሥላሴ አማትቦ: በፈረሱ ላይም ተቀምጦ ዘንዶውን በጦር ገደለው:: የዘንዶውም ርዝመት ሃያ አራት ክንድ ነበር::

ከነገር ሁሉ በኋላ ቅዱስ ቴዎድሮስ ስለ አባቱ ወሬ ሰምቶ: ካለበት ሥፍራ አፈላልጎ አግኝቶ ደስ አሰኘው:: እስኪያርፍ አብሮት ቆይቶ: ቀብሮት ወደ አንጾኪያ ሲመለስ ግን የሚያሳዝን ነገር ጠበቀው::
ክርስቶስ ተክዶ:
ጣዖት ቁሞ:
አብያተ ክርስቲያናት ተቃጥለው:
የክርስቲያኖች ደም ፈሶ:
ከተማዋ በግፍ ተሞልታ ተመለከተ:: እርሱም በዚያች ሰዓት መወሰን ነበረበትና አደረገው:: የሁሉ ሠራዊት አለቃ ቢሆንም የክብር ልብሱን አውልቆ: ባጭር ታጥቆ በንጉሡ ዲዮቅልጢያኖስ ፊት ቆመ::

ማር ቴዎድሮስ በአደባባይ እንዲህ ተናገረ:- "አንሰ አመልኮ ለክርስቶስ ንጉሠ ስብሐት በኩሉ ልብየ: ወእሠውዕ ሎቱ - እኔስ የክብር ባለቤት ክርስቶስን በፍጹም ልቤ አመልከዋለሁ: ለእርሱም ብቻ እሠዋለሁ::" ንጉሡ በቁጣ መሬት ላይ ጥለው እንዲደበድቡት አዘዘ:: ወታደሮቹ ደሙ እስኪንጠፈጠፍ ገረፉት::

በብዙ መክፈልተ ኩነኔ አሰቃይተው በእሳት አቃጠሉት:: እርሱ ግን በጸሎቱ እሳቱን ውኃ አደረገው:: ወታደሮቹ እርሱን በብዙ አሰቃዩ:: እርሱ ግን በእግዚአብሔር ኃይል ጸና: ታገሠ::

በመጨረሻም ጌታችን በግርማ ወርዶ "ወዳጄ ቴዎድሮስ ስምህን የጠራ: መታሠቢያህን ያደረገ: ገድልህን (ዜናህን) የጻፈ: ያጻፈ: ያነበበ: ገዝቶ በቤቱ ውስጥ ያኖረውን ሁሉ እምርልሃለሁ" አለው::

በስሙም ረድኤት እንደሚደረግ ነግሮት ዐረገ:: ወታደሮቹም በዚህ ቀን አንገቱን ሰይፈው የክብር አክሊልን ተቀብሏል:: እጅግ ብዙ ሺህ ሰዎችም አብረውት ተሰይፈዋል::

ቸሩ ፈጣሪ ከሰማዕቱ በረከት ይክፈለን::

ሐምሌ 20 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.በዓታ ለእግዝእትነ ማርያም (በሰማንያ ዕለት)
2.ቅዱስ ወክቡር ማር ቴዎድሮስ ሰማዕት (የሠራዊት አለቃ)
3.ቅዱስ ጢሞቴዎስ ዘእስክንድርያ
4.አራት መቶ አራት ሰማዕታት (የቅዱስ ቂርቆስ ማኅበር)
5.ቅድስት አውስያ (የማር ቴዎድሮስ እናት - በልጇ ምክንያት ያመነች እናት ናት)

ወርኀዊ በዓላት
1..ቅዱስ ዮሐንስ ሐፂር
2.ቅዱስ አክሎግ ቀሲስ
3.ቅዱስ አፄ ካሌብ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮጵያ)
4.አባ አሞንዮስ ዘሃገረ ቶና
5.ቅድስት ሳድዥ የዋሒት

"እግዚአብሔር ለኛ የሰማዕትነትን ሥራ ይሰጠን ዘንድ ቅዱሳን ስለሚሆኑ ሰማዕታት እንማልዳለን::"
(ሥርዓተ ቅዳሴ ቁ. ፸፫)

"በጐንም ለማድረግ ብትቀኑ የሚያስጨንቃችሁ ማን ነው? ነገር ግን ስለ ጽድቅ እንኳ መከራን ብትቀበሉ ብጹዓን ናችሁ:: ማስፈራራታቸውንም አትፍሩ:: አትናወጡም:: ዳሩ ግን ጌታን እርሱም ክርስቶስን በልባችሁ ቀድሱት:: በእናንተ ስላለ ተስፋ ምክንያትን ለሚጠይቋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዘወትር የተዘጋጃችሁ ሁኑ:: ነገር ግን በየውሃነትና በፍርሃት ይሁን::"
(፩ጴጥ. ፫፥፲፫-፲፮)

ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

@fnotesawiros


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ሐምሌ 19

ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣ

ሐምሌ ዐሥራ ዘጠኝ በዚህች ቀን ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣ በሰማዕትነት መከራ ተቀበሉ። ይህም ሕፃን ዕድሜው ሦስት ዓመት ሲሆነው ከሮሜ አገር ወደሌላ ሀገር እናቱ ይዛው ሸሸች በዚያም የሸሸችውን መኰንን አገኘችው ።

ሰዎችም ነገር ሠሩባት ወደርሱ አስቀረባትና ስለ አምልኮ ጠየቃት እርሷም ''መኰንን ሆይ ዕድሜው ሦስት ዓመት የሆነው ሕፃን አለ፣ አማልክቶችህን ማምለክ መልካም እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ ያስረዳን ዘንድ እርሱን ጠይቅ'' አለችው ።

ሕፃኑም ወደአለበት ጭፍራውን ልኮ ወደርሱ አስመጣው ሕፃኑንም ፊቱ ብሩህና ደስተኛ እንደሆነ አየውና ''አንተ ደስተኛ ሕፃን ሆይ እንዴት ነህ'' አለው። ሕፃኑም መልሶ ''አዎ ለእኔ ደስታ ተጠብቆልኛል ላንተ ግን ኀዘንና ልቅሶ ጥርስ ማፋጨትም ነው መጽሐፍ ለዝንጉዎች ተድላ ደስታ የላቸውም ብሏልና'' አለው እግዚአብሔር ኃይልና ንግግርን ሰጥቶታልና ብዙ ተናገረ በዚያም ያሉትን እስከ አስደነገጣቸው ድረስ ንጉሡን መኳንንቱንና ጣዖታቱን ረገማቸው ከብርታቱም የተነሣ አደነቁ ።

መኰንኑም በአፈረ ጊዜ በየአይነቱ በሆነ ሥቃይ ታላላቆች የማይችሉትን ታላቅና አስጨናቂ የሆነ ሥቃይን አሠቃየው እናቱንም ከርሱ ጋር እንደ እርሱ አሠቃያት። እግዚአብሔርም ያለምንም ጉዳት ያነሣቸው ነበር። ብዙዎች አሕዛብም ይህን አይተው አደነቁ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም አምነው በሰማዕትነት ሞቱ የሰማዕትነትንም አክሊል ተቀበሉ ።

በሕፃኑ ላይም የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ አደረበት። ታላላቅ ድንቆችና ተአምራቶችንም አደረገ ብዙዎች በሽተኞችንም አዳናቸው።
ከዚህም በኋላ መኰንኑ በታላቅ የናስ ጋን ውስጥ ውኃ ጨምረው በእሳት ያፈሉት ዘንድ አዘዘ የፍላቱም ድምጽ እንደ ክረምት ነጐድጓድ ሆነ ያን ጊዜም ፍርሀትና የሃይማኖት ጉድለት በእናቱ ላይ ደረሰባት ሕፃኑም ስለ እናቱ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ ።

ያን ጊዜ ጌታችን ልቧን ወደ ሰማይ አሳርጎ ለቅዱሳን ሰማዕታት የተዘጋጁ የብርሃን ማደሪያዎችን አየች ከዚህም በኋላ ጸናች፣ እግዚአብሔርንም አመሰገነችው። ልጅዋንም ''ልጄ ሆይ ከእንግዲህ አንተ አባቴ ነህ እኔም ልጅህ ነኝ'' አለችው ።

''ያቺ ከኔ የተወለድክባትም ቀን የተባረከች ናት'' አለች። ወደዚያ ወደ ጋኑ ውስጥ በገቡ ጊዜም የውኃው ፍልሐት እንደ ንጋት ጊዜ ውርጭ ቀዘቀዘ ከእግዚአብሔር የታዘዘ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወርዶ የእሳቱን ኃይል አቀዝቅዞታልና ።

ከዚህም በኋላ መኰንኑ ሥጋቸው ተቆራርጦ እስከሚወድቅ ድረስ በመቃጥን ውስጥ አድርገው እንዲጐትቷቸው አዘዘ ከእግዚአብሔርም የታዘዘ መልአክ አዳናቸው መኰንኑም በታላቅ ሥቃይ ያሠቃያቸው ዘንድ አስቦ እስኪመክር ድረስ በወህኒ ቤት ዘጋባቸው ።

ያን ጊዜም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሕፃኑ ቂርቆስ ወርዶ አጽናናው አረጋጋውም። ስሙን ለሚጠራና መታሰቢያውን ለሚያደርግ ቃል ኪዳን ሰጠው ።

እግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ቂርቆስና በኢየሉጣ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ትድረሰን ለዘላለሙ አሜን!

(ስንክሳር ዘወርኀ ሐምሌ) ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
@fnotesawiros


በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

ታላቁ ቅዱስ ሳዊሮስ (የሃይማኖት ጠበቃ!)

ቅዱስ ሳዊሮስ በስድስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ አካባቢ በሶርያ አንጾኪያ የተነሳ አባት ነው። ወቅቱ መለካውያን (ሁለት ባሕርይ ባዮች) የሰለጠኑበት እንደ መሆኑ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምእመናን ያነሱበትና የሚሰደዱበት ጊዜ ነበር። በዚህ ጊዜ ነበር ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ሳዊሮስ በሥላሴ ፈቃድ ለቤተ ክርስቲያን የተነሳው። ሊቃውንት አንበሳ ሲሉ ይጠሩታል።

ቅዱሱ ለተዋሕዶ ሃይማኖት ብዙ ሆኖላታል። የመናፍቃን ጸር በመሆኑ ብዙ ድርሰቶችን ደርሷል። ንጉሡን ዮስጢያኖስን (Justinian) ሳይቀር በይፋ ይገስጸው ነበርና ንጉሡ ሊገድለው ቆረጠ።

ሃይማኖቷ የቀና ንግሥቲቱ ታኦድራ ግን ይህንን ስትሰማ በሌሊት ወደ ሊቁ ሒዳ "እባክህን ሽሽ።" አለችው። እርሱ ግን "ሞት ለእኔ ክብር ነውና አልሔድም።" ሲል መለሰላት። አባቶችን ሰብስባ "ስለ ቤተ ክርስቲያን ስትል" ብለው ለምነው ወደ ግብጽ ሸኙት።

እርሱ እየሔደ ገዳዮቹ ያሳድዱት ገቡ። መንገድ ላይ ቢደርሱበትም ተሰወረባቸው። ለብዙ ቀናትም አብሯቸው ተጓዘ። እነርሱ ተስፋ ቆርጠው ሲመለሱ እርሱ ግን ምድረ ግብጽ ደረሰ።

በምድረ ግብጽም የጵጵስና ልብሱን ትቶ የመነኮሳትን አሮጌ ልብስ ለብሶ ሕዝቡንና መነኮሳቱን አስተማረ፤ አጸና። በየቦታውም ብዙ ተአምራትን ሠራ። አባቶች መነኮሳትም ማንነቱን ባወቁ ጊዜ ሰገዱለት። ዶርታኦስ (ዱራታኦስ) በሚባል አንድ ደግ ሰው ቤትም በስድስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ አካባቢ የካቲት ፲፬ ቀን ዐርፏል። "ለቅዱሳን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ስለ ተሰጠ ሃይማኖት እንድትጋደሉ እየመከርኋችሁ እጽፍላችሁ ዘንድ ግድ ሆነብኝ።"
(ይሁዳ ፩፥፫) ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

@fnotesawiros


Репост из: Kirub art🎨
#ወፌ /ስነ-ግጥም 👉 @Binigtm

በምስጋና ዜማ ለተሰጣት መና
ተግታ ዘምራለች በፀሀይ በዳመና
ቅኔን እየዘራች አርሳ በሰምና ወርቅ
ምንዳ ትከፍላለች ለምትለቅማት ስንቅ።

🎨 @kiradavi 🎨
🎨 +251985426631 🎨
🎨 @kirubrt 🎨

🗿 @pilasethiopia 🗿


     ♥✿♥ ብረሪ ብረሪ ♥✿♥
አንቺ የዋህ ፍጡር ብረሪ ብረሪ
ባህሩን አቆርጠሽ ደስታና ሀዘኑን
ለዛ ለወገኔ ሂጂና አብስሪ
ፍቅርን ዝሪ ሰላምንም ጥሪ
ጩኸትሽ ይሰማል ለምላክ ተናገሪ

©ከቢኒኦኔ ገብሬ
join  -   👇

💚  @binionae 💚
💛  @binionae 💛
 ❣    @binionae
   


     ፡፡፡፡፡፡ ባለ ምንጬ ፡፡፡፡፡፡
የሩቅም የቅርብም ጎረቤቱ ሁሉ
ከግቢ ውስጥ ገብተው ውሃን ይቀዳሉ
               ውሃን ያፈሳሉ ውሃን ይጠጣሉ ፤
ያ ምስኪን የምንጭቱ ጌታ በድንገት ወደቀ
          በሽታው ፀንቶበት ጉልበቱም አለቀ ፤
በአያኑ እያየ የሚፈልቀውን ምንጭ
ውሃ እንዳለ ሞተ አጥቶ የሚያስጎነጭ ።
፡፡፡፡፡፡፡፡፡  ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡ ፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
እንደ ንፉግ ሀገር መፈጠርን ያህል የእድል በደል የለም ንፍገት በረከት ይመስል ፀንቶ የሚኖርባት ክፉ አባዜ ባለበት እኩይ አፈር መብቀልን የመሰለ መረገም የለም ።

©ከቢኒኦኔ ገብሬ
join  -   👇

💚  @binionae 💚
💛  @binionae 💛
 ❣    @binionae
  


     ፡፡፡፡፡፡፡፡፡ ምቀኞቼ ፡፡፡፡፡፡፡፡
ምቀኞቼ የምላቸው                              ልቤ አጥብቆ የጠላቸው።
በፉክክር ያበረቱኝ
ጉልበቴንም ያፀኑልኝ ።
ምቀኞቼ ናቸው መንገዴ
ከንፉቅቅ ያነሱኝ ወደ ዳዴ
ካዳደም አስቁመው ለመራመዴ ።
በህይወቴ ገብተው መልካም ሰራንልህ
ሲሉ የኖሩ
ለካስ ወዳጆቼ ምቀኞቼ ነበሩ ።

©ከቢኒኦኔ ገብሬ
join  -   👇

💚  @binionae 💚
💛  @binionae 💛
 ❣    @binionae
   


Репост из: ፍኖተ ሳዊሮስ መንፈሳዊ ማኅበር
                   ሰው
ከራሱ ሲጠላ ከሂሊናው ሲጋጭ
ደስታውን ሲለዉጥ ለሀዘን ግልባጭ !
ሲቀጣ ሲገረፍ በፀፀት አለንጋ
ሰው ሆኖ ተፈጥሮ ሲያጣ የሰው ዋጋ !
መኖሩን ይረግማል ደጋግሞ ደጋግሞ
እዉነትን አቁስሎ በሀሰት ታክሞ ::

.©ከቢኒኦኔ ገብሬ

join  -   👇
💚  @binionae 💚
💛  @binionae 💛
 ❣    @binionae


      #ማዲንጎ_አፈወርቅ
#ትዝታ

|አግኝቶ ላያገኝ ወይ ጠቅሞ ላይጠቅመው
ሰው ለምን ይኖራል ትዝታ ሲያደክመው|➋

ትርጉሙ ምንድነው ምንድነው ትዝታ
ምንድነው ሰው ማሰብ ምንድነው ትዝታ
ባክህ ተው የማይሉት የሁሉም ሰው ጌታ

|ይኸው ሰው ይኖራል በትዝታ ሰበብ|➋
የኋሊት ሲጋልብ ትናንትን በማሰብ

|ሰው እንዴት ባለፈው በትናንት ይኖራል|➋
|ዛሬን በእጁ ይዞ ለነገው መሰላል|➋

ገለል በል ትዝታ ልርሳ በሽታዬን
አትጋርደኝ ልይበት የነገ ተስፋዬን
ባይጠፋ አሻራው ትዝታው ቢነፍስም
ባለፈ ዓመት ዝናብ ዛሬ አይታረስም
በትዝታ ሰበብ ላለፈው ሲጨነቅ
ስንት ሰው አለፈ ከአምላክ ሳይታረቅ
ገነባለሁ እንጂ ድካሙ ቢያመኝም
ለፈረሰው ቤቴ ሳለቅስ አልገኝም

|ያለፈን ላይቀይር በከንቱ ይለፋል|➋
መቼም ሰው ደፋር ነው ፈጣሪን ይጋፋል

|ትንሽ እልፍ ሲሉ እልፍ እየተገኘ|➋
ደሃ ነው በልቡ ሞቱን የተመኘ

ነ ነ ነ ነ ነ ነ ነነነ ነ ነነ ነነነ ነነነ ነነነ ነነነ
ነ ነ ነ ነ ነ ነ ነነነ ነ ነነ ነነነ ነነነ ነነነ ነነነ
ነ  ነነነ ነነነ ነነነ ነነነ

ለምን በትዝታ ኑሮዬን ገፋለሁ
|ለምን በትዝታ ኑሮዬን ገፋለሁ
 ኑሮዬን ገፋለሁ|➋
ማጣትም እንዳለ ለማግኘት ግዜ አለውማጣትም እንዳለ ለማግኘት ግዜ አለው


አቅም አለኝ ብሎ የሰው ልጅ ቢሰፍርም
|አቅም አለኝ ብሎ የሰው ልጅ ቢሰፍርም
 የሰው ልጅ ቢሰፍርም|➋
|ታሰበ አሰበ ከልኩ አያልፍም
ታሰበ አሰበ ከልኩ አያልፍም|➌

|አግኝቶ ላያገኝ ወይ ጠቅሞ ላይጠቅመው
ሰው ለምን ይኖራል ትዝታ ሲያደክመው|➋
 
©ከቢኒኦኔ ገብሬ
join  -   👇

💚  @binionae 💚
💛  @binionae 💛
 ❣    @binionae
   


      ኣ.ኣ
ወንድም ባይታሰር ፤ ባይጎድል ስጋ ዘመድ
በእንቶፈንቶ ምክንያት ፤ በምናምን ልማድ
ይህ ድምፅ ይሰማኛል ፤ አባቢ የታለ የሚሉ ህፃናት
ልጄ እንዴት ይሆን ፤ ምትል ምስኪን እናት
በፍቅር የተሞላ ፤ የረዘመ ፀሎት ።
በሸገር ጣሪያ ስር ፤ አንድ ሰው አጉድለህ
ከቀዬው ወስደኸው ፤ ከቤቱ ነጥለህ
ለትምህርት ነው አልከኝ ፤ ስለሰላም ብለህ?
እውነት ትገርማለህ ፤ ልብ ትሰብራለህ !
መ'ልስ! !
ለሚስት ባሏን ልቀቅ ፤ ለህፃናቱም አባት
ለእናት ልጇን ሰደህ ፤ ይልቅ እረፍት ስጣት

ከየሰዉ ጓዳ የተነቀለውን ፤ የየቤቱን ዋርካ
የጎደለን አድባር ፤ ይቅር ብለህ ተካ ።
እስራኤል ፀጋዬ(እስ)
       
©ከቢኒኦኔ ገብሬ
join  -   👇

💚  @binionae 💚
💛  @binionae 💛
 ❣    @binionae
   


Репост из: ፍኖተ ሳዊሮስ መንፈሳዊ ማኅበር
                  ** የጠፍው **
የጠፋው ታሪኬ ለካስ አፍሮ ነበረ
    በራሱ ሲዋረድ አንገቱን የሰበረ
ሚስጥሩን ደብቆ ከአይን የተሰወረ
ጥበቤን አርክሼ አንኳስሼ አይቼ
የሰውን ሳዳንቅ ማንነቴን ዘንግቼ
በየዋሁ ልቤ ጥላቻን ቢሞሉኝ
ሂሊናዬ ታወረ ማስተዋሉ ከበደኝ
እራሴን ጠላሁ ሌላ መሆን ተመኘሁ
     ባለማወቅ መስሎኝ እድሜዬን
      በከንቱ የገፋሁ
ከቤቴ  አውጥቼ በር አፌን ዘግቼ
አባረርኩ ጥበቤን ክብሯን አዋርጄ
ይሉንታዬን ትቼ
ድንበርን ተሻግራ ዘምና ተራቃ
ስሟንም ለዉጣ ማንነቷን ለቃ
በባአድ ምድር ላይ ቁልፍ ስትሆን መክፈቻ
                    እኔ ያባረርኳት ንቄ በጥላቻ
ሳያት ጥበቤን ጊዜ እድል ሲወልድ
ወርቄን ማሰገሬ በክፋት ወጥመድ
የዘመን ስተቴ በዘመን ሲገለጥ
በቁጭት ወቂኖስ ሂሊናዬ ሲሰምጥ
የጠፋዉ ታሪኬ የእኔ ስልጣኔ
ይቅር በለኝ ባክህ ይሰማህ ሀዘኔ
አዉቂያለሁ ዛሬ ገብቶኛል ጥፋቴ
ዞርኩኝ ወደኋላ ጎዳኝ ማየት ፌቴ
ላልደርስ ዘላለሜን በከንቱም አልተጋ
        እራሴን ልፈልግ ጨለማዬ ይንጋ ::
©ከቢኒኦኔ ገብሬ

join  -   👇
💚  @binionae 💚
💛  @binionae 💛
 ❣    @binionae

Показано 20 последних публикаций.

6

подписчиков
Статистика канала