ኤሎሄ
ይሄውልሽ ጉዴ ብሎ ቢል ገጣሚው
ቃላቶቹ ገዙኝ ፡
አንቺጋ እደርስ እንደሆነ በጥበብ
ሊያስጉዙኝ ፡፡
አውቃለው መደረስ እንደሌለለ
አውቃለው ሩቅ ነሽ፡
መሆኑን አውቃለው ጥበበኛው እሱ
እግዜር የከለለሽ።
ቢሆንም
በሆሄ እንድስልሽ በምናብ እንዳይሽ
በጥበብ ባረከኝ በቃል እንዲፈጥርሽ
የቃላትን ሀይል እንድረዳ
ጥበብን በስንኝ እንድቀዳ
አንቺን ነሳኝእና ቃላት አስነከሰኝ
ብዕር እንዳነሳ ብሶት አቀመሰኝ
አይ እግዜሩ
እውነት ቸርነት ነው? ደግነት ነው ይሄ
ፅዋህን አንሳልኝ አባት ሆይ ኤሎሄ።
by kerim
@poem2513
@getem
@getem
@getem
ይሄውልሽ ጉዴ ብሎ ቢል ገጣሚው
ቃላቶቹ ገዙኝ ፡
አንቺጋ እደርስ እንደሆነ በጥበብ
ሊያስጉዙኝ ፡፡
አውቃለው መደረስ እንደሌለለ
አውቃለው ሩቅ ነሽ፡
መሆኑን አውቃለው ጥበበኛው እሱ
እግዜር የከለለሽ።
ቢሆንም
በሆሄ እንድስልሽ በምናብ እንዳይሽ
በጥበብ ባረከኝ በቃል እንዲፈጥርሽ
የቃላትን ሀይል እንድረዳ
ጥበብን በስንኝ እንድቀዳ
አንቺን ነሳኝእና ቃላት አስነከሰኝ
ብዕር እንዳነሳ ብሶት አቀመሰኝ
አይ እግዜሩ
እውነት ቸርነት ነው? ደግነት ነው ይሄ
ፅዋህን አንሳልኝ አባት ሆይ ኤሎሄ።
by kerim
@poem2513
@getem
@getem
@getem