የደስታ ሰማይ - በር መክፈቻ፣
ይገኛል መስሎሽ - በመብረር ብቻ፣
በተዋስሽው ክንፍ - ሽቅብ ስትመጥቂ፣
የደመና ሆድ ስትሰነጥቂ ፣
(ድንገት ከአየር ላይ)
በባለ ክንፉ - ስትነጠቂ፥
በማይገመት - በማይጠበቅ ፣
በእድል ጨፈቃ - በጊዜ ለበቅ፣
በጊዜ ለበቅ - በማይመከት፣
ስትገረፊ -
ደንግጠን ሽቅብ - ስንመለከት፣
ስንመለከት የማታ ማታ፥
ያዘልሽው ላባ -
የአንቺ እንዳልሆነ - ትዝ ያለሽ ለታ፥
ወዮ የዛን 'ለት - ለመንደራችን፤
ወዮ ለመሬት፥
ወዮ ለጆሮ - ወዮ ለዐይናችን፤
By Michael Minassie
@getem
@getem
@paappii
ይገኛል መስሎሽ - በመብረር ብቻ፣
በተዋስሽው ክንፍ - ሽቅብ ስትመጥቂ፣
የደመና ሆድ ስትሰነጥቂ ፣
(ድንገት ከአየር ላይ)
በባለ ክንፉ - ስትነጠቂ፥
በማይገመት - በማይጠበቅ ፣
በእድል ጨፈቃ - በጊዜ ለበቅ፣
በጊዜ ለበቅ - በማይመከት፣
ስትገረፊ -
ደንግጠን ሽቅብ - ስንመለከት፣
ስንመለከት የማታ ማታ፥
ያዘልሽው ላባ -
የአንቺ እንዳልሆነ - ትዝ ያለሽ ለታ፥
ወዮ የዛን 'ለት - ለመንደራችን፤
ወዮ ለመሬት፥
ወዮ ለጆሮ - ወዮ ለዐይናችን፤
By Michael Minassie
@getem
@getem
@paappii