..........
በመዳፌ ጠፈር ዳሳሽ
በኣይኖቼ ህዋን አሳሽ
አፈር ድንጋዩን መርማሪ
ፀሀይን በጥፊ ኣብራሪ
ጨረቃን በኩርኩም ቀባሪ
በውርቅያኖስ የምግሞጠሞጥ
ከንፋስ እጥፍ የምሮጥ
ጉም ዘጋኝ በመዳፌ
በኖህ መርከብ ቀዝፌ
ከጥፋት ውሀ ተርፌ
ቅንጥብ ዘንባባ ቀጥፌ
ኣዲስ ምዕራፍ የማበስር
ብኩርናዬን የማልሸጥ በምስር
በኮከብ ወደም ምጫወት
የማድር ከኣብርሀም ቤት
እንግዳ ያልሆንኩኝ እንግዳ
የሩቅ ዘመድ የቅርብ ባዳ
ከጲላጦስ ሸንጎ የምፋረድ
በደመና ይምራመድ
ከሰባሰገሎች ኣንዱ
ወርቅ እጣን ከርቤ የገበረ
ንጉሱን ከበረት ኣይቶ እረኛውን ያከበረ
ከድንጋይ ከህጻናት ጋር
ሆሳእና ብሎ የዘመረ
እኔ ነኝ ብኩኑ ባሪያህ የጥበብህ ማሳያ
የሀዲስ ኪዳን ነብይ የኦሪት ሀዋርያ
በሀሳቤ እሩቅ ተጎዝ
ባካሌ ከቅርብ የማድር
ቅንጣት እምነት የጎደለኝ
የሚነቅል የተራራን ስር
እንኳንስ በደመና ላይ
በጠፈር ሰማይ ምድሩ
ሸክም ሆኖ የከበደኝ
የኣካሌ ክፋይ ኣፈሩ
ጉም መጨበጥ የምመኝ
የእጄን መና ለቅቄ
በሀሳብ ከኣብርሀም ያደርኩ
ከመንገድ መሀል ወድቄ
በኮከብ ወደሙ ቀርቶ
ጠጠር ማንሳት ያቃተኝ
ፍቅር መስቀል ይመስል
በየቀን የሚያቃትተኝ
አንድ ቀን ጠግቦ ለማደር
ብኩርናዬን የምሰዋ
ባገሬ መኖር ያቃተኝ
እንኳን በጠፈር ህዋ
ኣንድ ጉንጭ ውሀ የምለምን
ውርቂያኖስ መሉ ተፍቼ
ከሰገባ የማድር
ከስልክ እንጨት ስር ተኝቼ
ከጥፋት ውሀ ታዳሚ
ወይ ኣልድን ወይ ሰጥሜ ኣልሞት
እስትንፋስ አልባ የሆነ
የምኖሮ ትርጉም ኣልባ ህይወት
የኖህም መርከብ የራቀኝ
ለምግብ ጥንብ ኣንሳ የነቀኝ
መሲህ ፍለጋ ወጥቼ
ነብይ ይዜ የተመለስኩ
ሰባሰገል ተብዬ
ከሄሮድስ ጭፍሮች ያበርኩ
እንኳንስ ፀሀይ በጥፊ
ውቧን ጨረቃ በኩርኩም
ዝንብ ሽ ማለት ያቃተኝ
ሀሳቤ ብናኝ እንደ ጉም
እኔ ነኝ ብኩኑ ፍጡርህ
በህልሜ ሁሌ ከደጅህ
ስነቃ ከተራራው ስር
ደራሽ በሌለበት ምድር
በሲቃ ድምጽ የምጣራ
ከመብረቅም በሚያስፈራ
የቅንጣት እምነቴ ተራራ ኣነቅል ቢለኝ
ተራራ ያሸከመኝ
ከገነት ያላደርኩ ከሲኦል ያልገባው
መሲሁን ጠቋሚ ኣንድ ኮከብ ያጣው
ወይ ድኜ ኣልድን ከስሜ አልጠፋ
ከፈራጅ ችሎት ዳኛ የማስከፋ
እኔ ነኝ ብኩኑ ፍጡርህ
ወድቄ ያለው ከግርህ
ፍቅርህን የምሻ ልቤን ኣሽችቼ
ልክ እንደ ኣይሁድ ጎኑን ወግቼ
ከእቅፍህ ውስጥ ማደር የምመኝ
ብኩኑ ልጅህ
ባሪያህ እኔ ነኝ
By @Mad12titan
@getem
@getem
@getem
በመዳፌ ጠፈር ዳሳሽ
በኣይኖቼ ህዋን አሳሽ
አፈር ድንጋዩን መርማሪ
ፀሀይን በጥፊ ኣብራሪ
ጨረቃን በኩርኩም ቀባሪ
በውርቅያኖስ የምግሞጠሞጥ
ከንፋስ እጥፍ የምሮጥ
ጉም ዘጋኝ በመዳፌ
በኖህ መርከብ ቀዝፌ
ከጥፋት ውሀ ተርፌ
ቅንጥብ ዘንባባ ቀጥፌ
ኣዲስ ምዕራፍ የማበስር
ብኩርናዬን የማልሸጥ በምስር
በኮከብ ወደም ምጫወት
የማድር ከኣብርሀም ቤት
እንግዳ ያልሆንኩኝ እንግዳ
የሩቅ ዘመድ የቅርብ ባዳ
ከጲላጦስ ሸንጎ የምፋረድ
በደመና ይምራመድ
ከሰባሰገሎች ኣንዱ
ወርቅ እጣን ከርቤ የገበረ
ንጉሱን ከበረት ኣይቶ እረኛውን ያከበረ
ከድንጋይ ከህጻናት ጋር
ሆሳእና ብሎ የዘመረ
እኔ ነኝ ብኩኑ ባሪያህ የጥበብህ ማሳያ
የሀዲስ ኪዳን ነብይ የኦሪት ሀዋርያ
በሀሳቤ እሩቅ ተጎዝ
ባካሌ ከቅርብ የማድር
ቅንጣት እምነት የጎደለኝ
የሚነቅል የተራራን ስር
እንኳንስ በደመና ላይ
በጠፈር ሰማይ ምድሩ
ሸክም ሆኖ የከበደኝ
የኣካሌ ክፋይ ኣፈሩ
ጉም መጨበጥ የምመኝ
የእጄን መና ለቅቄ
በሀሳብ ከኣብርሀም ያደርኩ
ከመንገድ መሀል ወድቄ
በኮከብ ወደሙ ቀርቶ
ጠጠር ማንሳት ያቃተኝ
ፍቅር መስቀል ይመስል
በየቀን የሚያቃትተኝ
አንድ ቀን ጠግቦ ለማደር
ብኩርናዬን የምሰዋ
ባገሬ መኖር ያቃተኝ
እንኳን በጠፈር ህዋ
ኣንድ ጉንጭ ውሀ የምለምን
ውርቂያኖስ መሉ ተፍቼ
ከሰገባ የማድር
ከስልክ እንጨት ስር ተኝቼ
ከጥፋት ውሀ ታዳሚ
ወይ ኣልድን ወይ ሰጥሜ ኣልሞት
እስትንፋስ አልባ የሆነ
የምኖሮ ትርጉም ኣልባ ህይወት
የኖህም መርከብ የራቀኝ
ለምግብ ጥንብ ኣንሳ የነቀኝ
መሲህ ፍለጋ ወጥቼ
ነብይ ይዜ የተመለስኩ
ሰባሰገል ተብዬ
ከሄሮድስ ጭፍሮች ያበርኩ
እንኳንስ ፀሀይ በጥፊ
ውቧን ጨረቃ በኩርኩም
ዝንብ ሽ ማለት ያቃተኝ
ሀሳቤ ብናኝ እንደ ጉም
እኔ ነኝ ብኩኑ ፍጡርህ
በህልሜ ሁሌ ከደጅህ
ስነቃ ከተራራው ስር
ደራሽ በሌለበት ምድር
በሲቃ ድምጽ የምጣራ
ከመብረቅም በሚያስፈራ
የቅንጣት እምነቴ ተራራ ኣነቅል ቢለኝ
ተራራ ያሸከመኝ
ከገነት ያላደርኩ ከሲኦል ያልገባው
መሲሁን ጠቋሚ ኣንድ ኮከብ ያጣው
ወይ ድኜ ኣልድን ከስሜ አልጠፋ
ከፈራጅ ችሎት ዳኛ የማስከፋ
እኔ ነኝ ብኩኑ ፍጡርህ
ወድቄ ያለው ከግርህ
ፍቅርህን የምሻ ልቤን ኣሽችቼ
ልክ እንደ ኣይሁድ ጎኑን ወግቼ
ከእቅፍህ ውስጥ ማደር የምመኝ
ብኩኑ ልጅህ
ባሪያህ እኔ ነኝ
By @Mad12titan
@getem
@getem
@getem