በድቅድቅ ጨለማ ወንበሬን አውጥቼ
መሀል መሬት ላይ ጨረቃ እሞቃለው
ወፎች ሲዘምሩ ቁጭ ብዬ አደምጣለው
ወደ ላይ ቀና ስል...
የጨረቃ ብርሃን አይኔን ይወጋኛል
ሙቀቷ እሳት ሁኖ በላብ ያጠምቀኛል
''አ ዎ! አሁን ይበቃኛል''
''ከዚ በላይ ብቆይ ምቀልጥ ይመስለኛል''
ብዬ አሰብኩና...
ጥላውን ፍለጋ ወደ ቤቴ ገባው
ከቆጡ አልጋዬ ለመተኛት ሳስብ...
የ አልጋው ዝቅታ ሰላም ስላልሰጠኝ
ከፍ ካለው ቁርበት ከላይ ተንጋለልኩኝ..
አይኖቼን ገልጬ ድብን ብዬ ተኛሁ
ሰዉን እየረበሽኩ በደንብ አንኮራፋሁ
እንቅልፌ ሲመጣ ...
እንቅልፌ ሲመጣ ከ ሰመመን ነቃሁ;
ነግቷል መሰለኝ ሰማዩ ጨልሟል
ኮከቦችም አሉ ደመናም ደምኗል
ሊዘንብ ነው መሰል ልብሴን ቶሎ ላስጣ
ዝናብ ዘንቦ ሳያልቅ ፀሀይዋ ሳትመጣ::
✍ ዘይድ ሁሴን
ታህሳስ -15 -2017
@getem
@getem
@getem
መሀል መሬት ላይ ጨረቃ እሞቃለው
ወፎች ሲዘምሩ ቁጭ ብዬ አደምጣለው
ወደ ላይ ቀና ስል...
የጨረቃ ብርሃን አይኔን ይወጋኛል
ሙቀቷ እሳት ሁኖ በላብ ያጠምቀኛል
''አ ዎ! አሁን ይበቃኛል''
''ከዚ በላይ ብቆይ ምቀልጥ ይመስለኛል''
ብዬ አሰብኩና...
ጥላውን ፍለጋ ወደ ቤቴ ገባው
ከቆጡ አልጋዬ ለመተኛት ሳስብ...
የ አልጋው ዝቅታ ሰላም ስላልሰጠኝ
ከፍ ካለው ቁርበት ከላይ ተንጋለልኩኝ..
አይኖቼን ገልጬ ድብን ብዬ ተኛሁ
ሰዉን እየረበሽኩ በደንብ አንኮራፋሁ
እንቅልፌ ሲመጣ ...
እንቅልፌ ሲመጣ ከ ሰመመን ነቃሁ;
ነግቷል መሰለኝ ሰማዩ ጨልሟል
ኮከቦችም አሉ ደመናም ደምኗል
ሊዘንብ ነው መሰል ልብሴን ቶሎ ላስጣ
ዝናብ ዘንቦ ሳያልቅ ፀሀይዋ ሳትመጣ::
✍ ዘይድ ሁሴን
ታህሳስ -15 -2017
@getem
@getem
@getem