“ስኬተኛ ማነው ?”
ብዬ ጠየቅኋቸው
ታዋቂ አመጡልኝ
ይሄ ነው መልሳቸው ።
አልተዋጠልኝም !
አልተረቱልኝም …
አሳዩኝ ከበርቴ
ባለ ንብረት ፣ ነዋይ
እንደዚህ ያለውን
ቀና ብዬም አላይ።
አልተዋጠልኝም !
አልተረቱልኝም …
አመጡልኝ ምሁር
ፊደል የቆጠረ
የተመራመረ
ይሄም አልሰመረ።
አልተዋጠልኝም !
አልተረቱልኝም …
ጠሩ ባለ ጥበብ
በጥሁፍ በቅኔ
ያስገኘልን ረብ
(በርግጥ ጥሩ ነበር
እንደዚህ ሲታሰብ )
መልስ ግን አይደለም።
አልተዋጠልኝም !
አልተረቱልኝም …
አንድ አጩ ቀጥሎ
ጽድቁን አደላድሎ
ያናናቀ ሞቱን…
የቃል ጥሩር ለብሶ
ያስታጠቀ ነፍሱን…
አገኙብኝ መልሱን !
(ሚካኤል አ)
@getem
@getem
@getem
ብዬ ጠየቅኋቸው
ታዋቂ አመጡልኝ
ይሄ ነው መልሳቸው ።
አልተዋጠልኝም !
አልተረቱልኝም …
አሳዩኝ ከበርቴ
ባለ ንብረት ፣ ነዋይ
እንደዚህ ያለውን
ቀና ብዬም አላይ።
አልተዋጠልኝም !
አልተረቱልኝም …
አመጡልኝ ምሁር
ፊደል የቆጠረ
የተመራመረ
ይሄም አልሰመረ።
አልተዋጠልኝም !
አልተረቱልኝም …
ጠሩ ባለ ጥበብ
በጥሁፍ በቅኔ
ያስገኘልን ረብ
(በርግጥ ጥሩ ነበር
እንደዚህ ሲታሰብ )
መልስ ግን አይደለም።
አልተዋጠልኝም !
አልተረቱልኝም …
አንድ አጩ ቀጥሎ
ጽድቁን አደላድሎ
ያናናቀ ሞቱን…
የቃል ጥሩር ለብሶ
ያስታጠቀ ነፍሱን…
አገኙብኝ መልሱን !
(ሚካኤል አ)
@getem
@getem
@getem