ወዳንቺ እዘረጋለሁ!
ባድግ ብዬ
ባውቅ ብዬ
አንዳች ምስጢር ተረድቼ ባልፍ ብዬ!
መቃብር ቤቴን ማሞቂያ
የሙት መንደሬን ማድመቂያ
ካለፉም ወዲያ መታወቂያ…
የምትሆን
አንድ ሀተታ
አንድ እውነታ
የህይወትን ምናልባት
የመኖርን እልባት
አውቃት ነበር እንድልባት
ወዳንቺ እዘረጋለሁ!
ከሰማይ በታች አዲስ ነገር
ከምድር ከፍ ብሎ የሚነገር
“የከንቱ ከንቱ” የምትባል
የአላዋቂን ፈላስፋ
በአፍጢሙ የምትደፋ
ስታቅፊ ዐለም እንደሚጠቀለል
ስትገፊም ሰውነት ከላባ እንደሚቀል
ስትስሚ ኢምንት እንዲሆን ጠፈሩ
ስትነክሺም ማንነት እንደሚበተን አፈሩ…
ይቺን ምስጢር ተረድቼ ባልፍ ብዬ
የህይወት መስመሬን ማንቂያ
ውሎ አዳሬን መደበቂያ
ተስፋ ህልሜን መታረቂያ
የምትሆን
አንዲት ሁነት
አንዲት ኪነት
የመክረምን ፍልስምና
ከንቱነት ላይ ውብ አድርጋ ሸምና
ታውቀኝ ነበር እንድልባት
ወዳንቺ እዘረጋለሁ ካልተረሳሁ ምናልባት።
By Yadel Tizazu
@getem
@getem
@paappii
ባድግ ብዬ
ባውቅ ብዬ
አንዳች ምስጢር ተረድቼ ባልፍ ብዬ!
መቃብር ቤቴን ማሞቂያ
የሙት መንደሬን ማድመቂያ
ካለፉም ወዲያ መታወቂያ…
የምትሆን
አንድ ሀተታ
አንድ እውነታ
የህይወትን ምናልባት
የመኖርን እልባት
አውቃት ነበር እንድልባት
ወዳንቺ እዘረጋለሁ!
ከሰማይ በታች አዲስ ነገር
ከምድር ከፍ ብሎ የሚነገር
“የከንቱ ከንቱ” የምትባል
የአላዋቂን ፈላስፋ
በአፍጢሙ የምትደፋ
ስታቅፊ ዐለም እንደሚጠቀለል
ስትገፊም ሰውነት ከላባ እንደሚቀል
ስትስሚ ኢምንት እንዲሆን ጠፈሩ
ስትነክሺም ማንነት እንደሚበተን አፈሩ…
ይቺን ምስጢር ተረድቼ ባልፍ ብዬ
የህይወት መስመሬን ማንቂያ
ውሎ አዳሬን መደበቂያ
ተስፋ ህልሜን መታረቂያ
የምትሆን
አንዲት ሁነት
አንዲት ኪነት
የመክረምን ፍልስምና
ከንቱነት ላይ ውብ አድርጋ ሸምና
ታውቀኝ ነበር እንድልባት
ወዳንቺ እዘረጋለሁ ካልተረሳሁ ምናልባት።
By Yadel Tizazu
@getem
@getem
@paappii