..........
ቀለም
ጸሀይ አይደለችም የቸረች ተፈጥሮን
ውበቷ ነው እንጂ ጨለማን ሰውሮን
በነጭና ጥቁር
በበዛበት ህይወት
ተፈጥሮን በረሳ ቀለም በናፈቀው
ጸሀይ አይደለችም
ገላሽን አቅፎ ነው ጓዳዬ የሞቀው
ቤቴ የደመቀው
ያልተጋሩት እቶን
የሚማገዱበት ልክ እንደ ዕሳት ዕራት
ሞቶ የመኖር ብስራት
በብርሀኗ ውስጥ በሚንቦገቦገው
ፍቅርን ልፈልገው
ስዳራሽ እያዩ
ሞቶ ነው እያሉ ህያዋን ሲለዩ
ለዚህ ነው የምልሽ
ቀለም
ጸሀይ አይደለችም የሰጠች ተፈጥሮን
ውበቷ ነው እንጂ ጨለማን ሰውሮን
በሳት ላልተዳሩ
ላልተፋቀሩ!
ቅሉ አይገባቸውም የቀለም አደሱ
የፍቅራቸው ምሱ ?
ዕሳት ዕራት መሆን ጸጋ መች ታደለ
ከሚነድ ወላፈን ጠብታን ያከለ
ለዕሳት ነፍስ የዘራ ስጋውን ሰውቶ
ጸሀይ አይደለችም
ውበቷ ብቻ ነው የሚታየው ጎልቶ
By @mad12titan
@getem
@getem
@getem
ቀለም
ጸሀይ አይደለችም የቸረች ተፈጥሮን
ውበቷ ነው እንጂ ጨለማን ሰውሮን
በነጭና ጥቁር
በበዛበት ህይወት
ተፈጥሮን በረሳ ቀለም በናፈቀው
ጸሀይ አይደለችም
ገላሽን አቅፎ ነው ጓዳዬ የሞቀው
ቤቴ የደመቀው
ያልተጋሩት እቶን
የሚማገዱበት ልክ እንደ ዕሳት ዕራት
ሞቶ የመኖር ብስራት
በብርሀኗ ውስጥ በሚንቦገቦገው
ፍቅርን ልፈልገው
ስዳራሽ እያዩ
ሞቶ ነው እያሉ ህያዋን ሲለዩ
ለዚህ ነው የምልሽ
ቀለም
ጸሀይ አይደለችም የሰጠች ተፈጥሮን
ውበቷ ነው እንጂ ጨለማን ሰውሮን
በሳት ላልተዳሩ
ላልተፋቀሩ!
ቅሉ አይገባቸውም የቀለም አደሱ
የፍቅራቸው ምሱ ?
ዕሳት ዕራት መሆን ጸጋ መች ታደለ
ከሚነድ ወላፈን ጠብታን ያከለ
ለዕሳት ነፍስ የዘራ ስጋውን ሰውቶ
ጸሀይ አይደለችም
ውበቷ ብቻ ነው የሚታየው ጎልቶ
By @mad12titan
@getem
@getem
@getem