ከ3 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ዘይትና ስኳር መወረሱ ተገለጸ
በሕገ-ወጥ መንገድ ተከማችቶ የተገኘ ከ3 ሚሊየን 52 ሺሕ 904 ብር በላይ የሚገመት የዘይትና ስኳር መውረሱን የየካ ክፍለ ከተማ የሕገ-ወጥ ንግድ ክትትልና ቁጥጥር ግብረ-ሃይል አስታውቋል።
የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 07 አስተዳደር የወረዳው ንግድ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሚር ከሊፋ እንደገለጹት ከፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ ንግድ ተቋም በክፍለ ከተማው ሕገ-ወጥ ንግድ ክትትልና ቁጥጥር ግብረ-ሃይል በተደረገ ክትትል በሕገ-ወጥ መንገድ ተከማችቶ የተገኘው የዘይትና ስኳር ተወርሷል።
አቶ አሚር አክለውም በፍተሻው ወቅት 149 ባለ 20 ሊትር ዘይት እና 304 ኩንታል ስኳር መያዙን ተናግረዋል።
የተወረሱት ንብረቶችም በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ የሸማች ህብረት ሥራ ማህበራት ሱቆች በማከፋፈል ህብረተሰቡ እንዲጠቀምበት መደረጉን የጽ/ቤት ኃላፊው ገልጸዋል፡፡