Репост из: Bahiru Teka
👉 በረመዳን ከኛ ምን ይፈለጋል ?
በረመዳን ከኛ ምን እንደሚፈለግ ለማወቅ ረመዳን ለምን እንደ ተደነገገ ማወቅ ያስፈልጋል ። ረመዳን ከኛ በፊትም በነበሩት ህዝቦችና በኛ ላይም የተደነገገው አላህን እንድንጠነቀቀው ( እንድንፈራው ) ነው ። ይህን አስመልክቶ አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል : –
« يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُتِبَ عَلَيْكُمُ الصِّيَامُ كَمَا كُتِبَ عَلَى الَّذِينَ مِن قَبْلِكُمْ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ »
البقرة ( 183)
" እናንተ ያመናችሁ ሆይ ጾም በነዚያ ከናንተ በፊት በነበሩት (ሕዝቦች) ላይ እንደ ተጻፈ በናንተም ላይ ተጻፈ (ተደነባ) ልትጠነቀቁ ይከጀላልና " ፡፡
ይህን አንቀፅ መሰረት በማድረግ ዑለሞች ከፆም የሚፈለገው ዋነኛው ግብ ራስን ከስሜትና ከልማድ ነፃ ማውጣት ነው ይላሉ ። ይህ በጣም ሰፊ ትንታኔ የሚፈልግ አባባል ነው ። ለጥያቄያችንም መልስ ይሰጣል ።
ሁላችንም እስኪ ፍላጎታችንንና ልማዳችንን እንዲሁም በዙሪያችን ያሉ ሰዎችንም ፍላጎትና ልማድን እንመልከት ። የአውሮፓ ሊግ ብሎ ከቴሌ ሺዥን ስር ማፍጠጥ ፣ የሀገር ውስጥ ክለቦች ውድድሮች ለማየት እስታዲየም ማዘውተር ፣ አብዛኛውን ጊዜ ሞባይል ይዞ ጊዜ ማጥፋት ፣ የተለያዩ ፊልሞችና ድራማዎችን መመልከት ፣ በየሱቅ ደጃፍ ተሰባስቦ ወሬ ማውራት ፣ የተሻለ ነው የሚባለው መንዙማ መስማት ፣ ማታውን በጫትና መንዙማ ማሳለፍ ፣ ቀን አብዛኛውን ሳአት ተኝቶ ማሳለፍና የመሳሰሉት ይገኙበታል ።
እነዚህ ልማዶች ፆም ላይ ከቀጠሉ ከፆማችን የምናተርፈው ረሀብና ጥም ነው የሚሆነው ። ልክ እንደዚሁ ፍላጎታችንን መተው ይናርብናል ። የስሜታችን ታዛዥ ከሆንን ፆም የተደነገገበት አላማ አልገባንም ማለት ነው ። በመሆኑም በረመዳን ከኛ የሚፈለገው ከልማዳችንና ፍላጎታችን ተቆጥበን ቀኑን በፆም ለሊቱን በተለያዩ ዒባዳዎች እንድናሳልፍ ነው ።
ጫት መቃም ዒባዳ ሳይሆን እዳ ነው ። ጫት መቃምን ዒባዳ የሚሉ በተለይ የገጠሩ ቤተሰቦቻችን ከዚ ልማዳቸው እንዲላቀቁ መምከር ይኖርብናል ።
አላህ ካገራላቸው ባሮቹ ያድርገን ።
https://t.me/bahruteka