➡️ የምቀኝነት ክርፋት ግሳት
በየአንዳንዱ ሰው ውስጥ ምቀኝነት አለ ። አላህን የሚፈራው ታግሎ ይደብቀዋል ። ወራዳ ግን በአሳፋሪ ሁኔታ ግልፅ ያደርገዋል ። በዚህም ማንነቱን አገር ያውቀዋል ።
በሚሊኒየሙ ፕሮግራም ሲንጨረጨር የነበረው የሙነወር ልጅ በብስጭት በሚወራጩ ጣቶቹ የሞነጫጨረውን አንድ ወንድም ፎርዋርድ አድርጎልኝ ነበር ። በጣም የሚገርመው ይህ ሙንጭርጭር የተለጠፈው ኦክቶበር 10 መሆኑንም እስክሪን ሻት አድርጎ ልኮልኛል ። ‼ ለኛ የፕሮግራሙ መሸጋሸግ አስፈላጊነት የተነገረንና የለጠፍነው ኦክቶበር 11 ነው ። ታዲያ የሙነወር ልጅ ኦክቶበር 10 ላይ ስለፕሮግራሙ መስተጓጎል ያወራው በጥንቁልና ይሆን ወይስ እንዲስተጓጎል ካደረጉት አካላት ጋር ግንኙነት ነበረው ? መልሱን ለራሱ ።
የለጠፈበትን ቀን በሚቀጥለው ሊንክ ገብተው ይመልከቱ : – 👇👇👇👇👇👇👇👇
https://drive.google.com/file/d/1MMHa5GFqsFig27MDOEvvdWf81Q1ykjz9/view?usp=drivesdk አንድ ፅሑፍ መች እንደተለጠፈ ለማወቅ እስክሪኑ ላይ ፁሑፉን ትንሽ ወደታች ካደረጉት በኋላ በመጠኑ ተጭኖ ወደ ላይ ሲደረግ ከላይ ጫፍ ላይ ይመጣል ።
የሙነወር ልጅ ውስጡ ታምቆ ሲያስጨንቀውና አብጦ ሊፈነዳ የደረሰውን የምቀኝነት ክርፋት በማግሳት ሲያወጣው ካነሳቸው ነጥቦች ውስጥ ገና ከርእሱ እንዲህ ይላል : –
" እዩኝ ፣ እዩኝ ማለት ደብቁኝ ፣ ደብቁኝ ማለት ያመጣል " ።
ይህ አገላለፅ " ሸማተተል አዕዳእ " ( የጠላት መዘባበት ) ይባላል ። ለመሆኑ የሙነወር ልጅ ጠላትነቱ ለባሕሩ ወይስ ለዳዕዋው ? በምኑ ነው እየተዘባበተ ያለው ? ሌላው የተውሒድ ዳዕዋ አለ ብሎ ማስተዋወቅ እዩልኝ ማለት ነው ? ደብቁኝ የሚያሰኝ አሳፋሪ ስራ ስላልሰራን እንድንል የሚያደርገን ነገር የለም ። ይልቁንም ይበልጥ ወደፊት ነው የምንሄደው አላህ ካለ በውጤቱ ታየዋለህ ። የበለጥ ለመበሳጨት ተዘጋጅ !!!
በዚህ ነጥብ ላይ ብዙ በማለት አንባቢያንን ማሰልችት አልፈልግ ።
በመቀጠል ጥቂት ነጥቦችን ብታስተውሉ ብሎ ምክር በሚል ልብስ የተሸፈነ የማንነቱ ማሳያ መክሮችን እንዲህ እያለ ይዘረዝራል ። ከእነዚህ ውስጥ : –
– 2ተኛ ላይ ምክር በሚመስል መልኩ ብዙ ከሞነጨረ በኋላ ውስጡ ያለውን የተደበቀ ማንነቱን ሲገልፅ እንዲህ ይላል : –
" ብዙ ሰው ያላቸው አካላት ጋር ትከሻ እየተለካኩ ሲንገዳገዱ ከማዘን በአቅም ልክ ማሰብ ይሻላል "
ይህ እንግዲህ ነሲሓዎች ሚሊኒየም አዳራሽ ላይ ረመዳን መግቢያ አካባቢ አሕባሾችን ፣ ሱፍዮችን ፣ የኢኽዋን መሪዮችን የክብር እንግዳ አድርገው ጠርተው እነዚህን አካላት ዑለሞቻችን ፣ ዶክተራችን እያሉ ያሞካሹበትን ፕሮግራም ለማስታወስ ያደረገው ነው ። ለመሆኑ ከእነዚህ አካላት ጋር ትከሻ ስንለካካ የት ሆነህ ነበር ያየኸን ? የአቅም መለኪያህ ብዛት መሆኑን ማሳየትህን ከዚህ ነው የምትጀምረው ። የተከታይ ብዛት መኖር አቅም አፈርጥሞ የፈለጉትን ማድረግ እንዲቻል የያደርጋል በሚል ስሌት ነው ተከታይ ለማብዛት መከራህን እያየህ ያለኸው !!! ለመሆኑ ነሲሓዎች አንተ በምትለው መድረክ ላይ የክብር እንግዳ ብለው በጠሩት አካል የተዋጣላቸው ለማኞች ናቸው እኔ ካለሁበት አካባቢ በአንድ ቀን 8 ሚሊየን ብር ሰብስቧል ሲባሉ አድንቀሃቸው ነበር ማለት ነው? ዛሬ ስለአቅማቸው እያወራህ አድናቂ ተከታያቸው መሆንህን የምትገልፀው ። ወይስ ከነበርክበት አቋም ወርደህ እነርሱ ሰፈር እንትገባ ያደረገህ የሰለፍዮች ምስኪንነትና የእነርሱ በልመና ያካበቱት ሀብት ነው ? የኛ ሀገር አቀፍ የዳዕዋ ፕሮግራም በሀገሪቱ ዋና መዲና ላይ በሚሊኒየም አዳራሽ ለማድረግ መከራየት ለምን በዚህ መልኩ አስጨነቀህ ? እውነት የኛ አቅምና የተከታይ ማነስ አሳስቦህ ወይስ ነሲሓዎች እንዴት ተደፈሩ የሚል ስሜት ? አሁንም መልሱ ለራስህ ትቼዋለሁ ።
እይታህ እርስ በርሱ የሚጋጭ መሆኑ እዚህ ጋር ተከታያችን ትንሽ ሰለሆነ አቅም እንደሌለን እየነገርከን መልሰህ ደግሞ ስለኛ ተከታዮች ብዛት ሊቀንስ እንደሚችል ትተነብያለህ ።!!!
– 4ተኛ ላይ እንዲህ ይላል : –
" ኢኽላሳችሁን ፈትሹ ፣ የቀስድ መበላሸት ብዙ ነገር ያበላሻ " ‼
አቶ ኢብኑ ሙነወር አንተና አምሳያዎች ደጋግማችሁ ሰዎች የሆነ ሰራ በሰሩ ቁጥር ዘላችሁ ኢኽላስ የሌለው መሆኑን ለማሳየት ትጥራላችሁ ኧረ እንደውም መሀላ ሁሉ ይቃጣችኋል !!! ለመሆኑ በሰው ንያ ውስጥ ስላለ ነገር በዚህ መልኩ መቀባጠር የሩቅ ሚስጢር አውቃለሁ ማለት እንደሆነና ተውሒድን የሚያበላሽ መሆኑን ረስታችሁት ነው ወይስ የኪታቡ ተውሒድን መትን እንኳን አልቀራችሁም ?
– ወደ ማጠቃለያ አካባቢ ካነሳቸው ሁለት ነጥቦች ውስጥ መጀመሪያ ላይ እንዲህ ይላል : – " አንድ ነገርአስረግጬ ልንገራችሁ ። ቁጥራችሁ አሁን ካለውም የበለጠ እያነሰ ነው የሚሄደው "‼
ሱብሃነላህ የቁጥር ማነስና መብዛት እዚህ ድረስ ነው የሚያስጨንቅህ ? ቅድም ቁጥራችሁ ትንሽ ነው አቅም የላችሁም ከነሲሓዎች ጋር ትከሻ አትለካኩ እነርሱ ብዙ ተከታይ አላቸው ስትል ነበር ። አሁን ደግሞ የኛ ቁጥር መብዛ ምን ያክል እያስጨነቀህ መሆኑና ህልም ቀንሶ ማየት እንደሆነ በዚህ ልክ እየነገርከን ነው ። በመጀመሪያ ደረጃ ወደ ፊት ስለሚሆነው ነገር አስረግጬ ልንገራችሁ ብለህ የሩቅ ሚስጢር መናገርህን መቀጠልህ ከተውሒድ አስተምሮ ርቀህ ነሲሓዎች ስፈር መግባት በእንደነዚህ አይነት ትላልቅ የዐቂዳ ግድፈቶች ውስጥ እንድትዘፈቅ እንዴት እንዳደረገህ ተመልከት !!! ቢያንስ ተውበት አድርገህ ተመለስ ። ሌላው ከሚቀጥለው ነጥብ ጋር ስለሚመሳሰል አንድ ላይ እመልሰዋለሁ ።
– ከማጠቃለያ ነጥቦቹ ሁለተኛው አሁንም ከብዛት ጋር በተገናኘ እንዲህ ይላል : –
" በሆይሆይታ ያሰለፋችኋቸው መንጋዎች ወደ ቀልባቸው ሲመለሱ እናንተ ከምትሾፉሩት የስሜት ባቡር እየተንጠባጠቡ ይወርዳሉ ።‼
ይህ እያብከነከነው ያለውን ቁጥራቸው በዛ የሚለው የምቀኝነት እብጠት ክርፋት ያገሳህበት የመጨረሻ ሀሳብ ነው ። አሁንም በቁጭትህ ሙት እኛ ከቁጥር ጋር ግንኙነት የለንም ። አንተ የስሜት ባቡር ያልከው የሱና መርከብ ላይ ያሉ ሰዎች አላህ ያጠብቃቸውና ሳይሆን ቀርቶ ዛሬውኑ ከሱናው መርከብ ወርደው ባንተ የስሜት ባቡር ላይ ቢሳፈሩ ምንም አይመስለንም ። የአላህ መልእክተኛ የመካ አጋሪያኖች በስምምነቱ ላይ ከኛ ሰልሞ ወደናንተ የሄደውን ወደኛ ትመልሳላችሁ ከናንተ ከፍሮ ወደኛ የመጣውን ግን አንመልስም ሲሉዋችው የሰጡትን መልስ ነው ላንተም የምሰጥህ ።
የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ነበር ያሉት " አላህ ከእዝነቱ ያባረረው ሰው ወደኛ ቢመጣ ምን ያደርግልናል ከእነርሱ ወደኛ መጥቶ የሚመለሰው ግን አላህ መውጫ ያደርግለታል "።
ልክ እንደዚሁ ዛሬ ከሱናው መርከብ ተንጠባጥቦ ወርዶ ወደ ቢዳዓው ባቡራችሁ የተሳፈረ ለኛ ምን ያደርግልናል ። የቂያማ ቀን ነብይ ሆኖ አንድ ሰው ሳይከተለው ብቻውን የሚመጣ መኖሩን የአላህ መልእከተኛ የነገሩን የሱና ሰዎች ነንና ይህ ለኛ ምናችንም አይደለም ።
በመጨረሻም ይህን ስሜታችሁን አይተው ነው ኢኽዋንና ነሲሓዎች የተጫወቱባችሁ ። ለማንኛውም ከገባችሁበት የምቀኝነት አሮንቋ አላህ ያውጣችሁ የሚለው ዱዓችን ነው ።
http://t.me/bahruteka