📜 ማርች 8 የማጭበርበሪያ እና የትዝብት ቀን!
በጎርጎሮሳዊያኑ አቆጣጠር ማርች 8 (እንደሚሉት ከሆነ) በየአመቱ እንደ አለም አቀፍ የሴቶች ቀን ተብሎ የሚከበርበት ቀን ነው። በዚህ ቀን በርካታ መድረኮች እና ማህበራዊ ሚዲያዎች ስለ ሴቶች ክብር፣ መብት እና እኩልነት የመሳሰሉትን ያወራሉ። በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ኢስላምን እና ከሴቶች ጋር ያለው የተባረኩ ህግጋቶችን ይተቻሉ። ይህንን የኢስላም ህግን የሚጠብቁ ሀገሮችን፣ ተቋሞችን እና ቤተሰቦችን በጭቆና እና በመብት መንፈግ ይተቻሉ።
ኢስላም ማለት በየትኛውም ቦታ፣ ዘመን እና ሁኔታ ለሰው ልጆች የሚመጥ እና ዘመን የማይሽራው ሀይማኖት ነው። በዱንያም ይሁን በአኼራ ለሰው ልጆች መንፈሳዊም ይሁን ገሀድዊ ደስታ እና ስኬት መሰረት ነው። ከኢስላም ውጪ የሰዎች ጥቅም የሚያስጠብቅ ጉዳትን ደግሞ የሚያስወግድ እና የሚከላከል ሀይማኖት በጭራሽ የለም። ፈጣሪም ዘንድ ተቀባይነት ያለው ከአደም ጀምሮ ከሰማይ የተዘረጋ ብቸኛ ሀይማኖት ኢስላም ነው። አይሁዳዊነት፣ ክርስትና እና ሌሎችም ሀይማኖቶች በሰውልጆች ጠባብ አእምሮ መሰረት የተፈበረኩ ድርሰቶች ናቸው።
ኢስላም ለሴቶች (በተለይም ለእናት) ለየት ያለ እይታ አለው። ለሴቶች ወደር የሌለው እንክብካቤ አለው። ለመጀመርያ ግዜ የድንቁርናውን ዘመን የጭቆና ቅንበርን ከሴት ልጅ ጫንቃ ላይ ያነሳው ኢስላም ነው። ኢስላም ለሴቶች ያለው ትኩረት ትልቅ ለመሆኑ በቁርአን ውስጥ በነሱ ስም «የሴቶች ምእራፍ» የሚባል ምእራፍ መኖሩ ማሳያ ነው። በየትኛውም ሀይማኖት ውስጥ ባልታየ መልክ በመርየም ስምም ሱራ አለ። ለሴት ልጅ የሚገባትን እንክብካቤ እና ክብር እንዲሰጣት ያደረገው ኢስላም ነው። ኢስላም ለሴቶች ያለውን ክብር እና ቦታ ለማወቅ የፈለገ ሰው የታላቁን ፈጣሪ መፅሀፍ ቁርአንን እንዲሁም የነብያዊ ጥቅሶችን በንፁህ አእምሮ ያጥና። በተጨማሪም በርካታ የሆኑ የሊቃውንቱን ድርሰቶችን ያጥና።
ምእራባውያን የኢስላምን ትልቅነትንና መለኮታዊነት ባወቁ ግዜ የሚችሉ መስሏቸው ኢስላምን ለማጣጠል እና ለማንቋሸሽ ብለው ካጠመዷቸው በርካታ ወጥመዶች መካከል አንዱ ማርች 8 ነው። ብዙ ሰዎች (በተለይም ሴቶች) በዚህ ቀን ማላዘብ የምር ለሴቶች ክብር እና መብት የተጨነቁ ይመስላቸዋል። አመቱን ሙሉ የሚደረገው የመብት መግፈፍ እና ጭቆናን በአንድ ቀን መዝሙር ይረሱታል። በተቃራኒ ደግሞ ያለውን ተጨባጭ እና እውነታ የሚያውቁ በርካታ ሰዎች አመቱን ወደሃላ በማሰብ ይህንን ቀን እና የዚህ ቀን ወሬን ታዝበው ያልፋሉ።
ሴቶች ላይ የሚደርሱ ጭቆናዎች በጣም በርካታ ናቸው። በየቦታው የሚታየው የብዙሀኑን ሴት መብት የገፈፈው የኒቃብ መልበስ እገዳ እና ከሱ ጋር ተያያዥ የሆኑ በርካታ እገዳዎች (ለምሳሌ የት/ት እገዳ) ማሳያ ናቸው። መልበስ ተፈጥሯዊ እና ሰብአዊ መብታቸው አልነበረም ለምን ይታገዳሉ?! በብስለት ላጤነ ሰው ሴት ልጅን እንድትራቆት፣ ከተቃራኒ ፆታ ጋር ልቅ የሆነ መስተጋብር እንዲኖራት እና ከወንደንዶች ጋር የተለያዩ መድረኮችን እንድትጋራ መፍቀድ ከዚህ በላይ ክብሯን ዝቅ ማድረግ የለም። ከዚህም ባሻገር በየሆስፒታሉ ከወሊድ ጋር በተያያዘ ተገቢውን ክትትል ባለማግኘት እና የሴት አዋላጆች እጥረት ምክንያት በርካታ እናቶች ህይወታቸው ያልፋል። በየመስሪያ ቤት ስራ ፍለጋ ከቀረበች ወይ ውድድር ውስጥ ከገባች በተለይ ሙስሊም ከሆነች ካልተገላለጠች፣ ሴትነቷን ካልሸጠች ወይም ሌላ መጥፎ ነገር ውስጥ ካልገባች ስኬታማ አትሆንም። አረ በሴቶች ላይ የሚደርሰው ጭቆና ብዙ ነው። ይሄ ሁሉ በሚታይበት የሴቶች መብት እያሉ ማላዘብ ማጭበርበሪያ እንጂ ምንም አይደለም።
በዚህ ዘመን የሴት ልጅን መብት እናስከብራለን በሚል ሽፋን እንድትገላለት፣ እንድትራቆት፣ ከወንድ ጋር እንድትቀላቀል፣ ሚዲያ ላይ እንድትወጣ፣ በቴሌ-ቪዥን መስኮት እንድትታይ ወዘተ የሚያደርጉ ሰዎች እያረከሷት ነው። ከዚህም አልፎ በተለያዩ ምርቶች ላይ ፎቶዋን በመለጣጠፍ ማሻሻጪያ ብልጭልጭ አድርገዋታል። ይሄ ሁሉ ባለበት ማርች 8 የበለጠ ከዚህ በላይ እንድትረክስ የሚደረግበት እንጂ ሌላ አይደለም። ሴትን ልጅ ወደ ክብሯ ወደ ልእልትነቷ መመለስ የሚቻለው ወደ ኢስላም በመዞር ቢቻ ነው። የሷን መብት እና ልቅናን ማስጠበቅ የሚቻለው ወደ መሸፋፈኗ፣ ከጥፋት ስፍራ በመራቋ፣ ሴትነቷን በመጠበቋ እንዳጠቃላይ የኢስላምን መርህ በጠበቀ መልኩ ሲሆን ቢቻ ነው።
✍ ሙሀመድ አል-ወልቂጢይ
t.me/abuzekeryamuhamed