ኀዲጎ ተስዓ ወተሳዕተ ነገደ
ቆመ ማዕከለ ባሕር
ዘጠና ዘጠኙን የመላእክት ነገድ ትቶ አንዱን አዳም ሊፈልግ ወደ ምድር መጣ። በዮርዳኖስ ባሕር መካከልም ቆመ። በፍጡሩ እጅ ተጠምቆም ጥምቀት እንደሚገባ አስተማረን። በዮርዳኖስ የተሠወረውን የአዳምን የእዳ ደብዳቤም ደመሰሰ።
በዚያም አብ ድምፁን ከሰማይ አሰማ። መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል ወረደ። እግዚአብሔርም የመለኮቱን ምስጢር ገለጠልን። ከብሉይክ ዘመን ጀምሮ ከሰዎች ተሰውሮ የነበረው የእግዚአብሔር ባሕርይ፣ የአንድነቱና ሶስትነቱ ምስጢር፤ አባቶቻችን ለዘመናት ሽተው ያላዩት የመለኮት ምስጢር በዚች ቀን ተገለጠ። እግዚአብሔር አብ ከሰማይ በድምጹ፣ እግዚአብሔር ወልድ በዮርዳኖስ መካከል በሥጋ፣ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል ተገልጠው አንድነታቸውን ሶስትነታቸውን አሳዩን። ስለዚህም አባቶቻችን የዚህችን ቀን ስም "አስተርእዮ" ወይም የመገለጥ በዓል አሏት።
እንኳን አደረሳችሁ!!