ኦሪጂናል ሲን ወይም ጥንተ አብሶ የሚባለው የካቶሊኮች አስተምህሮ ሲሆን የሰው ልጆች በሙሉ የአዳምን እና የሄዋንን ሃጢአት ወርሰናል የሚል ነው። በዚህም ምክንያት ሁላችንም የውርስ ሃጢአት አለብን ይላል። ነገር ግን ይህ አስተምህሮ የካቶሊኮች አስተምህሮ እና የኛ ቤትክርስቲያንም ሆነ የምስራቅ ኦርቶዶክሶች የማያምኑበት የተሳሳተ አስተምህሮ ነው። ይህንን አስተምህሮ ከጀመሩት ውስጥ ደግሞ አውግስጢኖስ አንዱ ነው።
የኛ ቤትክርስቲያን የምታስተምረው አዳም እና ሄዋን በበደሉ ጊዜ ሰውነታቸው መዋቲ፣ ለሃጢአት የተጋለጠ ወይም ሃጢአት ለመስራት ቅርብ የሆነ የተጋለጠ ባህሪን ያዝን የሚለው ነው። ታዲያ ጌታችን ሲወለድ ይህንን የወደቀ ለሃጢአት የተጋለጠ ባህሪ አልያዘም፣ ምክንያቱም እናቱ ድንግል ማርያምም ለዚህ ለሃጢአት የተጋለጠ ባህሪ አልነበራትም ብለን ነው የምናምነው። ለዚህም ነው እመቤታችን ሃሳቧ ሁሉ ስለ እግዚአብሔር የሆነ፣ በስጋም በህሊና(ሃሳብም) ድንግል የሆነች ብለን የምንገልጻት።
ነገር ግን ሰዎች ይህንን አስተምህሮ ያዩና ከጥንተ አብሶ ጋር ያምታቱታል። ነገር ግን ያ ስህተት ነው። ጥንተ አብሶ የሚባለው መጽሃፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ አስተምህሮ ነው።