ምርጧ ፋጢማ የነቢዩ ሙሐመድ ﷺ ቆንጆዋ ልጅ፤ በመልክም፣ በፀባይም በአካሄድም ጭምር ቁርጥ አባቷን ትመስል ነበር ይባላል፡፡ ትህትናዋና ደግነቷ በዝቶ ይወራላታል፡፡ ለአጎታቸው ልጅ ለደጉ ዐሊ ረ.ዐ. በእጃቸው የዳሯት ተወዳጇ ፋጤ ከርሣቸው ወደ አኺራ መሸጋገር በኋላ ምድር ላይ የቆየችው ለስድስት ወራት ብቻ ነበር፡፡ ከርሣቸው ልጆች መካከልም ወደኋላ የቀረችው እሷ ብቻ ነበረች፡፡
ነቢዩ ﷺ ልጃቸው ፋጢማን አብዝተው ይወዷታል፤ እንደ አባት ቅርባቸው፣ እንደ ልጅ ሚስጢረኛቸው ነበረች፡፡ በልዩ ሁኔታ ያዩዋታል፣ ተነስተው ሁሉ ይቀበሏታል፣ ከጎናቸው አስቀምጠው ያወጓታል፤ እርሷም እጅግ እጅግ ትወዳቸው ነበር፡፡ ሊሞቱ አካባቢ ጭምር በቅርቡ ወደኛ ትመጪያለሽ ብለው በጆሮዋ ሹክ ብለዉላታል፡፡ እርሷም ሳቀችም አለቀሰችም፡፡ ሳቋ ወደርሣቸው በቅርቡ የምትሄድ በመሆኗ መደሠቷን፤ እንባዋ ደግሞ እርሣቸው ተለይተዋት ሊሄዱ በመሆናቸው ማዘኗ ነበር፡፡
በበኩሌ ፋጢማ እነዚያን ከርሣቸው ተለይታ የቆየችባቸዉን ወራት እንዴት አሳልፋ ይሆን የሚለዉን ነገር ሳስብ ጭንቅ ይለኛል፡፡ ኢማም ዘሀቢ ሁኔታ “ፋጢማ ከርሣቸው መለየት በኋላ በቁሟ እየሟሟች አለቀች፡፡” በማለት ይገልፁታል፡፡
አንዳንድ ሰው ዱንያን ለቆ ከጎናችን ተነጥሎ ሲሄድ ብቻዉን የሚሄድ አይምሠላችሁ፡፡ ሩሓችን ይዞ የሚሄድ አለ፤ ቀልባችንን ይዞ የሚሄድ አለ፤ ጉልበታችንን፣ ተስፋችንን፣ ብርሃናችንን፣ ደስታችንን ይዞ የሚሄድ አለ፡፡የአንዳንድን ሰው ሐዘን በመፅናናት አይሻገሩትም፡፡ እያደር ይቆረቁራል፡፡
የአንዳንድ ሰዉን ቦታ ማንም ምንም አይሞላዉም፡፡ ነቢዩ የዕቁብ አሥራ አንድ ልጆች ነበሯቸው ግና ስለ ዩሱፍ እንዳዘኑ እንደተከዙ ዐይናቸው ጠፍቷል!!
@heppymuslim29