ወንድሞቼ! ሙስሊሞች በኛ ላይ ካላቸው መብቶች ውስጥ አንዱ እርስ በራስ በኸይር ላይ መረዳዳት ነው። አላህ ﷻ በተከበረ ቃሉ እንዲህ ይላል:-
{ وَتَعَاوَنُوا عَلَى الْبِرِّ وَالتَّقْوَىٰ ۖ وَلَا تَعَاوَنُوا عَلَى الْإِثْمِ وَالْعُدْوَانِ ۚ }
{ በበጎ ነገርና አላህን በመፍራትም ተረዳዱ፡፡ ግን በኃጢአትና ወሰንን በማለፍ አትረዳዱ፡፡ }
ነብዩ ሙሐመድ ﷺ በሀዲሳቸው:
የሙስሊሞች ምሳሌያቸው ሲዋደዱ ሲተዛዘኑ ልክ እንደ አንድ ሰውነት ነው። ያ ሰውነት በሽታ በሚኖርበት ጊዜ አጠቃላይ ሰውነቱ ይተኩሳል ይላሉ። እያንዳዳችን ሰውነታችን አካል ሲያመን ሁሉም አካላችን ይተኩሳል እንቅልፍ ያጣል።ሙስሊሞችም እንደዚህ ናቸው ይላሉ። ሙስሊሞች እንደዚህም ነው መሆን ያለባቸው። ካልሆኑ ሙስሊም ነን ብለው አንዳንድ ሰዎች የዚህ ባህሪ ካልመጣላቸው እንዲመጣላቸው ጥረት ማድረግ ይገባቸዋል። ሙስሊሞች ጉዳት ላይ የምናዝን ማንም ሙሰሊም ላይ የሚፈጠሩ ችግሮች እኛን ሊያስደስቱን አይገባም። ሙስሊም ማለት የሙስሊም ደስታ ሚያስደስተው; እሱ ላይ የደረሰ በላእ ደሞ የሚያሳዝነው ነው።
እርስ በራስ መተራረም የሙስሊሞች መብት ነው። መልካም ላይ ማዘዝ ከመጥፎ መከልከል እነዚህ ሁሉ አላህ ቁርአን ላይ ሰብስቦ ምን ይላል:-
{ وَالْمُؤْمِنُونَ وَالْمُؤْمِنَاتُ بَعْضُهُمْ أَوْلِيَاءُ بَعْضٍ ۚ يَأْمُرُونَ بِالْمَعْرُوفِ وَيَنْهَوْنَ عَنِ الْمُنكَرِ }
{ ምእምንና ምእምናትም ከፊሎቻቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው፡፡ በደግ ነገር ያዛሉ፤ ከክፉም ይከለክላሉ፡፡ }
ይሀውም እንግዲህ አንድ ወንድም ከሌላ ሙስሊም ወንድሙ ካለው መብት አንዱ ከመጥፎ ነገር ሊከለክለው ነው።
የአላህ ነቢ ዐለይሂ ሰላቱ ወሰላም: ዲን ማለት ኸይር ማሰብ(ነሲሀ) ነው ይላሉ። ለማነው ኸይር ምናስበው!? ተብለው ሲጠየቁ; ለአላህ፣ለኪታቡ፣ለመልክተኛው፣ ለሙስሊም መሪዎችና ለአጠቃላይ ሙስሊሞች ብለዋል። ስለዚህ ለአጠቃላይ ሙስሊሞች ኸይርን ማሰብ ይገባል ነው።
ተቀላቀሉ :-t.me/hidaya_multi