🚨 ከሪያል ማድሪድ ጋር በነበረው የመልስ ጨዋታ ዊልያም ሳሊባ ጥሩ ተጫውቷል ነገርግን አንድ ስህተት ብቻ አርሰናል ግብ እንዲቆጠርበት ምክንያት ሆነ።
🔸በክሪስታል ፓላስ ዊልያም ሳሊባ በውድድር አመቱ ብዙ የተሳካ ቅብብሎችን በማስመዝገብ ሪከርዱን ቢያስቀምጥም 1 ስህተት ብቻ አርሰናል ነጥብ ተጋርቶ እንዲወጣ ምክንያት ሆነ።
🔸2 ጨዋታዎች ፣ 99% ምርጥ እንቅስቃሴ ፣ 1% ትኩረት ማጣት ግን አርሰናልን ዋጋ ለማስከፈል በቂ ነበር።
🔸ሳሊባ ባለፉት 3 ጨዋታዎች የሰራው ስህተት (2) ካለፉት 126 ጨዋታዎች በ(1) ጥፋት በልጧል።
🔸አሁንም ጋቢ በጉዳት ከሜዳ ውጭ በሆነበት በዚህ ወቅት የመከላከል ሚና እና የተከላካይ ክፍሉን የመምራት ኃላፊነት ሳሊባ ላይ ወድቋል።
🔸ዊሊያም ሳሊባ በአርሰናል በመከላከል ላይ ያለው ጠቀሜታ እና ተሰጥኦ ለክርክር አይቀርብም...
🔸 ከፒኤስጂ ጋር ለሚደረገው የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ በከፍተኛ ትኩረት እንድትመለስ እንፈልጋለን...! 🤝
SHARE |
@HuleArsenal1