ወጣቱ ልጅ ከመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት አስተማሪው ጋር በአንድ ሰርግ ላይ ይገናኛሉ። ወጣቱም ሮጦ ሄዶ በትህትናናበአድናቆት ሰላም ካለው በኃላ "አስታወስከኝ ወይ" አለው
አስተማሪውም ግራ በመጋባት ውስጥ ሆኖ "ይቅርታ አላስታወስኩህም እንዴት እንደተዋወቅን ልትነግረኝ ትችላለህ?" በማለት መለሰለት
ወጣቱ ልጅም እንዲህ እያለ ተረከለት "3ተኛ ክፍል እያለው ያንተ ተማሪ ነበርኩ። ታድያ አንድ ቀን የክፍል ጓደኛዬን ቆንጆና ልዩ የሆነውን የእጅ ⌚ሰዓቱን ሰርቄበት ነበር። እሱም እያለቀሰ ሄዶ የእጅ ሰዓቱ እንደተሰረቀ ለአንተ ይናገራል አንተም መጥተ ልትፈትሸን ሁላችንንም ክፍል ውስጥ ያለንን ልጆች አይናችንን ጨፍነን እጃችንን ከፍ አዴግን ፊታችንን ወደ ግርግዳው አዙረን እንድንቆም አዘዝከን በዛን ጊዜ እኔ የፍተሻውን ውጤት እያሰብኩ ተረበሽኩ፤ የምገባበትን አጣሁ። አስበው ሰዓቱ በኔ ኪስ ውስጥ ተገኝቶ ሁሉም ተማሪ ሌባ እያለ ሲሰድበኝ፤ ጊቢ ውስጥ መጠቋቆሚያ ስሆን፤ ከት/ቤት ተባርሬ ወላጅ አምጣ ስባልና ወላጆቼ ይሄንን አሳፏሪ ድርጊት ሲሰሙ። በዚህ ጭንቅ ውስጥ እያለሁ የፍተሻው ተራ ደርሶ እጅህ ወደ ኪሴ ሲገባና ሰዓቱን ቀስ አድርገህ ከኪሴ ስታወጣ ተሰማኝ። በቃ መጥፎ ዜናውን ሊናገር ነው አለቀልኝ ብዬ ስጠባበቅ አንተ ግን ምንም ሳትል የመጨረሻው ልጅ ጋር እስክትደርስ ፍተሻውን ቀጠልክ። ፍተሻውም ሲያልቅ አይናቹን ግለጡና ወደየቦታችሁ ተመለሱ አልከን። እኔ ግን መልሰሀሰ ታቆመኛለህ ብለህ መቀመጡን ፈራው።
በጣም ሚገርመው አንተ ሰዓቱን አውጥተህ ለባለቤቱ መለስክለት ግን ከማን ኪስ ውስጥ እንዳገኘህ እና ማን እንደሰረቀበት ምንም አልተናገርክም ነበር በት/ቤት ቆይታዬም ምን እንደተፈጠረ ማንም አላወቀብኝም ነበር፤ አንተም ምንም ብለኸኝ አታውቅም። እኔ ግን ስሜንና ክብሬን እንዳዳንክና ስብዕናዬን እንደጠበክልኝ ዛሬም ድረስ አስታውሳለው። አንተም ይሄንን ታሪክ ቶሎ ትረሳለህ ብዬ አልገምት አሁንስ አስታወስከኝ?" አለው
አስተማሪውም በመገረም ውስጥ ሆኖ "ትንሽ ትንሽ አስታውሳለሁ በማን ኪስ እንዳገኘሁት ግን አላስታውስም፤ ምክንያቱም እኔም ስፈትሽ የነበረው አይኔን ጨፍኜ ነበር!!" አለው
በህይወታችን ለምናከናውናቸው ነገሮች ሁሉ ጥበብ ያስፈልገናል። እንደ አስተማሪ እንደ ወላጅ እንደ መሪ....ወዘተ ...ለአንዳንድ ነገሮች አይናችንን መጨፈን አለብን ምክንያቱም ሁሉም ጥፋቶች በቅጣት ብቻ አይታረሙም‼️
guys ተጫኑ👍😁😂
@huletmelk2