----------👇-----------
👇
✍️አሳዛኝ ታሪክ ነው 👌👇
🛏ሴትየዋ ልትወልድ ኦፕራሲዮን ክፍል አስገቧት ና ቆንጅዬ ወንድ ልጅም ተገላገለች። ልክ ልጇን እንደተገላገለች እሷ ግን አረፈች።ባልየው በጣም አዘነ በራሱ ህፃኑን ተንከበክቦ ማሳደግ ስለማይችልም ህፃኑን
ለአክስቱ አስረከቦ ለ7 ወራት መራራ የሀዘን ግዚያትን ካሳለፈ በኋላ ሌላ ምስት አገባ። ከአዲሷ ሚስቱም አሏህ አንድ ወንድ እና አንድ ሴት ልጅ ሰጠው።
ከ3 አመታት በፊት ለአክስቱ ሰጥቶ የነበረውንም የመጀመሪያ ልጁን ከራሱ ጋ ሊያኖረው አመጣው። ያን ግዜ የአዲሷ ምስቱ ሁኔታ ተቀየረ።ይሄን 4 አመት ማይሞላው ጨቅላ ህፃን ትበድለው ጀመር። ያለ ርህራሄ በተደጋጋሚ ያለጥፋቱ ትቀጣዋለች።
ጭንቀቷ ሁሉ ለራሷ ልጆች እንጂ ደንታም
የላትም።ምግብም ከልጆችዋ ለይታው ለብቻው ነበር ምትሰጠው። የሆነ ቀን እች ሴት ቤተሰቦችዋን እራሷ ቤት እራት ግብዣ ትጣራቸዋለች።
የተለያዩ የምግብ አይነቶች ተዘጋጅተውም ነበር እናም ይሄ እድሜው 4 ማይሞላው ጨቅላ (የሙት ልጅ) ከነዚህ ምግቦች ሊቀምስ እጁን ሲዘረጋ በጣም ትጮህበትና እያመናጨቀችው ከቤት ይዛው ትወጣለች።
ወደ በረንዳ አውጥታው እንግዳ እስኪወጣ ድረስ ከበረንዳ ንቅንቅ እንዳይል ታስጠነቅቀውና ቁራሽ ዳቦ በጁ አስይዛ እዛው
በረንዳ አስቀመጠችው።
ሌሊቱ በጣም ይበርድ ነበር አይደለም ለህፃን ለአዋቂ ከባድ ነበር።ብርዱም በጣም በረታበት ቤት ገብቶ እንዳይተኛ የ አባቱ ሚስት አስጠንቅቃዋለች። ህፃኑም በገዛ ቤቱ ባዳ ሆኖ የሰጠችውን ቁራሽ ዳቦ እየበላ እዛው ተጣጥፎ እንቅልፍ ወሰደው።
ሰዐቱም ረፈደ እንግዳውም ወጣ ሴትዮዋም በረንዳ ያለውንልጅ ረስታው ልጆችዋን ይዛ መኝታ ክፍሏ ገባች። ሰዓቱ ረፍዷል ባል ከስራ አርፍዶ ገባ።
እራት ላቅርብልህ ስትለው ውጭ እንደበላ ነግሯት ልጁ የት እንዳለ ሲጠይቃት "መኝታ ክፍሉ ተኝቷል" አለችው በዛ ብርድ በረንዳ እንደጣለችው ረስታ.. ሰውየውም ተኛ።
ወዲያው የቀድሞ ሚስቱ በህልሙ መጣችበት እና.... "ልጅህን ድረስለት" አለችው።
ሰውየውም ከእንቅልፉ ደንግጦ ተነሳና ልጁ የት ነው ብሎ ሚስቱን ሲጠይቃት..
"አልጋው ላይ ተኝቷል አልኩህ እኮ" አለችው።
ሰውየውም ድጋሚ ተኛ።
ሟች ሚስቱ ድጋሚ በህልሙ መጣች።
"ልጅህን ድረስለት" አለችው። ሰውየው ከመጀመሪያው በጣም ደንግጦ ከእንቅልፉ ነቃ።
"ልጄ የት ነው ያለው?" ብሎ ድጋሚ ጠየቃት ሴትየዋም "ምንድነው ዝም ብለህክፍሉ ምትጨናነቀው ልጁ ተኝቷል አንተም በቃ ዝም ብለህ ተኛ" ትለዋለች።
ሰውየውም ለሶስተኛ ግዜ ተመልሶ ተኛ።እንቅልፍ ሸለብ እንዳደረገው በህልሙ የቀድሞ ሚስቱ ከመጀመሪያው ለየት ባለ ሁኔታ ፊቷን ቀይራ መጣችና..."በቃ ተወው ልጁ እኔ ጋ መጥቷል" ስትለው በድጋሚ ሰውየው ከእንቅልፉ ነቃ።
ልጁ የሚያድርበትም ክፍል በፍጥነት ሲሄድ ልጁ የለም። በድንጋጤ ልጁን ይፈልገው ጀመር... ሁሉም ክፍል ፈልጎ አጣው ድንገት የበረንዳውን በር ሲከፍት... ልጁ በረንዳ ላይ ነው ከብርዱ ብዛት ሰውነቱ ደርቋል።
ጭንቅላቱን በሁለት እግሮቹ መሀል እስገብቶ.... ሴትየዋ ከሰጠችው ቁራሽ ዳቦ ግማሿን በልቶ ግማሹ አጠገቡ ወድቋል።
አባቱ ሲያንቀሳቅሰው ምንም የለም ቀና ሲያረገው ልጁ ግን እችን አለም ተሰናብቷል።ያለ እናት እቅፍ ያደገው ልጅ የእናቱ እቅፍ ናፍቆት ከናፈቃት እናቱም ተገናኝቷል...
# ኢና_ሊላሂ_ወኢና_ኢለይሂ_ራጂዑን
በራሳቹ ልጅ ለይ እንዲደርስ ማትፈልጉትን በሰው ልጅ ለይ እንዲደርስ አትፍቀዱ።
منقول
👌⭕️
https://t.me/abureyan14