የዩኒቨርሲቲው የስፓርት ፌስቲቫል ተሳታፊ ቡድን አሸኛኘት ተደረገለት፡፡
-----
ጥር 16/2017ዓ.ም፤እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
በዚህ ዓመት በሚደረገው የኢትዮጵያ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪዎች የስፖርት ፌስቲቫል ለመሳተፍ
ዝግጅት ሲያደርግ የቆየው የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የስፖርት ቡድን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት እና ምክትል
ፕሬዝዳንቶች በተገኙበት ሽኝት ተደርጎለታል፡፡
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጋርዳቸው ወርቁ (ዶ/ር) በሽኝት መርሐ ግብሩ ላይ ዩኒቨርሲቲው በዚህ ውድድር ሲሳተፍ የመጀመሪያ በመሆኑ ታሪካዊ እንደሚያደርገው ገልጸው ስፖርተኞች ከውጤት ባሻገር ዩኒቨርሲቲውን እና አካባቢውን ገጽታ ፣እንግዳ ተቀባይነት ፣የዩኒቨርሲቲውን አጠቃላይ ገጽታ ማስተዋወቅ
እንደሚገባቸው ተናግረዋል፡፡
ዶ/ር ጋርዳቸው አያይዘውም የስፖርት ቡድኑ አባላት ስፖርታዊ ጨዋነትን በተለበሰ መልኩ የእንጅባራ
ዩኒቨርሰቲ አምባሳደር መሆን እንዳለባቸው መልዕክት አስተላልፈው መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
የስፖርት ሳይንስ ትምህርት ክፍል ኃላፊ መምህር አማረ መብራት በበኩላቸው እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለመጀመሪያ
ጊዜ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የስፖርት ፌስቲቫል በተለያዩ 4 (አራት) የስፖርት አይነቶች እንደሚያሳትፍ
ገልጸዋል።