የአገው ፈረሰኞች በዓልን አስመልክቶ የተዘጋጀው የባህል ሲምፖዚየም በልዩ ልዩ ሁነቶች በድምቀት ተከበረ።
ጥር 22/2017 ዓ.ም፤ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
85ኛውን የአገው ፈረሰኞች በዓልን አስመልክቶ የተዘጋጀው የባህል ሲምፖዚየም በልዩ ልዩ ሁነቶች በድምቀት ተከብሮ በስኬት ተጠናቋል።
በሲምፖዚየም መክፈቻ ስነ ስርዓቱ ላይ የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ዶ/ር ጋርዳቸው ወርቁ የአገውን ህዝብ ቀደምትነት፣ ታሪክ፣ ጥበብ፣ ድንቅ ቅርሶችና የስልጣኔ ባለቤት በመሆኑ ይህን ሀብት ለዓለም ለማሳወቅ ዩኒቨርሲቲው አንዱ የትኩረት መስክ አድርጎ እየሠራ መሆኑን ጠቅሰው የአገው ፈረሰኞች በዓልም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቅርስ ሁኖ እንዲመዘገብ ጥናት በመሥራትና ሳይንሳዊ ማስረጃዎችን በማቅረብ በሀገር አቀፍ ደረጃ የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ እንዲመዘገብ አድርጓል ብለዋል። ይህ ባህል የዓለም ቅርስ ሁኖ በዩኒስኮ እንዲመዘገብ ከዞኑ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ጋር በመተባበር ለሚመለከተው ፌድራል ተቋም ዶክመንቱ ቀርቦ ወረፋ እየጠበቀ እንደሚገኝ አብራርተዋል፡፡
በሲምፖዚየሙ "አሱሪቴ" በሚል በሚታወቀው የአገው ባህላዊ ጨዋታ፣ ክዋኔ፣ ጭፈራ እና በዞኑ በሚገኘው "ባኩንሳ" ብሔራዊ ፓርክ ዙሪያ እንዲሁም የአገው ፈረሰኞች ማህበርን በዓለም አቀፍ ደረጃ ባህል ቅርስነት ለማስመዝገብ ባሉ ስኬቶችና ተግዳሮቶች ዙሪያም ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
https://www.facebook.com/100069178971700/posts/pfbid029fYNqCEHwu5fugYBbaabr5mKwpvYGGmQuNx1nF8YCxEkYKptMKgUCvmSnwvtiy4wl/?app=fbl