በአዳዲስ ቤተ ሙከራ ማሽኖች ላይ ያተኮረ ስልጠና ተሰጠ፡፡
የካቲት 5/2017 ዓ.ም፤እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በኬሚስትሪ ቤተ ሙከራ በአዳዲስ ማሽኖች Gas Cromatography እና High performance liquid chromatography አጠቃቀም ዙሪያ ለኬሚስትሪ መምህራንና የቤተ-ሙከራ ረዳቶች ስልጠና ተሰጥቷል፡፡
የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ላቦራቶሪ ሳይንስ ትምህርት መምህርና የቤተሙከራ አስተባበሪ ወርቅነህ ታምር እንደገለጹት በዩኒቨርሲቲው ከዚህ ቀደም ተገዝተው በመጡ የቤተ ሙከራ እቃዎችን አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ ለተማሪዎች በተግባር የተደገፈ ትምህርት ለመስጠት፣ ለምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት እንዲውል እንዲሁም ከሌላ ዩኒቨርሲቲ የሚመጡ ተመራማሪዎችም በትብብር እንዲሰሩበት የሚያግዝ በዘመናዊ የቤተሙከራ ማሽኖች ዙሪያ ስልጠና መሰጠቱን ተናግረዋል፡፡
አስተባበሪው አያይዘውም የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ቤተሙከራዎችን መደራጃት እና ለመምህራንና ባለሙያዎች ስልጠና መስጠት አስፈላጊ በመሆኑን በተለያዩ ምሁራን ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን
ተናግረዋል፡፡
በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ እና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ የኬሚስትሪ ትምህርት ክፍል ኃላፊ የሆኑት ወዳጄ አዲስ(ዶ/ር) በበኩላቸው ስልጠናው በሁለት መሳሪያዎች Gas Cromatography እና High
Performance Liquid Chromatography ዙሪያ ለ5 ተከታታይ ቀናት መሠጠቱን ገልጸው
የማሽኖቹ አገልግሎትም የደም አይነትን፣ የዘረ-መል ምርመራና የወንጀል ምርመራ ለማድረግ የሚጠቅሙ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
https://www.facebook.com/100069178971700/posts/pfbid022NMprrWKnhvybjHfwpuvWHDFSwe3wPznFYh5VwBfaB1JJb7fUgptE8416x15JrCml/?app=fbl