“ብሄራዊ ጥቅሞቻችንና ቀጠናዊ ትስስር ለሚዛናዊ የሕዝቦች ተጠቃሚነት'' በሚል መሪ ቃል ውይይት ተካሄደ።
የካቲት 10/2017 ዓ.ም፤እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ
እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ከሰላም ሚንስተር ጋር በመተባበር በሀገሪቱ ብሄራዊ ጥቅም እና የህዝቦች ተጠቃሚነት ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሂዷል፡፡
የውይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱት የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት እና የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ተወካይ ክንዴ ብርሃን(ዶ/ር) ዩኒቨርሲቲው ከሰላም ሚንስተር ጋር በመተባበር “ብሄራዊ ጥቅሞቻችንና ቀጣናዊ ትስስር ለሚዛናዊ የሕዝቦች ተጠቃሚነት'' በሚል ርዕስ ያዘጋጀው ውይይት ዋና ዓላማ የውይይቱ ተሳታፊዎች በብሄራዊ ጥቅሞቻች እና በቀጠናዊ ትስስር ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ዶ/ር ክንዴ አያይዘውም የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅምች በግዛት አንድነት መጠበቅ፣ ሰላምና ደህንነትን ማረጋገጥ፣ በተቋም ግንባታ፣ በህብረ ብሄራዊ አንድነት፣ በግብርና(በምግብ ራስን በመቻል)፣በአረንጓዴ አሻራ፣ በትምህርት ጥራት፣ በማህበራዊ ሀብቶች እና ቀጠናዊ ትስስር ላይ የተመሰረቱ መሆናቸውን ገልጸው ይህን ለማድረግ ሁላችንም ሀገራዊ ግዴታችን መወጣት አለብን ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ እንደ ሀገር የዜጎችን ጥቅም እንዲረጋገጥ ትስስር ለመፍጠር እና የሕዝቦች ተጠቃሚነትን ለማስፈን መሰል መድረኮችን በማዘጋጀት ምሁራን ጋር መወያየት እንደሚገባ ገልጸው የዩኒቨርሲቲው ምሁራንም የተለያዩ ጥናቶችን ማድረግ እንደሚጠበቅባቸውም ተናግረዋል፡፡
https://www.facebook.com/100069178971700/posts/pfbid02jkakBjYnNYZbzsNGHHLhK1eKt25dXWBYufJX1ZMTGe6Vq2N7auPUzjvNjJeQqKHAl/?app=fbl